በህግም በኮረናም ተጠርጥረዋል!
ደረጄ ደስታ
15 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ዚምባቡዌ ውስጥ ጓንዳ በምትባል ከተማ ተይዘዋል። አገር አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ በመሰደድ ላይ እንዳሉ አንድ ሰው ቤት ተደብቀው እንደተቀመጡ ነበር በጥቆማ የተያዙት። ፖሊስ ብቻ ሳይሆን የኮረና መርማሪ ግብረ ኃይል አባላት ተሽቀዳድመው ነበር የደረሱት። በተለይ አንደኛው ኢትዮጵያዊ በጠና በመታመሙ ኮረና ቫይረስ ሊኖርበት ይችላል ተብሎ ትልቅ ስጋት ሆኖ ነበር።
በውሃ ጥም ዝሎ የደከመ ቢሆንም የቫይረሱ ምልክት ያልተገኘበት መሆኑ መረጋገጡ ተዘግቧል። ሁሉም ስደተኞች በኮረና ቫይረስ ነጻ መሆናቸው እየተጣራ ድንበር ጥሰው በመግባታቸውም በህገወጥ ድርጊት እሚጠየቁ መሆኑን በሌላኛው ዘገባ ተመልከቷል። ይህ ማለት ከእንግዲህ ከርታቶቹ ስደተኞች እሚታዩበት ሌላ አስቸጋሪ መነጽር ደግሞ መጨመሩ ይሆን?
አንደኛው ዘገባ ይኸላችሁ።