ፀሎተ ሀሙስ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በህጽበተ እግር ታስቦ ይውላል!!! (ቪ.ኦ.ኤ)

ፀሎተ ሀሙስ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በህጽበተ እግር ታስቦ ይውላል!!

ቪ.ኦ.ኤ
የፀሎተ ሀሙስ በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ ትህትናን በማሰብ የተለያዩ ስነ ስርዓቶች ይከናወናሉ።
ክርስቶስ በዛሬዋ እለት የሃዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በማጠብ ትህትናን እና ታዛዥነት ማስተማሩን በማሰብ ነው እለቱ ታስቦ የሚውለው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የፀሎተ ሀሙስ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች የሚታሰብ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሚካሄደው ስነ ስርዓትም የብፁዓን ጳጳሳት ቆሞሳቱ እና ካህናቱ እግር በማጠብ የኢየሱስ ክረስቶስን አርአያነት ተከትለው ስርዓቱን ይፈፅማሉ።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንም ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን በተገኙበት፥ በልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል በዓሉ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተታስቦ ይውላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.