>

"ሕወሃት የዘራችውን ስታጭድ ከማየት በላይ ምን ደስ የሚል ነገር አለ?!?" (ዶ/ር ሰማኸኝ ጋሹ) 

“ሕወሃት የዘራችውን ስታጭድ ከማየት በላይ ምን ደስ የሚል ነገር አለ?!?”

ዶ/ር ሰማኸኝ ጋሹ

ለዘላለም እንገዝበታለን ብለው የዘረጉትን ዘረኛ መዋቅርን በመጠቀም ዶ/ር አብይ ከፌዴራል ስልጣን እየጠራረጋቸው ነው:: ተቋማትን የራሳቸው ስልጣን ለማራዘም ይጠቀሙበት እንደነበረው አብይም ይህንኑ ነው እያደረገ :: ሕወሃት የቀድሞዎቹ ተላላኪዎችዋ ከእርሷ ተምረው ያንኑ ቢያደርጉ ለመተቸት የሞራል ብቃት የላትም:: ደቀ መዝሙሩ ከመምህሩ የተማረውን ያንኑ ያደርጋል:: ኬርያ ኢብራሂም አምባገነን ስርአት ሲፈጠር አልተባበርም ብዬ ነው ስልጣኔን የለቀኩት ያለችው እንኳን እኛን ራስዋንም አያሳምንም:: ያ ሁሉ ትእቢት ተንፍሶ እንዲህ ሲንተከተኩ  ማየትም ትልቅ ነገር ነው::”
የወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም – ይሄ አባባላቸው እራሱ ህግን መጣስ ነው
………………………………………………………………………
“እኔ ሙስሊም ወጣት ሴት ሆኜ የወጣቶችን ነፍስ የታደገውን፣ የሃይማኖት እኩልነት ያረጋገጠውን ሕገመንግስት መጣስ ስለማልፈልግና ሕብረ ብሔራዊ ሥርዓትን አደጋ ላይ የሚጥል አንባገነናዊ ሥርዓት ለመቀበል አልፈልግም፣ አልተባበርም፣ አልፈጽምም” ሲሉ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡
Filed in: Amharic