>

በምርጫ 97 የሰኔ 1 የግፍ ሰለባ የሆኑ የዴሞክራሲ ሰማዕታትን ባልደራስ አስቧቸው ዋለ!!! 

በምርጫ 97 የሰኔ 1 የግፍ ሰለባ የሆኑ የዴሞክራሲ ሰማዕታትን ባልደራስ አስቧቸው ዋለ!!! 

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ 

* ለሰማእታቱ የመታሰቢያ ሀውልት እንዲቆምላቸውም ሀሳብ ቀርቧል
 
ሰኔ 1 ቀን 19 97 ዓ.ሞ በአዲስ አበባ  በግፍ የተጨፈጨፉ ንፁሃን ወገኖችን ሻማ በማብራት አስቧቸው ዋለ።
ህወሃት/ ኢህአዴግ በ1997 ዓ.ም የተካሄደውን 3ኛውን ሃገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ የተከናነበውን ሽንፈት ለመበቀል ፈቃደኛ ባለመሆኑ  ድምፃችን ይከበር ብለው አደባባይ በመውጣት በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን  ያሰሙ  ወጣቶችን ባሰማራቸው  አልሞ ተኳሾች  ጎዳና ላይ ጨፍጭፏቸዋል።
የዛሬ 15 ዓመት ልክ በዛሬዋ ቀን ህወሃት/ኢህአዴግ በንፁሃን ላይ በወሰደው ዘግናኝ እርምጃ አዲስ አበባ በደም ጨቀየች። እናትና አባት ነፃነት እና እኩልነት ፍለጋ የወጡ ልጆቻቸውን አስክሬን ተቀበሉ። የ12 ዓመት ታዳጊ ሳይቀር  ባልሞ ተኳሾች ያለርህራሄ ደረቱን እየተባለ ወደቀ።
ለዴሞክራሲ ÷ ለፍትህ እና እኩልነት ሲሉ ባደባባይ ገላቸውን ለጥይት እየሰጡ እስከወዲያኛው ያለፋትን የአዲስ አበባ ወጣቶች ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት በዋና ፅ/ቤቱ ፕሬዝዳንቱ በተገኙበት በተለያዮ መርሃ ግብሮች አስቦ ውሏል።
ባልደራስ
Filed in: Amharic