>

"አስቸኳይ አዋጁ ሴክሬተሪያት መምሪያ ማን ነው? የትስ ነው ያለው???" (ባልደራስ)

“አስቸኳይ አዋጁ ሴክሬተሪያት መምሪያ ማን ነው? የትስ ነው ያለው???”

ባልደራስ

..”የ”አስቸኳይ አዋጅ  የሚመራዉን አካል እኛም አናውቅም፤ የት መሄድ እንዳለባችሁ መረጃ የለንም!”
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
ፖሊስ ይህን ካላወቀ ሀገሪቷ በማን እየተመራች ነው? ባልደራስ
///
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ለተፈናቃይ ድሆች ያዘገጀው ዕርዳታ በማስመልከት የትብብር ደብዳቤ ለሁለተኛ ጊዜ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቢያስገባም ረ/ፖሊስ ኮሚሽኑ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ ጀማል የጠየቃችሁት  ጉዳይ የሚመራው አስቸኳይ አዋጁ ሴክሬተሪያት መምሪያ ስለሆነ መልስ አንሰጥም ብሏል።
ባልደራስ የአስቸኳይ አዋጁ መምሪያ የት ነው?  ኮቪድ 19 ያሰጨነቃቸው ድሆችን ለመርዳት ትዕዛዝ የሚሰጠዉ አካል ማነው? በማለት ቦታውን ጠቁሙን ለዚህ ክፍል ደብዳቤ እንጽፋለን በማለት ቢጠይቅም ፖሊስ አስቸኳይ አዋጅ የሚመራዉ አካል እኛም አናውቅም የት መሄድ እንዳለባችሁ መረጃ የለንም ሲል ገልጿል። ይህን ክልከላ አስመልክቶ ፖሊስ በደብዳቤ ለማሳወቅ አልፈለገም። ባልደራስ ለአራተኛ ቀን በዋና ጽህፈት ቤቱ የተቀመጠው እርዳታ ለታሰበለት አላማ ህዝብ ጋር እንዲደርስ በተደጋጋሚ ፖሊስን በደብዳቤ መጠየቁ ይታወቃል።
በአሁኑ ወቅት  ለተፈናቃይ ድሆች የዘጋጀው ዕርዳታ ከላይ በመጣ የመንግስት አፈና እንዳይሰጥ ተከልክሏል።
ኮሮና ቫይረስ ለፖለቲካ ሽፋን የሚጠቀመዉ መንግስት የራበውን ህዝብ ለመመገብ ባልደራስ ላይ እገዳ ተጥሏል። ህዝብ ይፈርዳል።
Filed in: Amharic