ባልደራስ መንግሥት ለችግረኞች እንዳይሰጥ የከለከለውን እርዳታ በጽ/ቤቱ አከፋፈለ!!!
* ” እርዳታ ከባልደራስ ተቀበላችሁ!?” በሚል መስተዳድሩ የነዋሪዎችን ቤት አፈረሰ!!!
…”የድሆች እርዳታ በመንግስት አፈና ቢስተጓጎልም ህዝብ ጋር ከመድረስ አንዳችም አልገታንም።
///
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ለተፈናቃይ ወገኖች ለመስጠት ያሰበው የምግብ እርዳታ በዋና ጽ/ቤቱ በትራንስፖርት እንዲመጡ በማድረግ አከፋፈለ።
ድርጅታችን ባልደራስ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት በማውጣት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ድሆች ያዘጋጀው የምግብ እርዳታ በመንግስት ክልከላ ለቀናት እንዲቆይ
መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን በስራ አስፈጻሚ ኮሜቴ የተቋቋመው አስተባባሪ ግብረሃይል የመጨረሻዉን አመራጭ በመጠቀም 6ኪሎ በሚገኘዉ በባልደራስ ዋና ጽ/ቤት ተፈናቃይ ወገኖች እንዲመጡ በማድረግ እርዳታዉን በቢሮ ውስጥ አከፋፍሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባልደራስ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በተለያየ ቦታ አቅም ላጡ አረጋዊያን ድሆችን የምግብ እርዳታ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል።
.”ይሄን ለመናገር ይከብዳል ግን ለምን?
” እርዳታ ከባልደራስ ተቀበላችሁ!?” በሚል መስተዳድር የነዋሪዎችን ቤት አፈረሰ!!!
የኮልፌ ወረዳ 3 አስተዳደር አሁን የሚደርስላችሁን እናያለን በማለት የስነ ልቦና ጥቃት በማድረስ ነፍስ በማያዉቁ ህፃናት አሳዛኝ ድርጊት በኦህዴድ/ብልፅግና ካድሬዎች ተፈጽሟል።
ባልደራስ ቀደም ሲል በአካባቢዉ ላሉ ተፈናቃዮች እና በችግር ለወደቁ ነዋሪዎች የምግብ እርዳታ ለመስጠት ተከልክሎ መመለሱ ይታወቃል። ይህን ወገናዊ ትብብር ያልወደዱ የወረዳው አስተዳደር በጥቂት ቤቶች ላይ ዛቻ ሲፈጽሙ ከርመዉ አሁን አፈረሱብን በማለት ተጎጂዎች በምሬት ይገልፀዋል። ግን ለምን?
ባልደራስ አዲስ አበባ