>
5:13 pm - Tuesday April 20, 5497

"አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌድራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!"  (ዶችቬሌ)

“አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌድራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!” 

ዶችቬሌ

 አቶ ጀዋርን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጥረት የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ከፌድራል የጸጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር።

በሁለቱ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ፍጥጫ ጉዳት ስለመድረሱ ለማወቅ ተችሏል። የፌድራል የጸጥታ አስከባሪዎች ኃይል ጨምረው የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ አመራሮችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉም ታውቋል።

ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ለጊዜው የታሰሩበት ቦታ አልታወቀም።በውጭ አገር የተመሠረተው እና አቶ ጀዋር መሐመድ በኃላፊነት ሲመሩት የነበሩት ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የአዲስ አበባ ስቱዲዮ መዘጋቱ ተረጋግጧል።

የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ የአዲስ አበባ ስቱዲዮ ሰራተኞች በፌድራል የጸጥታ አስከባሪዎች መያዛቸውን በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ ባሰራጨው መረጃ አስታውቆ ነበር። የቴሌቭዥን ጣቢያው ሰራተኞች የት እንደተወሰዱ እንደማይታወቅ ገልጿል።

የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ የድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ከተሰማበት ቅፅበት ጀምሮ በተከታታይ በኩነቱ ላይ አተኩሮ ሥርጭት ሲያከናውን ቆይቷል። 

Filed in: Amharic