

ኦነግ ኦሮሞን በገደለ ቁጥር በአማራ ላይ ሲካሄድ የኖረው የዘር ፍጅት…


አቻምየለህ ታምሩ
የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ሐጫሉ ሁንዴሳን የገደሉት በኦነግ ሸኔ ተልዕኮ የተሰጣቸው የኦሮሞ ተወላጆች መሆናቸውን በአቃቢ ሕጓ በወይዘሮ አዳነች አበቤ አማካኝነት በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ በሰበር ዜና ነግሮናል። የሐጫሉን ግድያ ብቻ ሳይሆን አማራ በኦሮሞ ላይ አደረገ እየተባለ ሲነተርክ የኖረውንና የኦሮሞ ልጆች ሲጋቱት የኖሩትን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሁሉ የፈጸሙት ኦነግ አልያም የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው።
ኦነጋውያን የትግል አባት አድርገው የሚቆጥሩትን ባሮ ቱምሳን የገደለው አብዱል ከሪም ኢብራሂም አሚድ ወይም በጫካ ስሙ ጃራ አባገዳ በመባል የሚታወቀው የእስላማዊ ኦሮሚያ ሪፐብሊክ ግንባር መሪ የነበረው ጨካኝ አውሬ ነው። “ኦሮሞ ከፖለቲካ ስልጣን ተገልሏል” ብሎ ኢስላማዊ ኦሮምያን ለመፍጠር ጫካ የገባው ጃራ አባገዳ ወይም አብዱል ከሪም ኢብራሂም አሚድ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛና ሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ገዢ የነበሩት የፊታውራሪ ኢብራሂም ሀሚድ ልጅ ነው።

ኦነግ የኦሮሞ ትግል አባት ያደረገውን ጀኔራል ታደሰ ብሩን የመሬት ላራሹን አዋጅ ተቃወመ ብለው የገደሉትም ኦሮሞዎች ናቸው። መጋቢት 5 ቀን 1967 ዓ.ም. አዲስ ዘመን ጋዜጣ ካወጣው ሪፖርት ማንበብ እንደሚቻለው ጀኔራል ታደሰ ብሩ ከነ ጭስኞቻቸውና ከኮሎኔል ኃይሉ ረጋሳ ጋር ከሸፈቱበት አስሶ የያዛቸው የኦሮሞ ነገድ ተወላጁ ሻለቃ ተስፋዬ ገብረ ኪዳን ነው። ሻለቃ ተስፋዬ [ኋላ ሌተናት ጀኔራል] የኢትዮጵያ 11ኛው መከላከያ ሚንስትር ሲሆን ከመንግሥቱ ኃይለ ማርያም በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ነበር።
ስለ ሻለቃ ተስፋዬ ገብረ ኪዳን ሲከነክነኝ የሚኖረውን አንድ ነገር ዛሬ ልተንፍሰው። ሻለቃ ተስፋዬ ታህሣሥ 20 ቀን 1971 ዓ.ም. የብርጋዴር ጀኔራልነት ሹመት ያገኘው ከሌተናት ኮሎኔልነት ተነስቶ ማዕረግ ሁለት በመዝለል ነው። የሻለቃ ተስፋዬ ማዕረግ መዝለል በዚህ አላበቃም። የመከላከያ ሚኒስቴር በሆነ ባመቱ በአንድም የጦር ሜዳ ሳይውል የጦር ሜዳ ሜዳይ አንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ። ሁለት ዓመት ቆይቶ ደግሞ በየካቲት ወር 1974 ዓ.ም. ማዕረግ የመዝለል ታሪኩን በመድገም ከብርጋዴር ጀኔራል ማዕረግ በቀጥታ የሌተናት ጀኔራል ማዕረግ ሹመት ተሰጠው። ይህ ሁሉ ሲሆን ሰጪውም አላፈረም ተሸካሚው ሻለቃ ተስፋዬም ከሻለቃነት ተነስቶ የሌተናት ጀኔራልነት ማዕረግ ሲሰጠው ሳይከብደው ተቀበለው።


ይህ ብቻ ሳይሆን ሐውልት የቆመለትን የጡት ቆረጣ ታሪክ ሳይቀር በኦሮሞ ላይ የፈጸመው ኦነግ እንጂ አማራ አይደለም። ይህን ታሪክ ኦሕዴዶችም፣ ኦነጎችም፣ ወያኔዎችም ያውቃሉ። የኦሮሞን ጡት የቆረጠው ኦነግ መሆኑን የማይሞተውን የታሪክ ምስክርነት የሰጠን የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት የነበረው ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ነው። ነጋሶ ጊዳዳ “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” በሚል በተረከውና የሕይዎት ታሪኩን ባቀረበበት መጽሐፉ ገጽ 50 ላይ ኦነግ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሴት ወታደሮችን ማለትም የሴት ኦሮሞ ወታደሮች ጡት ይቆርጥ እንደነበር ባይኑ ያየውን ታሪክ ነግሮናል። ነጋሶ ኦነግ የኦሮሞ ሴቶችን ጡት የቆረጠበትን ታሪክ የኦነግ አምበል የነበረው አባ ቢያ አባ ጆቢር አባ ጅፋር ሳይቀር በሽግግር መንግሥት ተብዮው ምክር ቤት ፊት ቀርቦ እንዳረጋገጠና የሰጠውም ምስክርነት በምክር ቤቱ ላይበራሪ ውስጥ በምስልና በድምጽ ተመርጆ እንደሚገኝ ነግሮናል።
ለኦሮሞ ወጣቶች ግን እየተነገራቸው ያደጉት ቀደም ሲል የቀረቡትን ኦሮሞዎች ሁሉ የገደላቸውና የኦሮሞን ጡት የቆረጠው አማራ እንደሆነ ተደርገው ነው። ይህም በመሆኑ ኦነጋውያን ለፖለቲካቸው መሳከት ኦሮሞን የመስዕዋት በግ እያደረጉ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሲፈጽሙ የኖሩትን ግፍ ግን በአማራ የተፈጸመ እያስመሰሉ ያስተማሩትና አማራን እንዲያጠቃ እያሰለጠኑ ያሳደጉት አንድ ትውልድ አንድ ፖለቲካውን አማራን መፍጀትንና የአማራ የመሰለውን ሁሉ ማውደም አድርጎታል።

እነዚህ የጠቀስኳቸው የዘር ፍጅት ጠማቂዎች ከሐጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን ባላፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ በየማኅበራዊ ሜዲያው ሲያካሂዱ በቆዩት እንቅስቃሴ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እያመረቱ ለኦሮሞን ወጣት አማራ የኦሮሞን መሬት ቀምቶ እንደሰፈረ፣ አማራ ኦሮሞን እንደጨፈጨፈና ጡት እንደቆረጠ ሲያስተምሩ የከረሙ፣ ለበቀልና ለዘፍ ፍጅት ሲያሰለጥኑ የባጁ የኢትዮጵያ ጁቪን ሃብሪማናዎች ናቸው። በጃዋር መሐመድ የሚመራውና የዘር ፍጅቱን ያካሄደው ቄሮም የተደራጀው ሩዋንዳ የተካሄደውን የዘር ፍጅት ያካሄዱትና በቱትሲዎች ጥላቻ የሰከሩ ወጣቶች ኅብረት የነበረው የኢንተርሐሞይ ትጥቅና ዝግጅት እንዲኖረው ተደርጎ ነው።
ይቀጥላል. . .