>
6:13 pm - Monday May 29, 2023

አቤቱ ስለምን አጥሯን አፈረስክ? (ሊቀ ጉባኤ ፋንታሁን ድምጸ)

አቤቱ ስለምን አጥሯን አፈረስክ?

ሊቀ ጉባኤ ፋንታሁን ድምጸ

አይቀርም ግፍ ወደ ተነሣበት ይመለሳል!! የመምህር ዮሐንስን እንባ ሳይ እጅግ እጅግ ስውነቴ ታመመ ወንድ ልጅ አያለቅስም ይባላል ግን ግፉ ምን ያህል ብርቱ መሆኑን የዚህ ሰው እንባ ይናገራል እግዚአብሔር ይፍረድ!!
በልቡናዬ አንድ ቃል ትዝ አለኝ። ነቢዩ ዳዊት ስለኢየሩሳሌም ጥፋት ሲናገር እንዲህ አለ “አቤቱ አጥርዋን ለምን አፈረስክ? መንገድ አላፊው ሁሉ ይቀጥፋታል የዱር እሪያ አረከሳት የሀገር አውሬ ተሰማራባት” መዝ 79፥12  ዛሬ ገጀራ ይዘው የንጹሐንን ነፍስ የሚቀጥፉ ኬኛዎች ጌኛዎች የዱር እሪያ የሀገር አውሬ እንጂ ሰዎች አይደሉም።
ኬኛዎች ሆይ የሰው ልብ ይስጣችሁ ሰው ያድርጋችሁ ሰው አይደላችሁምና። የበላችሁበትን ሆቴል የተማራችሁበትን ት/ቤት የምታቃጥሉ በውኑ ሰው ናችሁ ? አላህ ወአክበር እያላችሁ ሰውን የምታርዱት የእናንተ አላህ በሰው ደም ነው የሚከብረው? አምላካችሁ ሰው ካልታረደ ደስ አይለውም? መስጊድ ሄዳችሁ ባረደው እጃችሁ ነው የምትሰግዱት? ይህንን ነው አምልኮት የምትሉት? ይህንን ነው ዱአ የምትሉት? ለነገሩ እናንተ አላጠፋችሁም ሀጢአታችን ነው ለእናንተ አሳልፎ የሰጠን። አቤቱ በደረሰብን መከራ ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ እንለዋለን እንጂ አንማረርም።
ብቻ ይሁን!! ለእናንተም ይጨልማል ለሁሉም ጊዜ አለው!  እግዚአብሔ ሲነሣ ሾልካችሁ የምታመልጡበት ቀዳዳ የምትሮጡበት ሜዳ የምትጨብጡት ቅጠል የምትጠጉበት ገደል የምትመክቱት ጋሻ የምትደበቁበት ዋሻ አታገኙም። ያረጋዛችሁትን ጉድ ትወልዱታላችሁ የንጹሐን ደም ፈሶ በከንቱ እንደማይቀር ከባለፈው ታሪክ አይተናል።
ሰው ያረዳችሁ ገጀራ ያቀበላችሁ ቤት ንብረት ያቃጠላችሁ ክርሲቲያን ሲታረድ ደስ ያላችሁ የሙስሊም ወጣቶች ታዝባችሁ ዝም ያላችሁ የሙስሊም  ሽማግሌዎች እግዚአብሔር ለይቶ መምታት እንደሚችልበት እንነግራችኋለን። ይልቅስ ልጆቻችሁን ምከሩ!!
* * *
አምቦ ባኮ ከተማ ተወልደው ያደጉት አቶ ዮሐንስ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። በሻሸመኔ ከተማ  ሉሲ አካዳሚ የሚባል ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት ቤት አቋቁመው ለረዥም ዓመታት በከተማው ውስጥ የኖሩ በርካታ የሻሸመኔ ልጆችን በትምህርት ቤቱ እስከ 12ኛ ክፍል አስተምረው ለዩኒቨርስቲ ያበቁ በርካታ ዶክተሮችን ለሀገር  ያፈራውን  ትምህርት ቤት በብዙ ድካም ለፍተው የመሠረቱ ኢትዮጵያዊ ናቸው።በእርሳቸውና በቤተሰባቸው ላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎ ለጥቂት አምልጠዋል።መኖሪያ ቤታቸው ግን ሙሉ ለሙሉ በእሳት ወድሟል ይህንን ሁሉ ሲያደርጉ የነበሩት የኦሮሞ ሙስሊም ተማሪዎች ከሌሎች አሸባሪ ሙስሊሞች ጋር በመቀናጀት ነው።
የዚህ ሰው  ቃለ መጠይቅ በሀዘን ልብ ይሰብራል!!
Filed in: Amharic