>
8:13 am - Friday June 2, 2023

ነፃነት በገጀራ አይመጣም  … ሌሎችም ገጀራ አላቸውና !  (አሌክስ አብርሃም) 

ነፃነት በገጀራ አይመጣም  … ሌሎችም ገጀራ አላቸውና ! 

(አሌክስ አብርሃም) 

ኦሮሚያ ውስጥ ለሽብር የሚሆን ትልቅ ሃይል ተፈጥሯል … ሌላ ክልል ላይ ሂደህ ወጣቱን እንደፈለኩ ልንዳው ብትል አይሰማህም ! ለምን ይልሀል …ትልቅ እውነት ይዘህ እንኳን  ማሳመን ቀላል አይደለም ! ኦሮሚያ ላይ ግን ተጠላህ ተገፋህ፣ተዘረፍክ ፣ተናክ ፣ አባቶችህ ተጨፈጨፉ ተወረርክ በሚል የዓመታት የጥላቻ ስብከት አእምሮውን ለሌሎች አስረክቦ በሩቅ መቆጣጠሪያ የሚታዘዝ ትውልድ ተፈጥሯል ፡፡ ግደል ከተባለ ለምን ሳይል ገጀራውን መዞ ይሮጣል …ይገድላል፡፡አልቅስ ከተባለ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል ፣ሳቅ ከተባለ እየተንፈራፈረ ይስቃል ! ለምን አይልም.. እንዴት አይልም …ካለም በመንጋ ይወገራል ፡፡አልያም እንደሀጫሉ መንገድ ላይ ተገድሎ ‹‹መንግስት  ገደለው›› ይባላል፡፡
እስቲ የትኛው ኦሮሞ ነው ቄሮን ደፍሮ የሚቃዎም …በራሱ ምድር ላይ የራሱን ወገኖች ተው ቢል የሚጠብቀው እንደሌላው ብሔር ሁሉ ተወግሮ መሞት ነው፡፡ ከቄስ እስከ ፖለቲከኛ ከባለሃብት እስከ የኔቢጤ  ሳይወድ በግዱ አንገቱ ላይ ሜንጫ ተደቅኖበት ዳውን ዳውን ሚኒሊክ ሲል ይውላል፡፡ ይሄ ደግሞ በተደጋጋሚ የታየ ነው፡፡ጥቂት ኦሮሞዎች ‹‹ተው ይሄ እርስ በርስ መተላለቅ አይበጅም ›› በማለታቸው ከሃዲ ተብለው ከመፈረጅ ጀምሮ የሚቀምስቱን ፅዋ እያየን ነው !
     የኦሮሞ ህዝብ ነፃ የሚወጣው ገጀራ ይዘው ሰው በሚጨፈጭፉ ዱርየዎች አልያም በየአገሩ መንገድ ላይ እየወጡ እንደበቀቀን በሚጮሁ ጭፍን ጥላቻ ያሰከራቸው ዲስፖራዎች ሳሆን   እውነተኛ ፍትህ አገሪቱ ላይ ሲሰፍን ብቻ ነው፡፡ ፍትህ እንዴት ይስፈን ነው ጥያቄው!  በገጀራ ፍትህ አይመጣም ! ወጣት የሌለበት ክልል የለም … ገጀራ የሌለው ብሔር የለም …ገጀራ በሰው ልጅ ላይ ማንሳት አስተዳደጉ ስለማይፈቅድለት እንጅ ገጀራ የሌለው ብሔር የለም ! ይሄንን መረዳት ነው ቄሮና መሪዎቹ የተሳናቸው፡፡ የእኔን ዘር የሆነ አንድ ሰው  ተገደለብኝ  ብሎ ሌሎችን በግፍ የጨፈጨፈ እንዴት ነው የገደላቸው ሰዎች ወገኖች ነገ ይምሩኛል ብሎ የሚያስበው …የሌሎችን ንብረት ያወደመ እንዴት ነው ሰርቸ አልፎልኝ በሰላም  እኖራለሁ ብሎ የሚያስበው ….
ነገሩ ዓላማ ..የነፃነት ትግል  ምናምን እንደሚባለው አይደለም …እያንዳንዱ ቄሮ አዲስ አበባ ስራ ተገኝቶልሃል ቢባል ገጀራውን ወርውሮ ነው  ክንፍ አውጥቶ ወደአዲስ አበባ የሚሮጠው! እስቲ ቤት የሚያቃጥሉና ንብረት የሚያወድሙ ወጣቶችን ፎቶ ተመልከቱ እንደብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በነዝቅተኛ ኑሮ ላይ ያሉ …የሚለብሱት ደህና ጫማና ልብስ እንኳን የሌላቸው ሚስኪኖች ናቸው ፡፡ (ከታች ያለውንም ሌሎችንም ፎቶዎች ተመልከቱና ታዘቡ)መሪዎቻቸው የሚያደርጉት ሰዓት ቢመነዘር ለአንድ ሰፈር ቄሮ ሙሉ ልብስ ይገዛል፡፡
ታዘቡ … ደህና ልብስ የለበሰ አንድ እንኳን ቄሮ  ረብሻ ውስጥ አይታችሁ ታውቃላችሁ ?….ለምን ሃብታም ኦሮሞዎች መንገድ ሲዘጉ አይታዩም ?…ለምን የደህና ቤተሰብ ልጆች ዱላ ይዘው መንገድ ላይ ሲጎርፉ አይታዩም … ?መልሱ ምን በወጣቸው? ! እነሱ ኢሬቻ ሲከበር ሽክ ብለው ፎቶ ሲነሱ ነው የምታገኟቸው ! ልጆቻቸውን በጊዜ ወደውጭ አገር አልያም አዲስ አበባ ነው የሚልኩት ! ቦታ ቦታ ካስያዙ በኋላ ግን ‹‹ግፋ ለኦሮሞ ነፃነት›› ይላሉ !
 እንደንጉሱ አጎንብሱ ሁኖበት አብሮ ደፋ ቀና የሚለው ሚስኪን ወጣት ከየትኛውም ኢትዮጵያዊ በላይ ራሱም የመንጋው እስረኛ ነው ፡፡እምቢ ማለት አይችልም ፣  ግፋ ሲባል ካልገፋ በመንጋው ይገፋል ! ችግሩ እዚህ ላይ አይቆምም…በመላው ዓለም የሽብር እንቅስቃሴ  ሂደት ውስጥ የምንመለከተው  የመጀመሪያው ዝግጅት በበቂ ሁኔታ አንድን  ወገን መጥላት ነው፡፡ እንደምናየው ይሄ ተሰርቷል ! በዘር በሃይማኖት በብሔር በደንብ ጥላቻ አጠትተውታል! ቀጣዩ  የጠሉትን ወገን ሞት እንደሚገባው መስበክ ነው …በየቀኑ እየተሰራ ነው ፡፡ ከዛስ ካልን  መልሱ ቀላል ነው ….ይሄ በሌሎች መነዳት በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀለት  ነገ ከነገ ወዲያ ህዝብና መንግስት የተፋቸው ራስ ወዳድ መሪዎቹ ይሄን ሚስኪን ወጣት ቦምብ እያሸከሙ አጥፍቶ  እንዲጠፋ መላካቸው የማይቀር ነው !
ለዚህ ደግሞ በስልጠናም ሆነ በትጥቅ ለመርዳት ያሰፈሰፉ የአገር ጠላቶች እንኳን ተጠይቀው እንደውም መግቢያ  ሽንቁር እያነፈነፉ ነው !ይች ገጀራ ሩቅ አታስኬድም ፣መንገድ መዝጋትም ሆነ ንብረት ማቃጠል  ጅማሬዎቹ እንጅ  ዋናው የሽብር ጣራ አይደሉም ፡፡ ቀጣዩ የቄሮ የጥፋት መንገድ ((((አጥፍቶ መጥፋት))))  እንደሚሆን አትጠራጠሩ ! ለዚህ ደግሞ አድርግ ያሉትን ለምን ሳይል የሚያደርግ ለጥፋት የተዘጋጀ ወጣት በጥላቻ ተሞልቶ ተቀምጧል ! እደግመዋለሁ በጊዜ መላ ካልተባለ ፈጠነም ዘገየም የቄሮ ቀጣይ መንገድ አጥፍቶ መጥፋት ነው !! መሪዎቹ እንኳን ባይኖሩ ቄሮ ማንም ኬትም ሁኖ በጥላቻ ከገፋው የሚገፋ ሃይል ነውና !! ወጣቶች ይሞታሉ …ይቆስላሉ ..ሰላማዊ ሰዎች ያልቃሉ …ነፃነትም ይሁን ፍትህ ግን መቸም በዛ መንገድ አይመጣም …ምክንያቱም ነፃነትን የገፈፏቸው እንደጋሪ ፈረስ አይናቸውን ከልለው የሚነዷቸው የራሳቸው  መሪዎች ናቸውና !!
Filed in: Amharic