>

የሀይማኖት እና የጎሳ ጥምር ጥቃት...!!! (ሰላም ሞላ)

የሀይማኖት እና የጎሳ ጥምር ጥቃት…!!!

ሰላም ሞላ

* በአባ ጃራ ራእይ በሼሪአ የምትተዳደር እስላማዊት ኦሮምያን ለመመስረት እንቅፋት ከሆኑት ውስጥ   የኦሮሞ ክርስቲያኖች ናቸው ተብለው በጠላትነት  ተፈርጀው በህቡእ እንቅስቃሴ ስምምነት ላይ ተደርሶባቸዋል።
 
* ኦርቶዶክስ ተጠቃ ስንል ብሄርተኝነት ከሀይማኖት ጋር የተቀላቀለ ለመሰላችሁ 
– የኦርቶዶክስ አማኝ እንጅ አማራ ያልተገደለ ለሚመስላችሁ – አማራ ሙስሊም ቢሆን እንኳ በአማራነቱ ለመታረዱ በቂ ምክንያታቸው ነው!  
 በግብጽ ሴራ በሳውዲ አረቢያ በየመን እና ሱማልያ ትብብር ኦሮሚያን ገንጥሎ እስላማዊ የሼርያ መንግስት ለማቋቋም ከ30 አመት በላይ እድሜ ይዞ የሚሰራ ሀገር የመመስረት እቅድ ነበር(አለ)።
 ይህን እቅድ ለማሳካት እስላሚያ የተባለ ድርጅት የተመሰረተ ሲሆን የድርጅቱ መሪ ጃራ አባገዳ (አብዱል ከሪም ኢብራሂም ሀሚድ )ይባላል። ደርግ የሶማሌን ጦር ካሸነፈ በኋላ ሶማልያ የነበረው የድርጅቱ ቤዝ በጦርነቱ ሽንፈት ምክንያት እቅዱ ከሰመ። ኋላ ህወሀት ወደ ስልጣን ሲመጣ ዳግም ነፍስ ዘራ።
 በደርግ ዘመን ሱማልያ የሚሰለጥነው የጃራ አባገዳ ጦር በሐረርጌ ክርስቲያኖች ላይ የፈጸመውን እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋ የሀረርጌ ክፍለሀገር ነዋሪዎች ከማወቅም ተጠቂ በመሆናቸው የኦሮሞ ህዝብ  ድጋፉን ነፈገው። ፕሬዝዳንት መንግስቱ የዚያድ ባሬን ጦር አመድ ሲያደርገው እስላሚያ የተባለው ድርጅት ተቀበረ። ኋላ አካሄዱን ለውጦ በህወሀት ነፍስ ዘራ።
በአባ ጃራ ራእይ በሼሪአ የምትተዳደር እስላማዊት ኦሮምያን ለመመስረት እንቅፋት ከሆኑት ውስጥ   የኦሮሞ ክርስቲያኖች ናቸው ተብለው በጠላትነት  ተፈርጀው በህቡእ እንቅስቃሴ ስምምነት ላይ ተደርሶባቸዋል።
ይህም ማለት በደርግም በወያኔ አሁን በአብይ ዘመን የጥቃት ኢላማ ከሆኑት ውስጥ ክርስቲያን ኦሮሞዎች አንዱ ናቸው።
 – ሀገር ለመመስረት ሌላው እና ዋናው ችግር ደግሞ ሀገሩን ለ3ሽ ዘመን ሰርቶ ጠብቆ ያቆየው አማራ እና ሌላው ኢትዮጵያን የሚወድ ጎሳ ነው። የአባጃራ እስላሚያ ዋንኛው እቅዱ እነዚህን ማጥፋት ነው። አማራ ፣ አክራሪ እስላም ያልሆነ ኦሮሞ እና ኦሮሞ ያልሆነ ሌላው ጎሳ።
ወያኔ ትግራይ የምትባል ሀገር ለመስራት አቅዶ ሳያስበው 4 ኪሎ ምንልክ ቤተመንግስት ዙፋን ስር ተገኘ። ወያኔ ትግራይን እንደ ሀገር እውን ላለማድረግ አማራን እና ኦርቶዶክስን ጠላት አደረገ። አማራን ነፍጠኛ ነው። ኦርቶዶክስ የነፍጠኛ ሀይማኖት ናት በሚል 1  በጥላቻ የሰከረ ትውልድ ፈጠረ።
አማራ ይሄው ለዘመናት  በጠላት የተከበበ የሙት ፍርደኛ ሆነ። ክሱም ሀገር መውደዱ ነው ተብሎ ተሳደደ። እነዚህ የጃራ አባገዳ እሳቤ ተሸካሚዎች ለአማራ ሙስሊም ጠላት ናቸው። አላማቸው በሸርያ የምትተዳደር ሀገር መስራት ሆኖ እንኳን ጸረ ሰው በመሆናቸው ከኦሮሞ እስላም ውጭ ሰው ሰው አይመስላቸውም።
ሳሳጥረው
በጃራ አባገዳ እስላሚያ ንቅናቄ ዘመን ፣ ኋላ ድርጅቱ ፈርሶ በስውር በኦነግ ሴል በኦህዴድ እና በራሳቸው በስውር ሲንቀሳቀሱ ጠላታቸው አማራ እና የራሳቸውን እሳቤ የማይከተል ኦሮሞ ሆነ።
ወያኔም ጠላቴ አማራ እና ኦርቶዶክስ ናቸው ብሎ ወሰነ። መወሰን ብቻ ሳይሆን በመዋቅር ደረጃ ሰራበት። መንግስት እያለ ኦሮሚያ ውስጥ የተማረ ትውልድ ከመስራት ይልቅ አውዳሚ ትውልድ ፈጠረ።
በኢትዮጵያ ሚሊኒየም የታቀደው እና አሁን ውጤቱ ፍንትው ብሎ የወጣው በነአባዱላ ዘመን ፓርላማ ፓስተሮች ገብተው አምልኮ ሲፈጽሙ የምናስታውሰው እና ከአውሮጳ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ያለው እቅድ የፕሮቴስታንት መንግስት መመስረት አላማ ያለው ነው።
 አላማ ብቻ ሳይሆን ተሰርቶበት ፍሬ አፍርቶ አሁን የኦህዴድ ኦዴፓ መዋቅር ከላይ እስከታች በአንድ ሀይማኖት ስር የወደቀ እና እነ ለማ መገርሳም ከኦርቶዶክስ ቤተመቅደስ እየወጡ ሀይማኖታቸውን የቀየሩት ድምጹን አጥፍቶ በህቡእ የተሰራው የፕሮቴስታንት መንግስት ምስረታ ንቃናቄ አንዱ ነው።
በነገራችሁ ላይ የሁሉንም ሀይማኖማት እንደ ችግር ቆጥሬው ሳይሆን የእኔ ብቻ ሀይማኖት ይንገስ የሚል ጽንፈኛ አካሄድ ልክ ባለመሆኑ ነው። ይሄ በመዋቅር ደረጃ የተደራጀው የእምነት መንግስት ብዙ ግዜ ሀይማኖታዊ ጥቃቶች ሲፈጸሙ ከተጠቂዎች እንደምንሰማው ባላየ ማለፉ እና ቢደርስ እንኳን እርምጃ እንዳይወስድ ተጽእኖ መፍጠሩ ነው።
ኦነግ የኦሮምያ ሰራዊት ብሎ ከ30 + አመት በላይ ተደራጀ። ኦነግ ጠላቱ ተመሳሳይ ነው። አደረጃጀቱ ክርስቲያን ኦሮሞዎችንም ያቀፈ በኋላም በግልጽ ድርጅቱ በሀይማኖት ልዩነት ለመሰንጠቅና ጃራ አባገዳን እስከመግደል የሚያደርስ ልዩነት ገብተው ተለያዩ። አላማቸው እና ጠላታቸው 1 ነው።
 ኢትዮጵያ ልባቸው ውስጥ ያለችባቸው ጎሳዎች በዋንኛነት በቁጥር ከኢትዮጵያ ህዝብ አንደኛ ሁኖም ለኢትዮጵያ እየታረደ የሚኖረው ዐማራ፣ በረዥም ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ዋና የነበረችው ኦርቶዶክስ እና ለአላማቸው እንቅፋት የሆኑ የጋራ ጠላት ሆኑ።
Filed in: Amharic