ልደቱ አያሌው በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፓርቲያቸው አስታወቀ!!!

ልደቱ አያሌው በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፓርቲያቸው አስታወቀ!!!

በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ በቢሻፍቱ የተደረገውን አመጽ በማስተባበር እና በገንዘብ በመደገፍ በሚል ፖሊስ ጠርጥሮ ማሰሩን ፓርቲያቸው አረጋግጧል።
ልደቱ አያሌው ለአገሪቱ የፖለቲካ ችግር ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ህገ መንግስቱን መተርጎም ሳይሆን ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ድርድር ማድረግ መፍትሄ መሆኑን በግንባር ቀደምትነት ጠቁመው ሲከራከሩ የነበረ ሲሆን የአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ከመምጣቱ በፊት ከጃዋር ጋር ቀርባው ቃለ መጠይቅ ከሰጡ በሁዋላ የደህንነት ሰዎች ይከታተሉዋቸው እንደነበር መግለጻቸው አይዘነጋም።
የእነ አቶ ልደቱን እስር የጠቅላይ ሚ/ር ኣብይ አህመድ አስተዳደር አጋጣሚውን አስታኮ ተቀናቃኞቹን ለማፈን እና ባቀጥታ በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩትን ለመፍታት ማሙያ እንዳደረጋቸው ገና ሳይታሰሩ ታስረዋል ተብሎ ሲገለጽ ነበር።ዛሬ ከታሰሩም በሁዋላ ተመሳሳይ አስተያየቶች መንሸራሻር ቀጥሎዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.