>
5:14 pm - Monday April 20, 6099

በትርክት የተፈጠረው የነፍጠኛ ሥርዓት ሲፈተሽ. . .  (አቻምየለህ ታምሩ)

በትርክት የተፈጠረው የነፍጠኛ ሥርዓት ሲፈተሽ. . . 

አቻምየለህ ታምሩ

የነፍጠኛ ሥርዓት የሚባል የመንግሥት ሥርዓት በኢትዮጵያ የሥነ መንግሥት ታሪክ ውስጥ ኖሮ አያውቅም። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ  የነበረው የመንግሥት ሥርዓት የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ብቻ ነበር። የነፍጠኛ ሥርዓት የሚለው ያልነበረ በትርክት የተፈጠረ ማጭበርበሪያ ፖለቲካቸው የዘር ማጥፋት የሆነው የኦሮሞና የትግሬ  ብሔርተኞች አማራ ላለማለት የሚጠቀሙበት የኮድ ስም ነው።
ኦነጋውያን በጩኸታቸው ሊነግሩን እንደሚፈልጉት የነፍጠኛ ሥርዓት ማለት ነፍጥ አንግቦ ይገዛ የነበረ ስርዓት የነበረ ቢኖሮ/ ቢሆን ኖሮ የነፍጠኛ ሥርዓትን እየተዋጋን ነው በሚሉበት በዚህ ወቅት  በሻሸመኔ፣ በዝዋይ፣ በአጋርፋ፣ በኩየራ፣ በምዕራብ አርሲና በሌሎችም ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ በሚገኙ ከተሞችና ወረዳዎች ውስጥ በግፍ የተፈጀው፣ ስሙ እየተጠራ በዱልዱም የታረደው፣ እድሜ ዘመኑን የለፋበት ሀብቱ ዶግ አመድ የሆነውና የተፈናቀለው  መሳሪያ ያልተጠቀው ምስኪን አማራ አይሆንም ነበር።
በመሰረቱ ፍጠኛ ማለት የተነጠቀ ርስቱን ለማስመለስ፣ በወራሪ የተቀማውን ባድማ ለማስከበርና አገሩን ከወራሪ ለመጠበቅ የተሰማራ አርበኛ ማለት ነው።ርስቱን ለማስመለስ፣ ባድማውን ለማስከበርና አገሩን ለመጠበቅ የዘመተ አርበኛን የሚጠሉ ቢኖሩ ከርስቱ ያፈለሱት፣ ባድማውን የወሰዱበትና አገሩን ያጠፉ ሕገ ወጥ ወራሪዎች ብቻ ነው።
የአርበኛነት ተግባር የሆነውን ነፍጠኛነት ጭራቅ ሲያደርግ የሚውል ሁሉ የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ የሌለው የእውቀት ጾመኛ ብቻ ነው። በየትም ዓለም መንግሥት ማለት  ሕግና ሥርዓት ለማስከበር፤ ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ ጉልበት የመጠቀም  ሕጋዊ  መብት ያለው ብቸኛው አካል ነው።
አንድ አካል  መንግሥት የሚሆነው  ነፍጥ ታጥቆ  ጉልበት እንዲጠቀም ነው።  በሌላ አነጋገር  መንግሥት ሕግና ሥርዓት  የሚያስከብረው፤ ሰላምና ጸጥታ የሚያሰፍነው በአበባ ጉንጉን ተሽቆጥቁጦ ሳይሆን ደፍጥጦ የሚያነድ ነፍጥ ታጥቆ ጉልበት በሚጠቀም ኃይል ነው። ፈረንጆቹ ይህንን  ለመንግሥት  ብቻ የተሰጠ መብት “ጉልበት የመጠቀም  መብት” ወይም  በእንግሊዝኛ  “Monopoly of violence”  or  “Monopoly of  legitimate use of physical force” ይሉታል።
ባጭሩ  በዓለም ላይ ያለ መንግሥት የሆነ  አካል ሁሉ በመንግሥትነት የተሰየመው  ነፍጥ አንግቦ፤ ኃይል የመጠቀም ብቸኛ  ሕጋዊ መብት ተጎናጽፎ ነው። ይህ በዓለም ላይ ያሉ መንግሥታት ሁሉ ነፍጠ ታጥቀው  ጉልበት/ኃይል  በመጠቀም ሕግና ሥርዓት እንዲከበር፤ ሰላምና ጸጥታ እንዲሰፍን የሚያደርጉት የመንግሥትነት ግዴታ በቤተ ኦነግ ዘንድ የነፍጠኛ ሥርዓት አራማጅነት ነው።
ይቀጥላል …
Filed in: Amharic