>
5:13 pm - Tuesday April 19, 7031

የኢፌዲሪ ጠ/ ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከፋና ቴሌቪዥን የትግርኛ ፕሮግራም ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ -  ዋና ዋና ነጥቦች:-

የኢፌዲሪ ጠ/ ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከፋና ቴሌቪዥን የትግርኛ ፕሮግራም ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ –  ዋና ዋና ነጥቦች:

EPA

– የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ምሰረታ ጀምሮ ወሳኝ ተራ የነበረው ትልቅ ህዝብ ነው፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ንቁ ተሳትፎ ያላደረገበት ግዜ የለም ለወደፊትም አይኖርም የሚል እምነት ነው ያለኝ።
– በለውጥ ግዜ ችግር መፈጠሩ የለውጡ ባህሪ ነው። እናት ምጥ ችላ ልጅ እንምትወልደው ሁሉ እዚህም ትንሽ መታገስ ጥሩ ነው በቅርብም ችግሮቹ ሁሉ ቀስ በቀስ ይፈታሉ ብዬ አምናለሁ።
– በህወሓት እና ብልፅግና መካከል ልዩነት እንዳለ ግልጽና ሁሉም ሰው የሚያውቀው የአደባባይ ሃቅ ነው። በፌደራል እና በክልል ያለው እሰጥ አገባ በትግራይ ተጨማሪ ችግር መፍጠሩ ግልጽ ነው ምክንያቱም አብረህ ተነጋግረህ የማትሰራ ከሆነ ችግሮች እንደሚፈጠሩ ግልጽ ነው።
-እኛ እንደብልጽግና ተፈጥረው ያሉ የሃሳብ ልዩነቶች በጠረጴዛ ዙርያ ለመፍታት ፍላጎት አለን። በህወሓትም በኩል ነገሮች በውይይት እንዲፈታ የሚፈልጉ አመራሮች እናቃለን ነገር ግን ጥቂቶች ከህወሓት ጋር ያሉ ደሞ ከዚህ በተቃራኒ መፍታት የሚፈልጉም ክፍተቱ ለማስፋት የሚሰሩም እንዳሉ ለሁሉም ግልጽ መሆን አለበት።
– የትግራይ ህዝብ ወደ ጦርነት እንዲገባ እየገፋፉት ያሉ ሰዎችን ተው ሊላቸው ሊመክራቸው ይገባል። ይህ ለማድረግ የትግራይ ህዝብ የአቅም ችግር እንደሌለው አውቃለሁ፤ በአንጻሩ ደሞ ሰላም ለሚፈልጉት መሪዎች መደገፍ አለበት ይሄን ህዝቡ ካደረገ አብዛኛው ችግሮች ይፈታሉ የሚል እምነት አለኝ።
– በህወሓት እና ብልጽግና የተፈጠረው ልዩነት በማስፋት በዚህ ክፍተት የሚኖሩ ሃይሎችም አሉ።
-ትግራይ ለመጉዳት የሚባል ሃሳብ በእኔ በኩል ፍጹም የለም። በመንግስት ውስጥ እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ያለው ሰው ካለ ችግር ውስጥ ነው ያለው ነው ማለት ሊታገዝ፣ ሊገመገም ራሱም ባህሪው ማየት ይገባዋል ብዬ አምናለሁ።
-ከዚህ ውጪ ያለውን የፖለቲካ ጨዎታዎች ግን ህዝብ ጋር ጨምረህ ማየት ልክ አይደለም።
-ለውጡ ሲመጣ በመጀመርያ ደረጃ ከሰራናቸው ውስጥ የሚዲያ ነፃነት ነው፤ ይሄ ደሞ ሁሉም ሰው ዓለምም የሚያውቀው ሃቅ ነው። በትግራይ ክልል ያሉ ሚዲያዎች ሆነ እዚህ ያሉ ሚዲያዎች ችግር እንዳለባቸው እናቃለን በሂደትም ችግሮቻቸው ይፈታሉ ብለን እናስባለን።
-በትግራይ ላይ ያሉ ሚዲያዎች ግለሰብ ለመስደብ ሌትና ቀን እየሰሩ እንደሆነ እያየን ነው። ከአርቲስት ሃጫሉ ሞት ጋር በተገናኘ የነበረው ግርግር እንዲባባስ ሲያራግቡ ነበር፤ ይሄ ትልቅ ስህተት ነው። የሃጫሉ ሞት ድንገት ነው የሰማነው መንግስት እንዲያረጋጋ ሊያግዙን ሲገባ በሚዲያ እንዲባባስ ማድረጋቸው ስህተትና ያልጠበቅነው ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ የብሮድካስት ባለ ስልጣን ሃገር ለማዳን ጊዝያዊ እርምጃ ወስዷል።
-የምርጫ አስፈላጊነት እና ግዴታ መደረግ እንዳለበት ልዩነት የለን አይመስለኝም። ምርጫ ለማድረግ ቀጠሮ ይዘን እየተዘጋጀን እያለ ድንገት ሳናስበው የኮቪድ 19 በሽታ መጣ፤ የፌደሬሽን ምክርቤት ሁሉም ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች እንዲቀጥሉ ወስኗል። ይሄ ለብልጽግና ይሰራል ለህወሓትም ይሰራል፤
-ምርጫ የማይቀር ነገር ሁኖ እያለ የትግራይ ክልል መንግስት በሚልዮን ብር የሚቆጠር በጀት መድቦ ምርጫ አደርጋለሁ ማለቱ የሚገርም ነው።
– ኮቪድ 19 እያለ ምርጫ እናደርጋለን ማለት ኮቪድ19 ለትግራይ ስጋት አይደለም ማለት ነው፣ ትግራይ ላይ ሰው በኮረና አይያዝም ማለት ነው፣ ዘመናዊ ሆስፒታልና መድሃኒት አለን ማለት ነው ነገሩን ምክንያታዊ ሆኖ ለመረዳት ከባድ ነው። ኮረና አይደለም ለኢትዮጵያ ይቅርና ለአሜሪካ እንዴት እያደረጋቸው እንዳለ እያየን እንዴት በትግራይ ላይ ችግር አይፈጥርም ብለህ ጥያቄ እንድታነሳ ያደርጋል።
-የትግራይ መንግስት ሚልዮኖች አውጥቶ ምርጫ አደርጋለሁ ከሚል ሁለት ሶስት የውሃ ጉድጓድ ለምን አያሰራም ትግራይ ላይ የውሃ ችግር እንዳለ ይታወቃልና፤ ወይ ደግሞ አንድ ሆስፒታል ለምን አያሰራም ብለህ እንድትጠይቅ ያስገድዳል።
– ለልማት በጀት አጠረን፤ ፌደራል መንግስት በጀት ከለከለን እያሉ ለምርጫ የሚሆን ሚልዮኖች በጀት አውጥተን ማድረግ አለብን ማለታቸው ይገርመኛል፤
– ህወሓት ምርጫ እያለ ያለው ሌላ አማራጭ ላላቸው ሰዎች ማስረከብ ፈልጎ ነው እንዳይባል የተለየ ሃሳብ የያዙ ሰዎች ታፍነው ነው ያሉት ራሱ ተመልሶ ለመምጣት ከሆነ ደሞ የፌደሬሽን ምክርቤት እኮ ምርጫ እስኪደረግ ስልጣን ላይ እንዲቆይ ፈቅዶለታል። ትንሽ ግዜ ታግሶ ባገር ደረጃ ምርጫ ማድረግ ሲገባና በጀቱን የውሃ ጉድጓድ ማስቆፈሪያ፣ ሆስፒታል ማሰሪያ ቢጠቀሙበት ይሻል ነበር ብዬ አስባለሁ።
-የፌደራል መንግስት በክልል ጉዳይ ላይ እጁን አስገብቶ አያቅም ለወደፊቱም አያስገባም። ይሄን ስል ግን የፌደራል መንግስት ሃላፊነቱ አሳልፎ አይሰጥም ይሄ በህገ መንግስቱ የተሰጠን የስልጣን ክፍፍል ኣለ።
-የትግራይ መጠቀም ለኢትዮጵያ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም። ለይተህ ትግራይ ማጥቃት የሚባል ሃሳብ የፌደራል መንግስትም ብልጽግና ፓርቲም የላቸውም፤
-በኢትዮ ኤርትራ ያለው ግንኙነት በሁለት ሃገራት ያለ ግንኙነት ስለሆነ የፌደራል መንግስት ስራ እና ሃላፊነት ነው። አሁን ተገኝቶ ያለው ሰላም ለትግራይ ህዝብ ብቻ አይደለም የሚጠቅመው ለሁላችንም ነው የሚጠቅመው። የተጀመረው ግንኙነት አጠናክረን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታችንም ለማጠናከር እየሰራን ነው ያለነው።
-ማን ማንን ነው የሚወጋው፤ ለምንድነው የፌደራል መንግስት ትግራይ ክልልን የሚወጋው፤ ይሄ የእብደት ንግግር ነው። ከተናጋረው የደገመው ይብሳል፤
– የፌደራል መንግስት የትግራይን ህዝብ ሊወጋ ነው ብሎ ማሰብ ምን አይነት ሃሳብ እንደሆነ አይገባኝም። አይደለም ከህዝባችን ጋር ከጎረቤት አገሮች ጋር ውጊያ አንፈልግም እያልን እኮ ነው ያለነው፤
-ጦርነት የሚፈልጉ ሰዎች ጦርነት ጦርነት ይላሉ እንደ ዘፈን ጥዋትና ማታ የጦርነት ንግግር ሲናገሩ ትሰማለህ፤ ራሳቸው የሚያሰቡትን ነው እየነገሩን ያሉት።
-በዚህ ዘመን ጦርነት የሚያስነሳ ምክንያት አለ ብዬ አላምንም። በሁሉም በኩል አንዳንድ ወጣ ያሉ የፖለቲካ ጫዋታዎች ሊታዩ ይችላሉ፤ ነገር ግን ወደ ውግያ ሊያስኬድ የሚችል አይደለም አይገባምም።
-የኢትዮጵያ መንግስት ለኤርትራ መንግስት ጠርቶ ኢትዮጵያ ውጋ ብሎ ይጠራል ብሎ ማሰብ ሃጥያት ነው። እንዴት ብሎ ነው ህዝቤን ውጋልኝ ብሎ የሚጠራው፤ ይሄ በታሪካችን አልታየም ለወደፊትም አይኖርም፤
– የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች ጋር ያላባትን ችግር ለመፍታት እየሰራ ነው ያለው።
-የትግራይ ህዝብ ከህወሓት አመራሮች ውስጥ እንደነ ዶ/ር ደብረጽዮን ያሉ ሰዎች ልማት እና ሰላም ስለሚፈልጉ ሊደግፋቸው ይገባል የሚል እምነት አለኝ። እነ ዶ/ር ደብረጽዮን ከመጀመርያው ጀምሮ ከፌደራል መንግስት ጋር ያላቸው ችግር በውይይት ለመፍታት ዝግጁ ነበሩ ይሄ ከትግራይ ህዝብ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል በተለይ ለዶ/ር ደብረጽዮን ካገዙት አብዛኛው ያሉትን ችግሮች ይፈታሉ ብዬ አስባለሁ፤ በሌላ ጎን ደሞ ሰላም ለማይ ፈልጉ ሰዎች ተው የጥፋት መንገድ ነው ሊላቸው ይገባል።
-የትግራይ ህዝብ ለዚህ ወቅት የሚመጥኑ የተማሩ ወጣቶች አሉት። በልጆቻቸው እና በልጅ ልጆቻቸው እምነት ሊኖራቸው ይገባል። ትግራይ ሆነ ኢትዮጵያ በትላንትና ሃሳብ ከሃምሳ እና ስድሳ አመት በፊት የነበረ ሃሳብ መምራት አይቻልም።
– የራስህን ህዝብ በመደብ ከፋፍለህ ግማሹ የኔ ነው፤ ግማሹ ተከፋይ ነው፤ ሌላው ባንዳ ነው እያልክ መምራት የሚቻል አይመስለኝም፤ ይሄ ከፋፋይ ሃሳብ ትላንት ሰርቶ ሊሆን ይችላል ዛሬ ግን ይሰራል ብዬ አላስብም።
-በልጆችዋ የማትተማመንና በአዲስ ትውልድ የማትመራ ትግራይ ልትቀየር፣ ልትለወጥ፣ ልትለማና ካሉባት ችግሮችዋም ልትወጣ አትችልም፤
-ሰው በሆነ ግዜ ሃሳብ ሊኖረው ይችላል ነገር ግን ያቺ አቅም ሁሌ ቁጭ ብላ አትጠብቅም፤ አዲስ ትውልድ እየመጣ መሄድ አለበት።
-በአዲሱ ትውልድ እምነት ከሌለህ እያገዝክ ካላበቃሀው በቀጣይነት ልማት ማምጣት አይቻልም።
– ትግራይ እንደምናቃት ጥሩ ሚና እንድትጫወት ከተፈለገ አዲሱ ትውልድ መተካት አለበት የሚል እምነት አለኝ።
– ትግሉ የመሩ ኣባቶችም በትላንት ችሎታቸው እና ማንነታቸው የዛሬ ፍላጎት መመለስ እንደማይቻል አውቀው፤ ትላንት የራሳቸው ታሪክ እንደሰሩት ሁሉ የዛሬ ትውልድ ወጣቱም የራሱ ታሪክ መስራት እንደሚፈልግ ተረድተው ልጆቻቸው እና ልጅ ልጆቻቸው ከነሱ በተሻለ የተማሩ አቅም የፈጠሩ መሆናቸው አምነው አዲሱ ምዕራፍ ለአዲሱ ትውልድ ሊሰጡት እንደሚገባ አምናለሁ።
Filed in: Amharic