
የፀረ-ኢትዮጵያኖቹ ድሪያ – (የጅብና የአህያ ጋብቻ)….!!!

ደሴት ኢትዮጵ
ከለውጡ በሗላም ሆነ በፊት ኦሮሚያ ውስጥ የተካሄደው ዘርንና ሐይማኖትን ማእከል ያደረገ ጥቃትና ውድመት ኦሮሚያን ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን የማፅዳትና የኦሮሚያን ነፃ አገርነት የመመስረት አንዱ እርምጃ ነው ። እነ ነጀዋር መሐመድ ፣ ፀጋዬ አራርሳ ፣ እስቄል ጋቢሳ ወዘተ … ይህንን አጀንዳ በፊት አውራሪነት የሚያራምዱም ናቸው ። ሁሌም በነሱ መሪነትና አስተባባሪነት በሚኖሶታ በተደጋጋሚ በተደረጉ
የድጋፍና የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ” Ethiopia out of Oromoya ” የሚል መፈክር በከፍተኛ ጩኸትና የቀለም ድምቀት ሲቀነቀን ሰምተናል ፤ አይተናል ። ኢትዮጵያን ከኦሮሚያ ምድር የማውጣት መገለጫው ሌሎችን ብሔሮች በዚህ መልኩ በማጥቃት እንደሆነ እየታየ ነው ።
.
ቀደም ባሉት የወያኔ አመታት በአርሲ አርባ ጉጉ ፣ በሐረር-በደኖ ፣ ወተርና ግራዋ ወዘተ የአማራ ብሔር ተወላጆች ኢላማ ተደርገው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ። … በደቡብ ኦሮሚያ የጌዶዎ ብሔር ላይ ግዙፍ የማፈናቀል እርምጃ ተካሂዷል ። በቅርብ አመታት በቄሮ እንቅስቃሴ ወቅት በወላይታ ላይ ፣ በአዲስ አበባ ከተከበረው የእሬቻ በአል መልስ በቡራዮ ከተማ በጋሞ ሕዝብ ላይ ፣ ጀዋር ” ተከበብኩኝ ! ” ባለበት ወቅት በብዙ የኦሮሚያ አካባቢዎች ፣ ሐጫሉ በሞተበት ወቅት አሁንም በብዙ የኦሮማያ ከተሞች በአማራና ጉራጌ እንዲሁም በኦርቶዶክስ አማኞች ላይ የተደረገው ጥቃት የ” Ethiopia Out Of Oromia ” ፕሮጀክት አንዱ አካል ነው ።
.
ተጠቂዎች ቀደም ሲል ጥናት ተደርጎባቸውና ኢላማ ተደርገው
የተካሄደ መሆኑ ብዙ መረጃዎችና የተከሰቱት ጥፋቶች እየመሰከሩ ነው ። የምስራቅ አፍሪካ ክፍል ሁማን ራይት ወች ነሐሴ 2/2012 ባወጣው መግለጫም ” በኦሮሚያ አርሲና ባሌ ብሔርና ሐማኖትን ኢላማ ያደረገ የደቦ ጥቃት በዜጎች ላይ መፈፀሙን አረጋግጧል ። ኢትዮጵያን የመበታተን አንኛው መርሐ-ግብር ….. በዚህ መልኩ ኦሮሚያን ከሌሎች ብሔሮች በማፅዳት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ያሳያል ።
.

ኢትዮጵያ መረጃዎች ተመሳሳይ ነው ። አንዱ በአንዱ ቴሌቪዥን እየተገለገለ ነው ። ሁለቱን ያጣመራቸው ዋነኛ የጋራ አጀንዳ ኢትዮጵያን ፣ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊነትን የመጥላት ፤ ከዚያም ተሻግሮ ኢትዮጵያን የማፍረስና ትንንሽ የራሳቸውን የመንደር መንግስት የመመስረት ፍላጎት ነው ። በዚህም ፈጣኑና አስገራሚውን ጥምረት ሊያሳዩን ችለዋል ።
.
ከዚሁ ጋ ተያይዞ ጠቅ/ሚንስትሩ በፓርላማ ንግግራቸው ” ኢትዮጵያን የምታፈርሱት መጀመሪያ እኛን ማፍረስ ስትችሉ ነው ” ብለዋል ። ይህ ከፍተኛ ተስፋ የሚያሳድርና የሚያነቃቃ ንግግራቸው ኢትዮጵያዊ የሆኑትን ሁሉ በሐሴት የሞላ ነው ። ለዚህ ጠንካራ ሐሳባቸው ምስጋና ይድረሳቸው ። ለንግግራቸውም ተግባራቸውን በአፋጣኝ እንሻለን ።
.
ኢትዮጵያችን ከነክብሯ ለዘላለም ትኑር !!!