የአራጆቹን ወንጀል በጋራ ማውገዝ ይቀድማል ወይስ ድርጊቱን መሸፋፈን???
ዘመድኩን በቀለ
ሰሞኑን ወጉ ደርሶን ከፍርሃት ቆፈን ተላቀን በመጠኑ ዓለምአቀፍ እንቅስቃሴ ማድረጋችንን ያዩ አንዳንድ ሁሌ እንግደል፣ ሁልጊዜ እንረድ፣ ሁልጊዜ እናቃጥል፣ ሁልጊዜ እናፈናቅል፣ እናውድም ባዮች በየሚድያቸው ስሜን ጠቅሰው ሲንበጫበጩ እያየሁ ነው። ነውረኞች የሞትን እኛ። አታልቅሱ ድምጽ ቀንሱ፣ ዓለም አይስማው የምንባል እኛ። እና እኔ ዘመዴ መስሚያዬ ጥጥ ነው።
•••
ምድረ አራጅ ሁላ ድርጊቱን በጋራ ማውገዝ ይቀድማል ወይስ ድርጊቱን መሸፋፈን? አላህ ወአክበር ብለው ያረዱትን አይወክሉንም ማለት የአባት ነው። እሱ የጨዋ ደንብ ነው። ወንጀለኛን አጥፈን ማውገዝ ትቶ እስልምና ተነካብን ብሎ ማለቃቀስ ነውር ነው። በባሌ በአደባባይ ከካፊሮች ጋር አትገበያዩ፣ ካፊር ቤትም፣ መሬትም፣ ሱቅም ያከራያችሁ በአስቸኳይ አስወጡአቸው እያለ ሼኩ ሲያውጅ የት ነበርክ። በውስጥህ ልብህ ደስ እያለው ስለነበር አይደለም እንዴ ሳትቃወም ዝም ብለህ ያለፍከው? አስመሳይ ሁላ !! አዎ አክራሪ እስላም አራጅ ነው። የሚያርደው ክርስቲያኑንም ሙስሊሙንም ነው። የሚያወድመው ሀገር ነው። መጀመሪያ ይሄን እመን።
•••
አሁን እኔንና ምህረተአብ ላይ ለመንበጫበጭ እየሞከሩ እንደሆነ እየሰማን ነው። እኔ ዘመዴም ሆንኩ ወንድሜ መምህር ምህረተአብ መገደላችን ይብቃ፣ መሞታችን ይብቃ፣ መሰደዳችን ይብቃ፣ መታረዳችን ይብቃ፣ እንሰባሰብ፣ እንደራጅ፣ እንመካከር፣ አራጅ ገዳዩን በጋራ እንመክት ማለታችን ከሆነ ቅር ያሰኛችሁ ቅራሪ ጠጡ። ወሬያም ሁላ። በግድ ሙቱ በግድ ታረዱ ብሎ ነገር አለ እንዴ? ለምንድነው አንዳቸውም የእስልምና ተቋማት በአሩሲ የደረሰውን ውድመት ያላወገዙት። የትኛውም አክራሪ እስላም እያስጨነቀው ያለው የ300 ሰው መታረድ ሳይሆን የአንዱ ጃዋር መታሰርና የሃጫሉ መገደል ብቻ ነው። እና ከእነዚህ ጋር ነው እንዴ ተነጋግሮ መግባባት የሚቻለው? አንዳንድ እወደድ ባይ የእኛ ቤት ጉዶችም ሚዛናዊ ለመምሰል በየ አክራሪ እስላሙ ሚድያ ላይ ወጥታችሁ ባትላላጡ መልካም ነው። አሽቋላጭ አትሁኑ !!
•••
በረከታቸው ይደርብንና የብፁዕነታቸው የአቡነ ጎርጎሬዎስን ምክርና ቃለምዕዳን በዕድሜ ዘመኔ ስተገብረው እኖራለሁ። በቅድስት ቤተ ክርስቲያኔና በቅድስት ሀገሬ ጉዳይ አንበሳው ሲያጓራ ውሎ ቢያድር ፍንክች አልልም። ሲያላዝንብኝ የሚውሉትን የሰይጣን ውሻዎችንም ለመውገር አልቆምም፡፡ ጥንቸሎቹንም በማባረር ጊዜዬን አላጠፋም።
•••
ከአጋንንት ማደሪያ ዝሆኖች ጋርም ስታገል አልውልም። ገበሬ የደከመበትን ማሳ አውዳሚ የዝንጀሮ መንጋን እያየሁ፣ በግና ፍየል ነጣቂ ተኩላና ቀበሮንም እየተመለከትኩ ግን አልታገስም። በቸልታም አላልፍም።
•••
እየገደልኩህም ቢሆን፣ እየዘረፍኩህም ቢሆን፣ እያረድኩህም ቢሆን፣ እያቃጠልኩህም ቢሆን፣ እያወደምኩህም ቢሆን፣ እያፈናቀልኩህም ቢሆን፣ ሜዳ ላይ በትኜህም፣ በረሃብና በጥም፣ በውርጭና በብርድ፣ በዝናብና በሃሩርም ቢሆን ብቀጣህ አትናገረኝ፣ አትቆጣኝ፣ አትገስጸኝ፣ ዝም በል፣ ጭጭ በል፣ ታገሰኝ፣ ቻለኝ የሚለኝን አስብቶ አራጅም አልታገስም። የሹም ዶሮ ነኝ፣ እሽሽ አትበለኝ ባዩንም አልሰማም።
•••
ትእግስት ፍራቻ አይደለም። አልታረድም፣ አልገደልም፣ አልዘረፍም፣ አልወድምም፣ አልፈናቀልም ስላልኩ የሚከፋው ካለ በአፍጢሙ ይተከል። እንጠረጦስ ይግባ። ሕገ መንግሥቱም፣ ሕገ ፈጣሪም ቢሆን ከዚህ በላይ ታገስ አይለኝም።
•••
አረጋዊ አባቴን ከፊቴ እንደ በግ አጋድመህ እያረድክ፣ አምጣ የወለደችኝን እናቴን ከፊቴ አጋድመህ እንደ ዶሮ እያረድክ፣ ጨቅላዋን እህቴን በገጀራ ከታትፈህ እያረድክ፣ ወንድሜን በሜንጫ ጨፍጭፈህ፣ በመጥረቢያ ፈላልጠህ በቃ ዝም በል ቻለው ስትለኝ አልሰማህም። የአራስ ሴት የደረሰች አሆዷን እየቀደድክ፣ ካህኑን አባቴን ከመቅደሱ አውጥተህ አርደህ እያቃጠልክ ዝም በል ብትለኝ አልሰማህም።
•••
የደረሰው ግፍና የዘር ውድመት ያልዘገነነህ የእኔ ችግሩን መናገር እንዴት አመመህ? አንት አስመሳይ። በቀጣይ ቪድዮዎችን አወጣለሁ። ፎቶዎችን እለቃለሁ። ክርስቲያን የተዋሕዶ ልጆች ተደራጅተው ከአራጆችና ከአውዳሚዎች ራሱንና ቤተሰቦቹን ይጠብቅ ዘንድ ማንቃቴን እቀጥላለሁ። ይሄን በማድረጌ የሚከፋው ካለ እደግመዋለሁ በአናቱ ይተከል። በአፍጢሙም ይደፋ። ሲኦል እንጦሮጦስም ይውረድ።
•••
አንድ ሙስሊም ጥቃት ሲደርስበት ሰማይና ምድር ካልተጣበቀ ሞተን እንገኛለን እያለ ሀገር ምድሩን ቀውጢ የሚያደርግ ግሪሳ ሁላ 300 ክርስቲያን ታረዶ እያየ እየተመለከተ፣ እየሰማ በልቡ ጮቤ እየረገጠ በአፉ እኔንና ምህረተአብ ላይ ለመንበጫበጭ ይጥራል። አልጀዚራ፣ ቢቢሲ፣ ሲኤንኤን ሞጣ ሞጣ ሲል ከርሞ ኦሮሚያ ኦርቶዶክሳውያን በጅምላ ሲታረዱ ጭጭ ይላል። እና እነሱ ዝም ሲሉ እኛ ስንናገር ለምን ተነገረ ብሎ እሪሪ ሲል ይታያል። ኢትዮጵያዊው ሙስሊም እንደ እኔው እየታረደ ነው። እየተሰደበ ነው። ጽንፈኛውን በጋራ ማውገዝ ሲገባ ለአራጅ ጥብቅና መቆሙ አያዋጣም። አያዛልቅምም።
• እኔ ግን ከቢቢሲም፣ ከአልጀዚራም፣ ከሲኤንኤንም እበልጣለሁ። ድብን አድርጌ እበልጣቸዋለሁ። አከተመ።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ሐምሌ 22/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።