>

እስልምናን እና ኦርቶዶክስን ያገለለው የአብይ ካብኔ...!!! (አህመዲን ሱሌይማን)

እስልምናን እና ኦርቶዶክስን ያገለለው የአብይ ካብኔ…!!!

አህመዲን ሱሌይማን
ተረጋገጠ/ Confirmed.
ባለ ሂጃቧ ጠይባ ሀሰን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ወንጌላዊት ናት
 
* ….ሲጀመር እኮ ፕሮቴስታንት ካልሆንክና ከፕሮቴስታንት ጋር ንክኪ ከሌለህ በኦሮሚያ ዉስጥ በኦዲፒ ዉስጥ ስልጣን አይሰጥህም 
እንዲህ እያልኩኝ ወሬ ላቀባብል እንጂ እኔማ ምን ስራ አለኝ? ይሄ ግን ወሬ ብቻ ሳይሆን የተረጋገጠ ሀቀኛ ወሬ ነዉ።
“… ደግሞ ጴንጤ ሆና ሳለ ሂጃብና ስሟን የሙጥኝ ብላ ያልለቀቀች ናት ተብሎ የሚነገርላት ወሮ ጠይባ ሀሰን  …´´ ብሎ የዛሬ አመት ከምናምን ዘመድኩን በቀለ ሲፅፍ፣ ያለ ተጨባጭ አንድ ነገር እንደማይፅፍ ባዉቀዉም ይሄንን ፅሁፉን አሉባልታ ነዉ ብዬ አላመንኩትም ነበር። ከዛ የሆነ የሻሸመኔ ጴንጤ ልጅ በዉስጥ መስመር እረ ናት ጠይባ ሀሰን በጣምን አጥብቆ ወንጌላዊት ናት አለኝ። እንዲያዉም አለኝ እ አልኩት የእኛ ቸርች አገልጋይ ናት አለኝ። አይሆንም አልኩት አስታዉሳለሁ እኔ ተላላዉ ሞኙ ምክኒያቱም ሂጃብ ታደርጋለች ስሟም ጠይባ ሀሰን ይባላል በሚል። እሱንማ ቸርች ስትነግረን ስሜንና ሂጃቤን እንደጠበኩኝ ጌታዬን የማገለግለዉ እስላም ሴቶችን ለመሳብ ነዉ። እስላም ሴቶች ጌታን ሲቀበሉ ሂጃብና ስማቸዉን መጣል እንደሌለባቸዉና የእምነታቸዉን የተኩላ ካባ ለብሰዉ በበጎች መሀል መስኪድ ድረስ መግባት እንደሚችሉ ለማሳየት ነዉ ብላናለች አለኝ። በሌላ ቀን ጠየኩት በዚህ ክለብ ዉስጥ ሂጃብ አድርገዉ የሚጫወቱ ሌሎች ይኖሩ ይሆን አልኩት። እንዴ  ምን ማለትህ ነዉ ሲጀመር እኮ ፕሮቴስታንት ካልሆንክና ከፕሮቴስታንት ጋር ንክኪ ከሌለህ በኦሮሚያ ዉስጥ በኦዲፒ ዉስጥ ስልጣን አይሰጥህም አለኝ። የኦሮሞ ህዝብ ከግማሽ በላዩ እስላም ነዉ እየተባለ ኦህዴድ ዉስጥ በባትሪ እንኳ አንድ እስላም ለማግኘት ይከብዳል አለኝ። እስላም ናቸዉ ያልካቸዉንም ስታያቸዉ እንደ ጠይባ የጌታ ልጅ ወንጌላዊት ትሆናለች ወይም በባሏ ወይም በሚስቱ በኩል ጴንጤ የሆነ/ች ነዉ የምታገኘዉ አለኝ። አሰብኩት አብይ አህመድ አሊ ጴንጤ፣ ለማ  መገርሳ ጴንጤ፣ ጠይባ ሀሰን ጴንጤ፣ ወርቅነህ ገበየሁ ጴንጤ፣ ሽመልስ አብዲሳ ጴንጤ፣ ታከለ ኡማ ጴንጤ፣ ህዝቅኤል ጋቢሳ ጴንጤ፣ አባዱላ ገመዳ ጴንጤ፣ ፀጋዬ አራርሳ ጴንጤ፣ ጃዋር መሀመድ በሚስቱ ጴንጤ፣ ኦቦ ሌንጮ ለታ ጴንጤ፣ አቶ ዳዉድ ኢብሴ ጴንጤ፣ አቶ በቀለ ገርባ ጴንጤ… እነዚህ እንግዲህ ከከፍተኛ የኦሮሞ ባለስልጣናት አንስቶ ተፅእኖ ፈጣሪ እስከሚባሉት ያሉት ኦሮሞዎች ናቸዉ (ለዚህ ነዉ ይላሉ ኦርቶዶክሶች ሲያለቅሱ ከመሀላቸዉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነበረዉን አንድ ለናቱን ተፅእኖ ፈጣሪዉን ሀጫሉን ሁለቱም ቡድኖች ቀርጥፈዉ በጋራ የበሉት)። አህመዲን ጀበልስ፣ ካሚሌ ሸምሱስ፣ ራያ አባ ሜንጫስ ሙስሊሞች አይደሉ እንዴ የሚለኝ አይጠፋም እኮ ይሄን ግዜ።
አህመዲን ጀበል በአብይ ቢያንስ በጅማ አገር በደደፎ ከተማ አስተዳደር ዉስጥ የእርሻ መሬት ይዞታ ማረጋገጫ ቢሮ ሀላፊ መሆኑን አላጣዉም ብሎ ተስፋ አድርጎ ነበር መሰለኝ አብይ እንደመጣ አብሮት ሲሞዳሞድ የነበረዉ። አንተ በናትህም ባባትህም እስላም ነህ ተብሎ ነዉ የተመለሰዉ። እንደዛ ይመስለኛል የእሱ ነገር።  ከዚያ ጊዜ አንስቶ ነዉ የጀዋር ወዳጅና የአብይ ጠላት የሆነዉ። ባጭሩ ኦሮሚያ ዉስጥ በገጠር ቀበሌ በምክትል ሊቀመንበርነትና በክልሉ ባሉ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ዉስጥ የኩነት አስፈፃሚ ስልጣን ካልሆነ በስተቀር ሙስሊሞች ስልጣን የሚሰጣቸዉ አይመስለኝም። (እህህ አለ ገብስ እያረረ)። ሳስበዉ ደግሞ ትክክል ሊሆኑም ይችላሉ አልኩኝ። ምክኒያቱም አርሲና ባሌ ምናቸዉ ይታመናል?
ስለ ጠይባ ይህን ሁሉ የነገረኝን የሻሼዉንም ልጅ ግን ላምነዉ አልፈለኩም ነበር። ምክኒያቱም እስኪ ተመልከቷት እቺ አሁን ምኗ ጴንጤ ይመስላል?
የሆነዉ ሆኖ ጠይባ ሀሰን የጌታ ልጅ መሆኗ ታዉቋል።
ሙፍሪያት ካሚልስ? እሷ እንኳ የኛዉ ናት ሙስሊም ናት እርግጠኛ ነኝ። ምክኒያቱም ኦዲፒና ኦሮሚያ ዉስጥ ስላልሆነች ሙስሊምነቷ ስልጣን ከመያዝ አያግዳትም። የቀድሞ የለገጣፎ ከንቲባ የነበረችዉና አሁን የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣኗ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒስ? ሂጃብ ታደርጋለች ሳያት በደንብ ግን። የአሁኑ የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅስ እንዴት ናት?  ሙስሊም ናት?
በትናንትናዉ ዕለት አራስ ቤት እንዳለች ከስልጣን የመነሳቷን ዜና የሰማችዉ ጠይባችን ከስልጣን መነሳቷ ሲነገራት እኔ ወንጌላዊቷ የጌታ ልጅ ጠይባ ሀሰን እዉነቱን እግዚአብሄር ያወጣልኛል እግዚአብሄር አለልኝ ብላ በመፎከር ወንጌላዊነቷን ምናልባትም ለመጀመሪያ ጊዜ ባደባባይ በኦሮምኛ እንደመሰከረች ታዉቋል። በትዊተር ያሉ ወዳጆቿም ይሄንኑ መልዕክቷን በትናንትናዉ ዕለት ተቀባብለዉላታል። ዘሀበሻም በትናንቱ የዜና ዘገባዉ ይህንኑ ብሏል።
Filed in: Amharic