>

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ሆነው ተሾሙ (ኢዜአ)

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

ኢዜ አ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ አካሂዷል።
ምክር ቤቱ ዛሬ ከሰዓት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሹሟል፡፡
የቀድሞዋ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ባለፉት ሁለት አመታት የከተማ አስተዳደሩን በምክትል ከንቲባነት የመሩት ኢንጂነር ታካለ ኡማን የሚተኩ ይሆናል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ዛሬ በሰጡት የከፍተኛ የመንግስት የስራ ሐላፊዎች ሹመት ኢንጂነር ታከለ ኡማ የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

https://www.facebook.com/100002483561507/posts/3423128021113283/

Filed in: Amharic