>

በኦሮሙማ አስተሳሰብ ኢትዮጵያን ማፍረስ እንጂ ማስተዳደር አይቻልም! (አቻምየለህ ታምሩ)

በኦሮሙማ አስተሳሰብ ኢትዮጵያን ማፍረስ እንጂ ማስተዳደር አይቻልም!

አቻምየለህ ታምሩ

* … ማፍረስና ከኦሮሞ ውጭ ያለውን መሰልቀጥንና ማጥፋትን እንደ ፖለቲካ ዓላማ የያዘውን ኦሮሙማን መመሪያው ያደረገው የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ ይቅርና  የትኛውም ብሔርተኛ ቢሆን አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር አይቻለውም!!!
 
አንዳንድ ኢትዮጵያን እንደዳለን የሚሉ የዋሆች ኢትዮጵያ ውስጥ የቆመው የኦሮሞ ብሔርተኞች የአፓርታይድ አገዛዝ ቁንጮ የሆነው ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ በዐይኑ እንቅልፍ ሳይዞር የሚያድር፤ ረፍት አጥቶ የሚውል ይመስላቸዋል። ይህ በእውነቱ ለራሳቸው ክብር ከሌላቸው፣ አጥልቀው ማሰብ ከማይችሉና ሥርዓት የተላበሰ አስተሳስብ ከሚጎድላቸው ሰነፍ ሰዎች የሚሰነዘር አስተያየት ነው። ዐቢይ አሕመድ እንደ ወያኔ የጡት ልጅነቱ  የርዕዮተ ዓለም  አባቶቹ የሆኑት ወያኔዎችና የመስፈን አባቶቹ የሆኑት ኦነጋውያን የጀመሩትን  ኢትዮጵያን በዘርና በጎሳ የመከፋፈል ፕሮጀት ከግብ ለማድረስና ኢትዮጵያን የምታህል ኦሮምያ  የሚሏትን የምናብ አገር ለመፍጠር  ያለ ረፍት የሚታትር  የኦሮሙማ አላማ  ጉዳይ አስፈጻሚ እንጂ የኢትዮጵያን አንድነት የሚጠብ ሥርዓት ለመፍጠር ደፋ ቀና የሚል የሁላችን መሪ አይደለም።
ለሁሉ ነገር እርሾ ያስፈልገዋል። አገር ለምራትና ተቋማትን ለመገንባትም እንደዚያው። ለልጅ መፈጠር የእናት ማሕጸንና የእንቁላል አስኳል እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለማንኛውም አካል ለመፈጠርና ለማደግ የተመቻቸ መነሻ ያስፈልገዋል። እነዚህ እርሾዎች ሳይመቻቹ አዲስ፣ ተተኪ ወይም የተሻለ ፍጥረት ሊመጣ አይችልም። አገሮች የሚፈጠሩበት፣ ቀድመው ከነበሩበት ሁኔታ ለማሻሻል ወይም በተሻለ ለመተካትም ቢሆን የሚሳካው ያንን የሚያመቻች አስኳል ነገር አልያም እርሾ ሲኖር ብቻ ነው።
አንድ መሪ የተለያዩ አውራጃዎች በጦር ወግቶ በቁጥጥሩ ውስጥ ስላደረገ ብቻ አገር አይመሰረትም፣ መምራትም አይቻለውም። ይህ ባገራችም፣ በውጪም አገሮችም የታየ ታሪክ ነው። የግሪኮችን፣ የሮማን፣ የእንግሊዝን፣ የአሜሪካንን፣ የሩሲያን፣ የጃፓንን ታሪክ ብንመለከት አገሮቹ የተፈጠሩት አስኳል የሚሆን ምቹ ሁኔታ ስለነበራቸው፤ ካልነበራቸው ከሌላ አገር እንደ እርሾ በመዋስ ነው። ድሮ የንጉሣዊ ቤተሰብ ያልነበራቸው አገሮች አገር ለመመስረት ሰማያዊ ደም ያለውን ከሌላ አገር አንዳንዴም ከባላንጣ አገር ጭምር ይዋሱ ነበር። የዛሬው የኖርዌይ ንጉሣዊ ቤተሰቦች የመጡት ከድሮ ገዢዎቻቸው ከዴንማርክና እንግሊዝ ነው። ካናዳ እንደ አገር የቆመችው ከእንግሊዝ አገር ዘውድ ተውሳ  ምልክቷ በማድረግ ነው።
ሕገ መንግሥቶችንና የሕግ ስርዓቶችን የወሰድን እንደሆነም ታሪኩ ተወራራሽ ናቸው። ሌሎች ባሕሎች የራሳቸውን ተጽዕኖ ወይም አስተዋጽዖ ቢያደርጉም የመጀመሪያው እርሾ ለምን ኖረ የሚል ጥያቄ ግን አያስነሳም። ያለፉት ሶስት ሺሕ ዓመታትና እስከ ዛሬም ድረስ ያለውን የኢትዮጵያን ታሪክ መለስ ብለን ካየነው የሚነግረን እውነት ይህንኑ ነው።
ዮዲት ባካሄደችው አብዮት የኔ ያለቻቸውን የጎሣ አባላት ወደ ስልጣን ቢያወጣም ወደ ስልጣን የመጡት ወገኖቿ  ግን አገር በመምራት ኢትዮጵያን ማስተዳደር አልቻሉም፤ ስለዚህ ራሳቸውን ስልጣኑን ለሚመራ ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን በመጨረሻ ያለጦርነት ዘውዱን አሳልፈው ሰጥተው ሄዱ። ግራኝ አሕመድ ጦሩን ይዞ የኢትዮጵያን ግዛት መቆጣጠር ቢችልም፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ መያዝ የሚችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ዝግጅት ስላልነበረው  ማጥፋት እንደ አማራጭ ወስዶ መጨረሻ ሳይሳካለት ቀርቷል።
ከግራኝ በኋላ በመላው ኢትዮጵያ እንደዋርካ የተስፋፉት አባገዳዎችም ከሶስት መቶ አመታት በላይ ወረራ በማካሄድ የኢትዮጵያን ለም አውራጃዎች በቁጥጥራቸው ስር ሲያደርጉ ከሌላው ጋር አብሮ ለመኖር፣  የሌላውን አክብሮ በእኩልነት የመኖር ምንም ፍላጎት አልነበራቸው። ይህንም የሆነ ገዳ የሚሉት ሥርዓታቸው ስለማይፈቅድ ነው።  ስለዚህ ያገኙትን ሥልጣኔና ነገድ ሁሉ ማጥፋት እንደአማራጭ ወሰዱ እንጂ ሁሉንም እንዳባቱ የሚኖርበትን አስተዳደር አልገነቡም። ባለፉት ሀያ ሰባት አመታት ስልጣን ላይ የነበሩት ወያኔዎችም በነገድ ተደራጅተው በመንግሥትነት ቢሰየሙም በሀያ ሰባት አመታት ውስጥ ያደረጉት ነገር ቢኖር በግራኝና በፋሽስት ጥሊያን ዘመን ያልተካሄደ መዝረፍና ማፈናቀል  ነው። ወያኔዎች ሀብታችንን ጨርሰው ኩላሊታችን ወደ መዝረፍ ገቡ እንጂ አገር ለመገንባትና ማስተዳደር ችሎታምም ፍላጎት ፍላጎት እንዲሁም የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ አልነበራቸውም።
ብሔርተኛነት እንደ እሳቤ የያዙ ሁሉ አላማው የሌላውን ነጥቆና ተቀራምቶ የራስ ብቻ የማድረግ የቅሚያ፣ የወረራና የመውረስ እንቅስቃሴ እንጂ ከእኩልነትና መብት ትግል ጋር የሚያገናኘው አንዳች ግብ የለውም። ኦሮሙማን ታጥቀው በመንግሥትነት የተሰየሙት እነ ዐቢይም አላማቸው እንደዚያው ነው። ለዚህም ነው የእነ ዐቢይ የአፓርታይድ አገዛዝ ፋሽስት ወያኔ 27 ዓመታት የፈጀበትን የቅድሚያ፣ ወረራና የመውረስ ክብረ ወሰን በአስር ወራት ውስጥ የሰበረው።
ሲጀመር እነ ዐቢይ መንግሥታዊ ያደረጉት የኦነጋውያን ኦሮሙማ ፖለቲካ ሳይሆን ዘረፋን፣ ወረራንና ቅርምትን የትግል ዓላማው የሚያደርግ የወንጀል ተግባር ነው። የኦሮሙማው ፈጣሪዎች ኦነጋውያን ራሳቸው ፖለቲከኞች ሳይሆኑ ዘረፋን፣ ወረራንና ቅርምትን የትግላቸው ዓላማ ያደረጉ፣ ሕጻናትና ሴቶችን ሲሰልቡና ሲዘርፉ የኖሩ፣ አቅመ ደካሞችን ሲያፈናቅሉ የኖሩ ተራ ማጅራት መቺዎች ናቸው። ኦነጋውያን ሁሉ የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ የሌላቸው ወሮበሎች ናቸው። ኦሮሙማን መርሁ ያደረገው ዐቢይ አሕመድና ድርጅቱ በመላው ኢትዮጵያ ላይ በመንግሥትነት ተሰይመው አገር ከዳር እስከ ዳር እየገዙ «አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት» የሚሉን የሁሉ መንግሥት ሆነው እንኳን የዘረፋ፣ የወረራና የቅርምት ፖለቲካቸው አባዜ አልለቃቸው ብሎ ነው።
የኦነጋውያን ኦሮሙማ ማዕከሉ ዘረፋ፣ ወረራና ቅሚያ ስለሆነ አዲስ አበባን ዳግማዊ ምኒልክ ከመምስረታቸው በፊት የነበሩት ኦሮሞዎች አይደሉም የሚለው የታሪክ እውነት ደንታ አይሰጣቸውም። በዚያ ላይ በአዲስ አበባ ዙሪያና በመላው አገሪቱ የሚገኘው ኦሮምኛ ተናጋሪ ሁሉ ኦሮሞ አለመሆኑን የራሳቸው ሰዎች እንኳ ያጠኑትን ታሪክ ለመቀበል ዝግጁ ያልሆኑ ሕመምተኞች ናቸው።
በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ኦሮሞዎቹ ወራሪዎቹ አባገዳዎቹና የነሱ ዘመዶች ብቻ ናቸው። ነባሩ ሕዝብ ኦሮምኛ እንዲናገር የተደረገው ተገዶ ኦሮምኛ ስለተናገረ ኦሮሞ ነው ማለት አይደለም። ኦሮምኛ የሚናገረው ሁሉ ኦሮምኛ እንዳልሆነ እውነተኞቹ ኦሮሞዎቹ ራሳቸው ምስክር ናቸው። በእውነተኞቹ ኦሮሞዎች ትውፊት ውስጥ «Salgan Borana, sagaltamman gabra» የሚል አባባል አለ። ይህ ወደ አማርኛ ሲተረጎም «ዘጠኙ ኦሮሞ ነው፤ ዘጠናው ገርበ ነው» ማለት ነው። ገርበ ኦሮሞ ሲስፋፋ ያስገበራቸውንና ባርያ ያደረጋቸውን ነገዶች የሚጠራበት ስያሜ ነው። በኦሮሞ በራሱ ትውፊት መሰረት ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ ከሚኖረው ኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝበ መካከል ትክክለኛው ኦሮሞ ከአስሩ አንዱ ብቻ ነው ማለት ነው። ከአስሩ ዘጠኙ ገርበ ወይም በአባገዳዎች በወረራ የተያዘና በኃይል ኦሮሞ የተደረገ ሕዝብ ነው።
ይህንን እውነት ከኦሮሞዎች ትውፊት በተጨማሪ ዛሬ በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። የሰላሌና አምቦ ሕዝብ የDNA ውጤት እንደሚያሳየው ዝምድናው ከምንጃርና ወይም ጅሩ ሕዝብ ጋር እንጂ ከቦረና (እወነተኛው ኦሮሞዎች) ጋር አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ፖል ሶሊሌት የተባለው የፈረንሳይ ጎብኝ እ.ኤ.አ. በ1884 ዓ.ም. ሸዋን ጎብኝቶ በጻፈው የጉዞ ማስታወሻው በሰላሌና ጃርሶ ውስጥ ኦሮሞ ገርበ ያደረጋቸው የአካባቢው ቀደምት ባለይዞታዎች አማሮች እንደሆኑ ጽፏል።
የአርሲ ሕዝብ ዝምድናው ከሐዲያ ጋር እንጂ ከቦረና ጋር አይደለም። ጀርመናዊው የታሪክ ምሁር በርካምበር እንዳጠናው ከአርሲ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛው ሐድያ ነው። የጅማ ሕዝብ ከየምና ከከፋ ሕዝብ እንጂ ከኦሮሞ ጋር ምንም ዝምድና የለውም። አባጅፋር ራሱ አረብ እንጂ ኦሮሞ አይደለም። ወለጋ እውነተኛ ኦሮሞዎች ከመቶ አስርም አይሞሉም። እውነተኛ ኦሮሞዎቹ ለባሪያ ፍንገላና ውሀና ሳር ፍለጋ መጥተው ሌላውን ገርበ አድርገው የቀሩት አባገዳዎችና ልጆቻቸው ብቻ ናቸው።
አንዳንዱ የዋህ ዐቢይ አሕመድን የሚደግፈው የነገድ ፖለቲካን ያጠፋልናል ብሎ ነው። እዚህ ሰዎች ግን በዐቢይ አሕመድ ውስጥ የሚንተከተከውን የኦሮሞ ብሔርኛነት መገንዘብ የማይችሉ ናቸው። ለዚህ ማሳያ የሚሆነን  ብዙ ርቀት መሄድ ሳያስፈልግ ባለፈው ዓመት  መጨረሻ ላይ  ከOBN ጋር ያደረገውን ቃለ-መጠይቅ ማየት በቂ ነው። ቃለ መጠይቁን ያደረገው የሓጫሉን ግድያ ተከትሎ በጥላቻ ያበዱት ኦነጋውያን “ዐቢይ ነፍጠኛ ነው” እያሉ ሲዘምቱበት ናዝሬት በሚገኘው የኦ.ቢ.ኤን. ስቱዲዮ በመገኘት  ነበር። በዚህ ቃለምልልሱ የኦሮሞነት ጥራቱን ለማብራራት የሄደበት ርቀት ገራሚ ነው። የአባቱን ንጹህ ኦሮሞነት ሲያብራራ “ከሰላምታ ያለፈ አማርኛ መናገር የማይችል” ሲል ነበር የገለጻቸው።
ይህ በግልጽ የሚያሳየው ዐቢይ እንኳን በነገድ ላይ የተዋቀረውን  የፖለቲካ ሥርዓት  ሊቀይር ይቅርና ሌሎች ጸረ ዘውድ ፓርቲዎች ወይም ግለሰቦች ዛሬ ኢትዮጵያ የተዋቀረችበትን የነገድ ርዕዮተ ዓለም ለመቀየር ቢሞክሩት ጦርነት የሚያውጅ ጉድ ነው። እነዚህ ዐቢይን ባልዋለበት እያዋሉ የነገድ ፖለቲካን ያጠፋልናል ብለው የሚያምኑት ሰዎች በቄሮዎች የተፈጁ ንጹሐንን ስለጉዳታቸው ከማዘንና አገዛዙ ጥበቃ ማድረግ ሲገባው ባለማድረጉ በተፈጸመው ፍትጅ  ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ያደረገው  ነገር ቢኖር አማራ ናችሁ ተብለው የተፈጁት ግፉዓንን ሬሳ ነገዳቸውን እየቀየረ ኦሮሞ በማድረግ  የተፈጸመባቸውን የዘር ማጥፋት ወንጀል  ለማድበስበስ ያላደረገው ጥረት የለም።
ባጭሩ እንኳን ማፍረስና ከኦሮሞ ውጭ ያለውን መሰልቀጥንና ማጥፋትን እንደ ፖለቲካ ዓላማ የያዘውን ኦሮሙማን መመሪያው ያደረገው የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ ይቅርና  የትኛውም ብሔርተኛ ቢሆን አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር አይቻለውም። በየትኛውም አለም ብሔርተኛ ሆኖ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር ሲያፈርስን እንጂ አገር ሲያረጋጋና ሲያስተዳድር ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም። በኢትዮጵያም ሆነ በአለም ታሪክ በብሔርተኛነት እሳቤ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር የማስተዳደር እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ ያለው አገዛዝ የለም። በዐቢይ አሕመድ የሚመራው ኦሮሙማም ዓላማው  የኦነግ ፕሮግራም እየተመራ የኦሮሙማ ኤምፓየር ቅዠት የሆነውን የተስፋ አገር መፍጠር እንጂ የሁላች የምትሆን ኢትዮጵያ የምትባልን አገር የማስተዳደር ፍላጎት፣ እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ የለውም።
ስለዚህ ከነገዳቸው ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት እንዲሁም የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ የሌላውን ዘረፋን፣ ወረራንና መውረስን ፖለቲካቸው ያደረጉ ያበዱ ብሔርተኞች መንግሥት ይሆኑናል ብሎ ማሰብ ውሻ ነከሰኝ ብሎ ለጅብ አቤት እንደማለት አይነት የዋህነት ነው። ብሔርተኛ ሁሉ አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር እንደማይችል ያለፉት አርባ አራት አመታት የኢትዮጵያ የቁልቁለት መንገድ ምስክር ነው። ልክ በቅሎ እንደማትወልድ ሁሉ የነገዱ ሳይሆን የኢትዮጵያ ስነ መንግሥት እሳቤ የሌለው፣ ከነገዱ ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት ያልያዘ ማናቸውም አይነት የሁሉም መንግሥት የመሆን ችሎታ የለውም። ያለው ችሎታ ቢኖር እንደ ወያኔና ኦነግ የሌላውን መዝረፍ፣ መቀማት፣ መቀራመትና መውረስ ብቻ ነው። ይኼው ነው።
Filed in: Amharic