>

አቶ ልደቱ አያሌው  ፍርድ ቤት ቀርበው  የ"እንገድልሃለን!" ማስፈራሪያ ከፖሊስ እንደተሰነዘረባቸው ተናገሩ...!!! (አቤል አለምነህ)

አቶ ልደቱ አያሌው  ፍርድ ቤት ቀርበው  የ”እንገድልሃለን!” ማስፈራሪያ ከፖሊስ እንደተሰነዘረባቸው ተናገሩ…!!!

አቤል አለምነህ

“ትናንት ምሽት ፖሊስ እኔ ከታሰርኩበት ክፍል ገብቶ በዚህ መዝገብ ፈትቸህ ነበር፤ አሁን ያቆየሁህ በዚህኛው ነው” በማለት ሁለት ሰነድ ይዞ መጣ። “መቼ ፈታህኝ ?” ስለው በዚህ መዝገብ ተፈተህ ነበር ያሰርኩህ በሌላ መዝገብ ነው። ይህን አምነህ ተቀብለህ ነገ ፍርድ ቤት ስትቀርብ ከዚህ በፊት ተፈትቼ ነበር አሁን የታሰርኩት በሌላ ክስ ነው ብለህ ቃል ስጥ ይህን ካላደረክ  እንገድልሃለን! “
በማለት አስፈራርተውኛል ሲል አቶ ልደቱ በእለቱ ለተሰየሙት ዳኛ አስረድቷል።
ፍርድ ቤቱም በምላሹ ፖሊስ ግለሰቡን በአስቸኳይ እንዲለቀው እና ሌላ ክስ ካለም በሌላ መጥሪያ ግለሰቡን ማሰር ይችላል በማለት መዝገቡን ዘግቷል።
ነገር ግን ፖሊስ አሁንም ልደቱን በማግስቱ 8:00 ቀጠሮ በመስጠት አስሮታል። በአጭሩ ግን የፖለቲካ መሀንዲሱን አቶ ልደቱ አያሌው ለመግደል እያሴረ ያለው ህገ ወጡ የአብይ አህመድ ቡድን መሆኑን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ያስፈልጋል።
ከዚሁ ሳንወጣ አቶ ሙሼ ሰሙ የልደቱን ህገወጥ እስር አስመልክተው ይህን ማለታቸው ይታወሳል:-
“አስተውል ወገን፣ ከልደቱ ጋር ልዩነት ኖረህም አልኖረህ ፍትሕ የተዋረደችው እና የተሰቀለችው ለልደቱ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም ነው!!!”
እወነት ነው! ፍርድ ቤት እየፈታው ፖሊስ (መንግሥት) አለቅም ያለበት ሂደት የፍትሕን መቀላት ያሳያል። ያስፈራል፣ ያሳፍራልም – በህግ አምላክ ፍቱት!
Filed in: Amharic