>
5:13 pm - Monday April 18, 0292

የሴራ ፖለቲካ ምጥቀት ላይ የደረሰዉ የኦህዴድ/ኦነግ ሀይልና የብአዴን የአሸርጋጅነት ሚና...!!! (ሸንቁጥ አየለ)

የሴራ ፖለቲካ ምጥቀት ላይ የደረሰዉ የኦህዴድ/ኦነግ ሀይልና የብአዴን የአሸርጋጅነት ሚና...!!!

ሸንቁጥ አየለ

ኦነግ ሽኔ የሚባለዉ የአቢይ ድርሰት:- “ቀዉስ /anarchy/ ትፈጥራለህ ቀዉሱን ለራስህ ጥቅም ታዉለዋለህ!” እንዲሉ የሴራ ፖለቲካ  አስጠኝዎች ኦህዴድ/ኦነግ ይሄን ህሳቤ በደንብ ተጠቅሞበታል::
——–
በአቢይ የሴራ ፖለቲካ ኦነግ ሽኔ  የሚል የሀሰት ትርክት የተፈጠረበት ሶስት አላማ አለዉ::
1ኛ. ባንክ እየዘረፉ በስፋት የኦሮሚያን ልዩ ሀይል ለማሰልጠን ነበር::ይሄ ግብ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል
2ኛ. በኦሮሚያ:በቤኒሻንጉል እና በደቡብ የአማራን ነገድ እየለዩ ለማረድ:ለማፈናቀል ብሎም ቀዉስ ለመፍጠር ነዉ::ይሄን ቀዉስም  እነ አቢይ እራሳቸዉ ባዘጋጁት የኦሮሚያ ልዩ ሀይል/በእነሱ አጠራር ኦነግ ሸኔ/ በኩል ካከናወኑ ብኋላ መልሰዉ ህዉሃት እና ኦነግ ሸኔ ናቸዉ ይሄን የፈጸሙት እያሉ ለመክሰስ እንዲያመቻቸዉ የፈጠሩት የሴራ ፖለቲካ ነዉ::
በዚህም የሴራ ፖለቲካ ብዙ አትርፈዉበታል::በዋናነትም አማራዉን ለማፈናቀል/ለማረድ:ተዋህዶን ለመቀጥቀጥ እና ኢትዮጵያዊነትን ለማዋረድ እንዲመቻቸዉ አድርገዋል::በዚህም ቀዉስ ይፈጥራሉ::ቀውሱንም ለራሳቸዉ ፕሮፖጋንዳ ይጠቀሙበታል::
አንዱን ምሳሌ እንኳን ብንወስድ የሻሸመኔን ከተማ ሙሉ ለሙሉ ካቃጠሉና ካወደሙ ብኋላ እንዲሁም በመላዉ ኦሮሚያ በሀያ ሽህ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ከፈጸሙ ብኋላ ጠቅላይ ሚኒስቲሩ ወጥቶ እንኳን ይሄን ጉዳይ በግልጽ ሳያወግዝ አድበስብሶ አልፎታል::
የሻሸመኔ ከንቲባ የነበረዉም የዚህን ሚስጢር ፍርድ ቤት ቀርቦ አጋልጧል:: “የኦሮሚያ መሪ አርፈህ ገብተህ እቤትህ ተኛ” ብሎኛል ሲልም ቃሉን ሰጥቷል::
ይሄ ሰዉዬ የተናገረዉ ነገር እዉነት መሆኑን ለማረጋገጥ የፈለገ ሰዉም የሽመልስ አብዲሳን ንግግር ማድመጥ ነዉ::ሽመልስ አብዲሳ በሴራ ፖለቲካ ትንታኔዉ በገሃድ እንደ አስረዳዉ ቀዉሱን ሁሉ የሚፈጥረዉ እራሱ ኦህዴድ/ኦነግ መሆኑን አስረድቷል::ይሄን የሚያደርጉትም ታላቋን ኦሮሚያን ለመፍጠር እንደሆነ መስክሯል::
3ኛ.የአማራ ተቃዋሚ ነኝ/የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ነኝ የሚለዉን ሀይል ሰብስቦ የአቢይ ደጋፊ ለማድረግ ሁሉንም ነገር በኦነግ ሸኔ/ህዉሃት ላይ በማላከክ አስፈላጊዉ ስራ ሁሉ ተሰርቷል::በዚህም የሌለዉን ምናባዊ ኦነግ ሸኔ የሚል ሀይል በአዕምሯቸዉ የተሳለባቸዉ የተቃዋሚ ሀይሎች ሁሉ ተሰብስበዉ ወደ አቢይ ጉያ እንዲገቡ ሆኗል::
ልክ ኦሮ-አማራ በሚል ፕሮፖጋንዳ የአማራ ተቃዋሚ ነኝ ባዩን ሁሉ ከሶስት አመት በትፊት ጢባ ጢባ እንደተጫወቱበት ሁሉ አሁን ደግሞ የሴራ ፖለቲካዉን ከፍታ አርቀዉ ሰቅለዉታል:: በዚህም ከዉጭ ሀገር/እስከ ሀገር ቤት ያለዉን የአማራ/የኢትዮጵያ አንድነት ሀይል አራማጅ ነኝ ባይ ተቃዋሚ ሁሉ አቢይ እግር ስር አስደፍተዉታል::
ርስትህ ሊመለስህ ነዉ:-
———
 የአማራን ወጣት ማጥመጃ የተንኮል ፖለቲካ ሆኖ በኦህዴድ ከሚዘወረዉ ብአዴን መንደር የተነፋ ፕሮፖጋንዳ ነበር::የአማራ ወጣት እና አርሶ አደርም ነገሩን አምኖ ወደ ግንባር በወኔ ዘምቶ በወያኔ አለ አግባብ የአማራ ህዝብ የዘር መጥፊያ የሆኑ ቦታዎችን ማስለቀቅ ጀመረ::ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስቴር ተብዬዉ እንዲሁም የኦህዴድ/ኦነግ መከላከያ ሚኒስቴር ሀላፊ እና የአቢይ ተሿሚዉ የትግራይ ብልጽግና ሀላፊዉ የምን ርስት ነዉ ?ዘመቻዉ ህገ መንግስቱን ማስከበር ነዉ ሲሉ ለመሳለቅ ሁለት ቀን አልታገሱም::ይሄም የሚጠበቅ ነበር::
ይሄም የተንኮል ፖለቲካ ለጊዜዉ አቢይን አትርፎለታል::አማራዉን በሀሰት ቀስቅሶ እፊት ለማሰለፍ ችሏል::ሆኖም መዘዙ ቀላል አይሆንም::
በአማራ ደም ቀዉስ መፍጠሩ ቀጥሏል:-
—————–
በደቡብ በአማሮ ወረዳ:በወለጋ:በመተከል:በጉራፋርዳ:በልዩ ልዩ የኦሮሚያ ወረዳዎች እና በልዩ ልዩ ስፍራዎች አሁንም የአቢይ ኦነግ ሸኔ ሀይል በአማራ ደም ቁዉስ መፍጠሩን ቀጥሏል::አማራዉ እየተፈናቀል እየታረደ: ስቃዩን እየበላ ነዉ::አሁንም የሚሳበበዉ ግን ኦነግ ሸኔ/ህዉሃት በሚባሉ ሀይሎች ነዉ::
ስለ አክራሪ የኦሮሚ ፖለቲከኞች የስነ ልቦና አወቃቀር አንዳችም እዉቀት የሌላቸዉ የአማራ/ኢትዮጵያ ፖለቲካ ተቃዋሚ ነን ባዮች እዉነትም ኦነግ ሸኔ እና ኦህዴድ/ኦነግ የተለያዩ ናቸዉ ብለዉ አሁንም ከበሮ መደለቃቸዉን ቀጥለዋል::
በቀዉስ ፖለቲካ : በተንኮል ፖለቲካ: በደባ ፖለቲካ የአማራ ህዝብ ደም እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ የአማራ ፖለቲከኛ ነኝ ባይ: የአማራ ልሂቅ ነኝ ባይ: የኢትዮጵያ አንድነትን እወዳለሁ ባይ ሁሉ የኦህዴድ/ኦነግን መርዛማ የተንኮል ፖለቲካ አተላ ተሸክሞ ሲሰበሰብ እና ሲመክር ይዉላል::ከሀገር ዉስጥ እስከ ዉጭ የኦህዴድ/ኦነግ የፕሮፖጋንዳ ማሽን ሆኖ ተሰልፏል::አማራዉ እያለቀ ባልሰማሁም እያለፈ አማራዉን እያስፈጀ ያለዉን የኦህዴድ/ኦነግ ሰራዊት የኢትዮጵያ ሰራዊት ነዉ የሚል ፉከራ ላይ ይገኛል::
ህዉሃት በራሱ ተንኮል ተጠልፎ የጠፋ ድርጅት ነዉ::ህዉሃት ቤተ መንግስቱን ሙሉ ለሙሉ ለአቢይ አስረክቦ ለቆ ወደ መቀሌ የመሸገ ጊዜ በአክራሪ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እጁ ተጠምዞ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ተወግዷል::ህዉሃት የተመኘዉን እግዚአብሄር ሰጥቶታል::ህዉሃት የአማራ ሀይል ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዳይመጣ በሚለዉ ቀመሩ: መከላከያዉን:ደህንነቱን:የፖሊስ ሀይሉ እና የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱን ሙሉ ለሙሉ ለኦህዴድ/ኦነግ ሀይሎች አሳልፎ በመስጠት በራሱ ላይ ተኩሶ እራሱን የገደለ ድርጅት ነዉ::የኦሮሞ አክራሪ ሀይሎችም ህዉሃት የናቃቸዉን ያህል ታላቁን የሴራ ፖለቲካ ህዉሃትን ግተዉ ከቤተ መንግስት አባረዉታል::
በተቃራኒዉ ግን ሀያ ሰባት አመታት የህዉሃትን ሀይል የታገለዉ የአማራ/የአንድነት ተቃዋሚ ሀይል በብአዴን ክህደት ተፈጽሞበት ድሉ ከጁ ተነጥቋል:: ይሄም  በመጨረሻዉ ሰዓት በአማራ ተጋድሎ:በፋኖ እና በእነ ጎቤ ተጋድሎ ህዉሃትን አከርካሪዉን መትተዉ ብአዴን ስልጣኑን እንዲይዝ ሁኔታዎችን ቢያመቻቹለትም ብአዴን  የተገኘዉን ድል ሙሉ ለሙሉ ለኦህዴድ/ኦነግ አሳልፎ ሰጥቶ የባርነት ሚናዉን ስለመረጠ ነበር::
ብአዴን በዚህ የግርድና ስራዉ በመቀጠል አሁን የኦህዴድ/ኦነግ ሴራ ፖለቲካ አስፈጻሚ ሆኗል:: የሴራ ፖለቲካ ምጥቀት ላይ የደረሰዉ የኦህዴድ/ኦነግ ሀይል የአማራ/የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ነኝ ባዩን ሁሉ በሚያስደንስበት ጊዜ ግንባር ቀደም ደናሽ ሆኖ የቀጠለዉም ብአዴን ነዉ::የብአዴንን ዳንስ ልዩ የሚያደርገዉ አሁን በተፈጠረዉ ሁኔታ ብቻ ደናሽ መሆኑ ሳይሆን ገና ለግርድና ትከሻዉን በደንብ እያመቻቸ መሆኑ ነዉ::
ኦህዴድ/ኦነግ በሶስት አመት ዉስጥ ብቻ ህዉሃት በሃያ ሰባት አመታት ጊዜ ዉስጥ ያልፈጸመዉን ወንጀል በአማራ ህዝብ ላይ በተዋህዶ ላይ እና በኢትዮጵያዊነት ላይ ፈጽሟል::በቁጥርም በስፋትም በጥልቀትም ኦህዴድ/ኦነግ የፈጸመዉ ወንጀል ወደርም የለዉም:: የመጭዉ ጊዜ ደግሞ ከዚህ የከፋ ነዉ::
በርግጥ ኦህዴድ/ኦነግ  በራሱ የሴራ ፖለቲካ ተጠልፎ ጠፊ ነዉ::ኦህዴድ/ኦነግን ጠልፈዉ የሚጥሉት የራሱ  የሴራ ጉንጎኖችም  የሚከተሉት አራት ኩነቶች ናቸዉ:-
1ኛ. ወላቃይት እና ራያን ርስትህ አይደለም ብሎ በአማራ ሀይል ላይ ጦር ይመዛል::ያን ጊዜም አንዱ የጦርነት መጎንጎኛ እና የመጥፊያዉ መነሻ እነዚህ አካባቢዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በአማራዉ ወጣት ልብ ዉስጥ አመጽ ይጫርለታል
2ኛ. ከመላ ሀገሪቱ የአማራን ህዝብ በኦነግ ሸኔ/በህዉሃት/በቤኒሻንጉል ልዩ ሀይል/እና በሌሎችም ሀይሎች በማሳበብ ማፈናቀሉን ይቀጥላል::በመላ ሀገሪቱም አማራዉን የማፈናቀል እና የማጽዳት ዘመቻዉን የሴራ ፖለቲካዉ ምጥቀት ማጠንጠኛ አድርጎ ስለሚያስበዉ ይሄን ወንጀል ይቀጥላል::የአማራ ህዝብም ነገሩ እየጠራ ሲመጣ ጸረ ኦህዴድ/ኦነግ እንቅስቃሴዉን በአዲስ መልክ በአዳዲስ ድርጅቶች ይጀምራል::
3ኛ.ተዋህዶን ሳያጠፋ እንቅልፍ የማይወስደዉ የኦነግ/ኦህዴድ ሀይል ተዋህዶ ላይ የሚሰራዉን ወንጀል አጠናክሮ ይቀጥላል::እናም ለመስዋዕትነት እንቢ ብሎ የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ከቃልቻ ክብር ጋር እያምታታ የሚገኘዉ የክርስትና መሪ ነኝ ባይ ሁሉ በጸረ ክርስቶስ ሀይል እየጠፋ ሲሄድ አዳዲስ የክርስቶስ ወታደሮች ወደፊት ይመጣሉ
4ኛ-የኢትዮጵያዊነት አንድነት ሀይሉን የኦነግ/ኦህዴድ ሀይል ፈጽሞ ሳይደመሥስ አይተኛም::የኦህዴድ/ኦነግ ትልቁ ህልም ትልቋ ኦሮሚያ ነዉና ትልቋን ኢትዮጵያ በልዩ ልዩ መልክ አኮስምኖ እና አዉድሞ ማጥፊያ ልዩ ልዩ ስልቶችን መተግበሩን ይቀጥላል:: እንደ እስክንድር ነጋ አይነት ጎልተዉ የሚወጡ የአንድነት ሀይሎችን ወይም እዉነተኛ የአንድነት ጉልበት ይኖረዋል የሚባሉትን ሁሉ ይበላቸዋል::በኢሳያስ አፈወርቂ መመሪያ መሰረት አቢይን እየደገፉ ያሉ እንደ ብርሃኑ ነጋ አይነት አስመሳይ የአንድነት ሀይሎችም ምናልባት ስልጣን አቅምሱን እንዳይሉ በደንብ ይቆነጠጣሉ::
የኦህዴድ/ኦነግ ሀይል የኢትዮጵያ አንድነት ሀይልን የሚያጠፋዉ ደረጃ በደረጃ ነዉ::መጀመሪያ አማራን ማጥፋት:ቀጥሎ ደቡብን መበታትን እና መምታት::የሚዋጠዉን መዋጥ::ምናልባትም አንዳንድ ነገዶች በኢትዮጵያዊነት ላይ አቋም እንወስዳለን ካሉ እነሱንም የማጥፋት  የወንጀል እርምጃዎችን ሁሉ ይወስዳል::ይሄ ሁሉ ግፍ እና ወንጀልም የፓን ኢትዮጵያ እንቅስቃሴዎችን ይፈጥራል::
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት አራት የሴራ ጎንጎኖች በራሱ በኦነግ/ኦህዴድ የሚፈጠሩ ሆነዉ በምላሻቸዉ ግን እራሱን የሚበሉ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ይዞ ይወለዳል::ህዉሃት በቅንነት ኢትዮጵያን ከመምራት ይልቅ በራሱ የሴራ: የክፋት እና የተንኮል ፖለቲካ ተጠልፎ እንደ ወደቀዉ ሁሉ ኦነግ/ኦህዴድም እንዲሁ ይጠፋል::
ኢትዮጵያ ግን በዚህ ሁሉ ከፋት ሴራ እና ተንኮል ዉስጥ በእግዚአብሄር ፈቃድ ህልዉናዋ ይቀጥላል::በህዝቧል ላይ ግን በኦህዴድ/ኦነግ የሴራ ፖለቲካ ብዙ መከራ ይወርዳል::እግዚአብሄር መከራዉን ያሳጥረዉ ዘንድ የሚጸልዩ እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያን ግን አሁንም ከኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ነገዶች መሃል ሞልተዋል::
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ
Filed in: Amharic