>

የሱዳን ጦር  የኢትዮጵያን  ድንበር ጥሶ  በመግባት  ጥቃት ፈጸመ...!!! ( አሻራ ሚዲያ)

የሱዳን ጦር  የኢትዮጵያን  ድንበር ጥሶ  በመግባት  ጥቃት ፈጸመ…!!!
      አሻራ ሚዲያ.       ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ
ህዳር፡-29/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር

የሱዳን ጦር  የኢትዮጵያን  ድንበር ጥሶ  በመግባት በአብርሀጅራ ወረዳ በስናር የእርሻ ልማት ካምፕ ውስጥ ጥቃት መፈጸሙ ተገልጻል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎችና ተጎጅዎች እንደገለጹት የተለያዩ ንብረቶች እንደወደሙ ገልጸው በግምት ሁለት ሚሊዮን ብር የሚሆን ንብረት ወድሟል ብለዋል፡፡
የተለያዩ የእርሻ መሳሪያዎች ትራክተር፣ጀኔኔተር፣የሰብል መርጫ እና ሌሎች የሰብል ምርቶች እንደተቃጠሉባቸውና እንደተዘረፉባቸውም ገልጸዋል፡፡
በአሁን ሰዓት የሱዳን የጦር ሀይል  በአካባቢያችን የደፈጣ ውጊያ  እያደረገብን ይገኛል እኛም ስንለፋበት እና ስንደክምበት የቆየነውን ሰብል ትተን እየሸሸን እንገኛለን ብለዋል የመረጃ ምንጫችን፡፡
የከፋ ችግር ከመድረሱ በፊት መንግስት አስፈላጊውን ጥበቃና እርምጃ ይውሰድልን ሲሉም ተናግረዋል፡፡
እንደምንጫችን ገለጻ የሰው ህይወት አልመጥፋቱንና አንድ ወጣት ግን የሱዳን ጦር በከፈተው ተኩስ መቁሰሉን ለአሻራ ሚዲያ ተናገረዋል፡፡
በመጨረሻ ለሚመለከተው የመንግስት አካላት  ብናመለክትም ምንም ሊሰማን የሚችል አካል አላገኘንም ብለዋል ምንጫችን፡፡ ስለሆነም በአሁኑ ሰዓት ችግር ውስጥ ስለምንገኝ መንግስት በአስቸካይ ይድረስልን ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ምልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ከተወሰኑት የሚከተለውን  አደረግሁ ባቸው። ግን ዪትዩቡ ሪዳይሬክት አያረግም
Filed in: Amharic