>

የወርቅ እንቁላል ጣይ ዶሮዎቻችንን ባናሳቅቃቸውስ??! (ዘመድኩን በቀለ)

የወርቅ እንቁላል ጣይ ዶሮዎቻችንን ባናሳቅቃቸውስ??!

ዘመድኩን በቀለ

~ እንደ እነዚህ ሦስት የሸዋ ኦሮሞ የቱለማ ልጆች የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያውያን ባለውለታ የሆኑ ግለሰቦችን በቀላሉ አይገኙም። እንደነዚህ ዓይነቱ የወርቅ እንቁላል ጣዮች በታሪክ አጋጣሚ የሚገኙት ከስንት ጊዜ አንደዜ ነውና ብንንከባከባቸው፣ ብንጠነቀቅላቸው ባይ ነኝ። እነሱ ባይኖሩ ኖሮ ብዙ ነገሮች እንደተሰወሩ ይቀሩ እንደነበር ማሰብ አለብን። እናም ባናስደነብራቸው መልካም ነው። ትንሽ ጠቅ፣ ወጋ ወጋ፣ ኮርኮር በማድረግ እንዲተነፍሱ ማድረግ፣ ከዚያም እየኮረኮሩ የሆዳቸውን ምስጢር እንዲዘረግፉ ማድረግ እንጂ ማስደንበሩ የምስጢር ሰንዱቁን ማስቆለፍ፣ ከሥራ ውጪ አድርጎ ሁሉን ነገር ዝግ ማድረግ ይመጣልና ባንጫናቸው መልካም ነው ባይ ነኝ።
• ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ( የእኔ አንደኛ )  
• ኦቦ ታዬ ደንደአ
• ኦቦ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ
… በተለይ ሽሜ የእኔ ፎልፏላ፣ የእኔ ቦጅቧጃ ነው። በሆዱ ምንም ማስቀመጥ የማይችል። በምስጢር የነገርከውን በገሃድ የሚዘራልህ። በጨለማ የተወራውን በብርሃን የሚገልጥልህ። ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን ገልጦ የሚያሳይህ፣ ምስኪን… ቦጅቧጃ… ገራገር… ነገር መቋጠርም ሆነ ሸር መሸርሸር የማይሆንለት። የጠቅላዩ አፍ። እንደልቡ። ባለውለታችንም ነው ባይ ነኝ።
… ሽሜ ማለት የብልጽግናን የልሳን ጸሎት የተረጎመልን። አቅጣጫውንም ያሳያን። በቢልየን ብር የማይገኝን ምስጢር በነፃ፣ በብላሽም የሰጠን። ኮንቪንስም ኮንፊዩዝድም አድርጎ ነገር ግን የሃገሪቱን የፖለቲካ አቅጣጫ የቀየረልን። የቁማርን ጥቅም የገለጠልን። ብአዴንን ያነቃ። ከጥልቅ እንቅልፉም የቀሰቀሰ። ዐማራን አንድ ያደረገ። ኢትዮጵያውያንን ያነቃ፣ ያበቃም ነው ሽሜ ማለት። ከሽሜ በላይ ለኢትዮጵያ ውለታ የዋለ እኔ አላውቅም።
… ጀባዱ ሽሜ ያ ሌንጨኮ። አማስ ዋኤ ዐቢዪ ወጂን መሪአተን አደባባዪቲ በዪቲ ንገረን። ዝም አትበል ሽሜ። ዝም አትበል። ዝም ስትል ሁሉ ነገር ይዘጋጋል። ጨለማ ነው ነው የሚሆነው። አንተ ትክክለኛው የሸዋ ቱለማ ኦሮማይዝድ የተደረግክ ኢትዮጵያዊ ነህ። ንገረን ሽሜ። አቢቹ በአደባባይ መናገር የሚያፍረውንና የሚፈራውን አንተ የእኔ ቦጅባጃ ንገረን። ኢንሶዳቲን ያ ሌንጨ ኬኛ። ኑርልን አቦ።
… ኦቦ ታዬንም ብዙ አንወርፈው። ተወደደም ተጠላም ከራሴ ከሚላቸው ወነጎች ጋርም ብቻውን የተተጋተገ የቱለማ ኦሮሞ ነው። ጃዋርንና ካምፑን የተተጋተገም ጀግና ነው። ችግሩ ሲያልቅ አያምር ሆኖ ከድል በኋላ ሸሸ፣ አፈገፈገ እንጂ በታዬ ላይ ብዙ አፍ ለመክፈት አልደፍርም። ታዬ ችግሩ በአንድ ጊዜ ኦነግም ኦፒዲኦም መሆን የሚያምረው መሆኑ ነው።
… ኦቦ ታዬ የአጎቱን ልጅ ሁለት ሚልየን ብር ይዘህ ወደ ቤት ጥፋ ብሎ ሰጥቶ፣ የጎረቤት ልጅ የፓርቲ ብር ሰረቀኝ ብሎ ወከባ የሚፈጥር የድሮ አራዳ ቢጤ ነው እያሉ ደዘ ዎች የሚያሙት ሰው ነው። በጫካ ላለው ኦነግ 23 ባንክ እንዲዘርፍ አድርጎ በከተማ ላለው ኦነግ ሁለት ሚልየን የፓርቲ ብር በሻንጣ ይዞ የሚያከፋፍል የተራበ ካድሬ ነም እያሉ ያሙታል። ታዬ ብዙ የተጎዳ ሰው ነው። ለዓመታት ቂሊንጦ የከረመ ነው። እናም ብዙም አትቀየሙት ደግሞም ፊትም አትስጡት። ኦቦ ታዬን እንደ ጋዜጠኛ ቤቲ አታሽቆጥቁጡት። እንደ ኦቦ ጃዌ ጀዋር ኢግኖር ግጩት።
… ዐማሮች ታዬን አትመልሱለት። ልክ እንደጃዋር ኢግኖር ግጩት። አዲስ ገቢ ካድሬ ስለሆነ ብዙም ቦታ አትስጡት። እዚያው የፓርቲ ስብሰባ ላይ ብአዴኖች በሚገባው ቋንቋ ያነጋግሩት። ግን እሱም ባለ ውለታችን መሆኑን አትርሱት። ይናገር። ሆድ ያባውን ብቅል አይደል የሚያወጣው። ይትፋው ዝም በሉት።  አታጀግኑት። እኔ የምመክረው ታዬንም አዲሱንም ችላ ብለን ሽሜን ብቻ ነው ማድነቅ። ሽሜን ብቻ ነው መንከባከብ። ሽሜን ነው ተናግሮ እንዲናገር ማስደረግ። ሌላውን እርሱት። ግን ኦቦ ታዬም ይመሰገናል።
… ኦቦ አዲሱ አረጋንም አትጋተቱት። ኦቦ አዲሱ መስሎ አዳሪ ነው። ዘመኑን መስሎ አዳሪ ነው። የሸዋ ኦሮሞም ስለሆነ በአሩሲና በወለጋ ኦሮሞዎች እንዳይዋጥ ይፈራል። ይደነግጣል። በዘመነ ህወሓት የህወሓት አሸርጋጅ፣ መኝታ አንጣፊ የነበረ ምስኪን ነው። የዳንኤል ብርሃኔ አድናቂ፣ የአሉላ ሰሎሞን ናፋቂ የነበረ ምስኪን ሰው ነው። የጃዋር ዘመን ሲመጣ ከጃዋር በላይ ጃዋርን ለመውደድ የሚላላጥ። እሁድ የተስፋዬ ገብረአብ ነቃፊ፣ ሰኞ በማግስቱ የተስፋዬ ገብረ አብ አድናቂ። ግራ የገባው ወንድማችን ነው። በዚህ ላይ ነፍጠኛ ነው እያሉ የዚያው ሰፈር ልጆች ያንገበግቡታል። እናም ኦጎኖቼ ብዙ አታስከፉት።
… ሦስቱም ግን ካወቅንበት ፈጣሪ የሰጠንና የእነሱን የጓዳ ምስጢሮች ወደ አደባባይ እያመጡ ያለ ድካም የብልጽግናን፣ የበዻዺናን ዕቅድና መዳረሻ ግብ የሚጠቁሙ ኮምፓሶቻችን ናቸው። እናም ብዙም አታዋክቧቸው።
… እኔ ግን በተለየ ሁኔታ የሽሜ አድናቂ ነኝ። ኑርልኝ የእኔ ፎልፏላ፣ የእኔ ቦጅቧጃ። አቦ ከግምገማ ሰይፍ ይሰውርህ። ሽሜኮ ቶሎ ቶሎ ተናገር !! ሂ ኢ …
Filed in: Amharic