>

የወቅቱ የወልቃይት ጉዳይ...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የወቅቱ የወልቃይት ጉዳይ…!!!

አቻምየለህ ታምሩ

የትግራይ ብሔርተኞች በዋና ሥራ አስፈጻሚው በሙሉ ነጋ፣ በአረና፣ በትዴት፤ በትግራይ ብልጽግናና ፈንቅል በሚባለው ስብስብ ዙሪያ የተኮለኮሉት ሁሉ የስልጣን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በአማራ ጥላቻቸው ሕወሓትን የሚያስንቁ ስለመሆናቸው ጥርጥር የለውም። በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ800 በላይ ንጹሐን የአማራ ተወላጆች በትግራይ ፖሊስ፣ በትግራይ ልዩ ኃይል፣ በትግራይ ሚሊሻና ወያኔ ሳምሪ ብሎ ባደራጃቸው ነፍሰ ገዳዮች የተረሸኑበትን የደም መሬት እንደ ሕወሓት ቅኝ ሊይዙና የዘር ፍጅት ፈጽሞ የሄደውን ሕወሓትን ተክተው በመንግሥትነት በመሰየም ሊገዙ ማሰፍሰፍ የጀመሩት የግፉዓኑ አስከሬን ተቆራርጦ ከየተጣለበት በፍለጋ ተገኝቶ አፈር እንዲለብስ ሳይደረግ ነው።
ምን ይሄ ብቻ! የትግራይ ፖሊስ፣ የትግራይ ልዩ ኃይል፣ የትግራይ ሚሊሻና ወያኔ ሳምሪ ብሎ ያደራጃቸው ነፍሰ ገዳዮች በአማራ ተወላጆች ላይ የፈጸሙት የዘር ማጥፋት በዓለም እንዳይታወቅ እንቅስቃሴ የጀመሩትና በተካኑበት ጩኸቴን ቀሙኝ የፖለቲካ ብልጠታቸው ውንጀላ ውስጥ የገቡት ማይካድራ አርዶ ወደ ሱዳን የሸሸውን የትግራይ ፖሊስ፣ የትግራይ ልዩ ኃይል፣ የትግራይ ሚሊሻና የሳምሪ ቡድን በትግሬነቱ ምክንያት እንዲፈናቀል የተደረገና በጦርነቱ የተነሳ በድንገት ስደተኛ የሆነ አድርገው ከጣራው በላይ በማስጮህ ነበር።
ለመሆኑ የትግራይ ብሔርተኞች ሁሉ ወልቃይትን ይገባናል የሚሉት የትግራይ ክፍል ሆኖ የማያውቀው ወልቃይት ሕገ መንግሥት በሚባለው መሰረት የሕዝብ ፍቃድ ተጠይቆ ወደ ትግራይ ስለተካለለ ነውን? በፍጹም! ወያኔ ወልቃይትን በትግራይ ስር annex ያደረገው የትግራይ ሪፑብሊክን ለመመስረት ጫካ በገባ ባመቱ ባዘጋጀው የ1968ቱ የመጀመሪያ የሕወሓት ማኒፌስቶው እንጂ በሕዝብ ፍቃድ አልያም ሕገ መንግሥት በሚሉት መሰረት አይደለም። ከታች የተያያዘውን የሕወሓት ማኒፌስቶ ይመለከቷል።
ልብ በሉ! ሕገ መንግሥት የሚባለው የታወጀው በ1987 ዓ.ም. ነው። ሕገ መንግሥት ተብዮው በ1987 ዓ.ም. የታወጀው ወያኔ ወልቃይትን በትግራይ ስር annex ባደረገ በ20 ዓመቱ ነው። ስለዚህ የትግራይ ብሔርተኞች የሕዝብ ፍቃድ ጠይቀው ወይም ሕገ መንግሥት በሚሉት መሰረት አይደለምና ወልቃይትን ወደ ትግራይ annex ያደረጉት ወልቃይትን በሚመለከት “የሕዝብ ፍቃድ ይጠየቅ፣ በሕገ መንግሥቱ መሰረት በተቋቋመው የወሰንና ማንነት ኮሚሽን መፍትሔ ይሰጠው” እያሉ የሚሰነዝሩት የፖለቲካ ብልጠት መሰረት የለውም።
ወልቃይት ወደ ትግራይ የተካተተው በታሪክ የትግራይ አካል ስለነበር ነው እንዳይሉ የኢትዮጵያ ታሪክ መመዝገብ ከጀመረበት ወያኔ እስከተፈጠረበት ዘመን ድረስ ወልቃይት የትግራይ ክፍል እንደነበር የሚያሳይ አንዳች የታሪክ ማስረጃ ማቅረብ አይችሉም። “የወልቃይት ጉዳይ” በሚል ባዘጋጀሁት የታሪክ ጥናት ውስጥ በዋናነት የትግራይ ገዢዎችና ከትግራይ የተወለዱ የኢትዮጵያ ነገሥታት የነበሩ የታሪክ ሰዎች የሰጧቸውን የታሪክ ምስክርነቶች በመሰነድ እንዳሳየሁት ወልቃይት በአንድም የታሪክ ዘመን የትግሬ ግዛት ሆኖ አያውቅም። የወልቃይት የ1660 ዓመታት የወሰን፣ የማኅበረሰብና አስተዳድር ታሪክ በሚመለከት “የወልቃይት ጉዳይ” በሚል ያዘጋጀሁትን የታሪክ መጽሐፍ ያነቧል።
የትግራይ ብሔርተኞች ወልቃይትን በታሪክ፣ በሕግም ሆነ በማኅበረሰባዊ ትስስር የትግራይ ማድረግ ሲያቅታቸው አንድ የደከመ መከራከሪያ ሲያቀርቡ አያለሁ። ይህም ክልል የመጣው ከ1984 ዓ.ም. በኋላ ስለሆነ እና “የአማራ ክልል” ከ1984 ዓ.ም.  ስላልነበረ  በፊት  አከላለሉ ሕዝብና ቋንቋን መሰረት ሲያደርግ ወልቃይት ወደ ትግራይ ተካለለ የሚል ነው። የዚህ መከራከሪያ መነሻ ወልቃይትን ትግሬ አስተዳድሮት ባያውቅም ኗሪው ግን ትግሬ ነው ለማለት ነው።  ሐቁ ግን ለቀን ስራ በኤርትራ በኩል ዞረው ወደ ወልቃይት ከሚሄዱ ትግሬዎች  ውጭ  ኗሪው አማራ እንደነበር  የትግራይ ሰዎች የሆኑት  ዐፄ ዮሐንስ  ሆነ  አራተኛ ትውልዳቸው ልዕል ራስ መንገሻ ሥዩም የማይታጠፍ ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡ ሕወሓት ከአርባ ዓመታት በላይ ዘር ማጥፋት ፈጽሞበትና አፈናቅሎት  ሊጠፋ ያልቻለው አብዛኛው ኗሪው አማራ በመሆኑ ነው፡፡
እንግዲህ! በታሪክም ሆነ በሕግ ወልቃይት የትግራይ ክፍል ሆኖ አያውቅም። ቢያንስ እስካሁን ድረስ አንድም የትግራይ ብሔርተኞች ወልቃይት በታሪክም ሆነ በሕግ የትግራይ ክፍለ እንደነበር አላሳየም። አሁን ጥያቄው የትግራይ ብሔርተኞች ሕወሓት የአማራ የደም ምድር ያደረገውን ወልቃይትን ይገባናል የሚሉት ከምን ተነስተው ነው? የሚለው ነው። ሕወሓት የዘረፈው ሁሉ ይገባናል ቅሚያ ካልሆነ በስተቀር የትግራይ ብሔርተኞች ወሰናቸውን ተከዜን ተሻግረው ወልቃይትን ይገባናል ሊሉ የሚችሉበት አንዳች አመክንዮ የለም።
በርግጥ የትግራይ ብሔርተኞች ሁሉ ወልቃይትን ይገባናል የሚሉበት አንዳች አመክንዮ ባይኖራቸውም የወልቃይትን ጉዳይ የመሬት ማስለለስ ጉዳይ አድርገው በማሳነስ ሊያሳኩት የሚፈልጉት አንድ የፖለቲካ ብልጠት አላቸው። ይህም በማይካድራ በግፍ የተፈጁትና ከአርባ አመታት በላይ ሲታረዱ፣ ለአውሬ ሲጣሉ፣ ሲፈናቀሉ፣ ሲታሰሩና ተነግሮ የማያልቅ ግፍ ሲፈጸምባቸው የኖሩት የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሁመራ የአማራ ተወላጆች ላይ የተካሄደው የዘር ማጥፋት እንዲድበሰበስና ፍትሕ እንዳያገኝ፤ የማይካድራው አይነት ፍትጅ ወደፊትም እንዲቀጥልና አካባቢው ከአማራ ተወላጆች እንዲጸዳላቸው ይፈልጋሉ።
ሆኖም ግን ዛሬ ላይ የወልቃይት ጉዳይ ሲነሳ መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ውስጥ ሊገባ የማይችለው አካባቢው በማን ስር ይተዳደር የሚለው ጉዳይ ሳይሆን በወልቃይት ሕዝብ ላይ ለደረሰው ተነግሮ የማያልቅ ግፍ ምን አይነት ፍትሕ ይሰጥ? እንዴትስ ይሰጥ? የሚሉት ናቸው።
አንዳንዶች “የወልቃይት ጉዳይ ሕግ ይታይ” ሲሉ እሰማለሁ። የወልቃይት ጉዳይ በሕግ ይታይ ከተባለ መታየት ያለበት ፓርላማ ተብዮው በአፋጣጥኝ ገለልተኛ ኮሚሽን አቋቁሞ በሕወሓት በጅምላ የተገደሉትን፣ የዘር ማጥፋት የተፈጸመባቸውን፣ የተፈናቀሉትን፣ አላግባብ ንብረታቸው የወደመባቸንና የት እንደደረሱ የማይታወቁ የወልቃይት የአማራ ተወላጆች የሚካሱበትንና ፍትሕ የሚያገኙበትን ሁኔታ ባፋጣኝ ለመፍጠር መሆን አለበት።
ስለዚህ ካሁን በኋላ ስለ ወልቃይት ሲነሳ ዋናው ትኩረት መሆን ያለበት የወሰን ጉዳይ ሳይሆን የፍትሕና የካሳ ጉዳይ መሆን አለበት። ወልቃይት በታሪክ ይተዳደር የነበረው በማን ሥር እንደነበረ ታሪኩ በአግባቡ የተሰነደ ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግም። በየትም አለም ቢሄድ ሕግ የሚለው ሀሳብ የተጸነሰው ፍትሕ ለመስጠትና የተጎዳን ለመካስ እንጂ ጉልበተኛ፣ አጭበርባሪ ወይም ባለጊዜ በኃይል የቀማውን የሰው ንብረት እንዲያዘገየው ወይም ይዞታው አድርጎ እንዲጸናለት አይደለም።
ሲጀመር አንድ በጉልበት የተዘረፈን ንብረት ለማን ይገባል? የሚል ጥያቄ መነሳት የለበትም። በጉልበት የተወሰደን ንብረት ለማን ይገባል የሚል ጠያቂ በኃይል ከቀማው ተለይቶ ሊታይ አይገባም። አንድ ንብረት በኃይል ከተወሰደ በኋላ ፍትሕ ሲታሰብ መነሳት ያለባቸው ጉዳዮች ንብረቱ የተዘረፈበት አካል ምን አይነት ጉዳት ደርሶበታል? ምን አይነት ካሳ ያስፈልገዋል? ወንጀለኛው ዘራፊስ ምን ይቀጣ? የሚሉት ብቻ ናቸው። የትግራይ ብሔርተኞች ግን ሕወሓት የዘረፈው ለባለቤቶቹ ሳይሆን ለኛ ይገባናል የሚሉበት ሕግ ተምረናል የሚሉን ጭምር ናቸው። በመሆኑም ሕወሓት በጉልበት የተወሰደውን ወልቃይትን ለኛ ይገባል የሚል ጥያቄ ጠያቂዎቹ የትግራይ ብሔርተኞቹ ሁሉ በኃይል ከቀማው ከሕወሓት ተለይተው ሊታዩ አይገባም።
ወልቃይት በሕወሓት ቅኝ ግዛት ወይም በጉልበት የተያዘ ነው፡፡ ከወሰንና አስተዳደር አኳያ ባለቤትነቱ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ በታሪክም ሆነ የትግራይ አስተዳዳሪዎችና ከትግራይ የፈለቁ የኢትዮጵያ ነገሥታት በሰጡት ምስክርነት ወልቃይት የአማራ ምድር ነው። ሕወሓት በቅኝ ግዛት በያዘበት ባለፉት አርባ ዓመታት ግን ወልቃይት በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአለም ላይ እጅግ ዘግናኝ ግፍ ከተፈጽመባቸው አካባቢዎች አንዱ ሆኗል፡፡ ለዚህም ነው ወልቃይት በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአለም ላይ እጅግ ዘግናኝ ግፍ ከተፈጽመባቸው አካባቢወች አንዱ የሆነውን ወልቃይትን ጉዳይ በአማራ ይሁን በትግራይ እያሉ እንደ እንደሚቀልዱትና በማይካድራ በግፍ ለታረዱትና ክአርባ አመታት በላይ የግፍ መለማመጃ ሆነው ለኖሩት ወልቃይቴዎች ምንም ሰባዊነት እንደሌላቸው የትግራይ ብሔርተኞች ተራ የመሬት ማስመለስ ጉዳይ አድርጎ ማቅረብ ስህተት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም የሚሆነው። ምን አይነት አረመኔነትስ ነው ከአርባ ዓመታት በላይ traumatize ሲደረግ የኖረን ሰው traumatize ከሚያደርገው አካል ጋር አብረህ ኑር ብሎ ሊፈርድበት የሚችለው?
“የወልቃይት ጉዳይ” በሚለው መጽሐፌ ማጠቃለያ እንዳወሳሁት የአማራና ትግሬ ነገዶች በወንድማማችነት የኖሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የግራኝንና የኦሮሞ ገዢ መደብ በኢትዮጵያ ላይ ያካሄዱትን  ወረራ ከባሌ ጀምሮ በግንባር ቀደምነት አብረው በመመከት  ለአገራቸው  አብረው ወድቀዋል። ወሰን ሳይገድባቸው በተመቻቸው ቦታ በአባቶቻቸው አገር  አብረው ኖረዋል። ለዘመናት የኖረውን   የአስተዳደርና የመልክዓ ምድር ወሰን በመሻገር የጥላቻ ግንብ የገነባው ሕወሓት ነው። የአማራ እና የትግሬ  ሕዝብ ወንድማማችነት እንዲታደስ ከተፈለገ ለፍትሕ፣ ለእውነትና ለሞራል የቆሙ የትግራይ ተወላጆች “ከመሬቱ እንጅ ከሕዝቡ ምን አለኝ” ከሚል የሕወሓት  አስተሳሰብ ወጥተው  ሕወሓት የኖረውን የትግራይ ወሰን የከተዜን ወንዝ ተሻግሮ  ባለፉት አራት አስርት ዓመታት በወልቃይት የአማራ ተወላጆች ላይ ያካሄደውን የዘር ፍጅት እና  ምድሪቱ ከምትሸከመው በላይ የፈጸመውን ግፍ በማውገዝ የአማራው ህመም ሊገባቸው፤  ሕወሓት በፕሮግራም ይዞ በአማራ ላይ ያካሄደውን  የዘር ፍጅትና ግፍ  እውቅና ሊሰጡ፤  በአደባባይ ሊያግዙና ከወልቃይት እና ከመላው አማራ  ግፉአን ጎን  ሊቆሙ ይገባል። ይህ ሲሆን በትግሬና በአማራ ሕዝብ መካከል ወያኔ ሲፈጥረው የኖረው ቅራኔ closure አግኝቶ የኖረው ወንድማማችነት ይታደሳል::
ባጭሩ ስለወቃይት የሚከራከሩ ወገኖች በወሰንና ማንነት ጉዳይ ጊዜ ማጥፋት የለባቸውም። ከአሁን በኋላ የወልቃት ጉዳይ በወልቃይት ለደረሰው ግፍ እንዴት ፍትሕ ያግኝ፤ የወልቃይት ሕዝብ እንዴት ይካስና ስለ መልሶ ማቋቋም መሆን ይኖርበታል፡፡ የአማራ መንግሥት ነኝ የሚለው አካል ካለ እና የአማራ ባለ ጉዳይ ከሆነ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአለም ላይ እጅግ ዘግናኝ ግፍ ከተፈጽመባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው በወልቃይት ምድር በሕወሓት በጅምላ የተገደሉትን፣ የዘር ማጥፋት የተፈጸመባቸውን፣ የተፈናቀሉትን፣ አላግባብ ንብረታቸው የወደመባቸንና የት እንደደረሱ የማይታወቁ የአማራ ተወላጆችን ጉዳይ የሚመረምር ገለልተኛ ኮሚሽን ፓርላማ ተብዮው በአስቸኳይ እንዲቋቁምና ወደ ስራ እንዲገባ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
ከታች የታተመው ዶሴ ወያኔ እነወልቃይትን ወደ ትግራይ ያካተተው በ1968 ዓ.ም. ባወጣው ማኒፌስቶ እንጂ በሕገ መንግሥት ተብዮው መሰረት አለመሆኑን የሚያሳየን የሕወሓት ፕሮግራም እናት መዝገብ ነው።
ሲጀመር አንድ በጉልበት የተዘረፈን ንብረት ለማን ይገባል? የሚል ጥያቄ መነሳት የለበትም። በጉልበት የተወሰደን ንብረት ለማን ይገባል የሚል ጠያቂ በኃይል ከቀማው ተለይቶ ሊታይ አይገባም። አንድ ንብረት በኃይል ከተወሰደ በኋላ ፍትሕ ሲታሰብ መነሳት ያለባቸው ጉዳዮች ንብረቱ የተዘረፈበት አካል ምን አይነት ጉዳት ደርሶበታል? ምን አይነት ካሳ ያስፈልገዋል? ወንጀለኛው ዘራፊስ ምን ይቀጣ? የሚሉት ብቻ ናቸው። የትግራይ ብሔርተኞች ግን ሕወሓት የዘረፈው ለባለቤቶቹ ሳይሆን ለኛ ይገባናል የሚሉበት ሕግ ተምረናል የሚሉን ጭምር ናቸው። በመሆኑም ሕወሓት በጉልበት የተወሰደውን ወልቃይትን ለኛ ይገባል የሚል ጥያቄ ጠያቂዎቹ የትግራይ ብሔርተኞቹ ሁሉ በኃይል ከቀማው ከሕወሓት ተለይተው ሊታዩ አይገባም።
ወልቃይት በሕወሓት ቅኝ ግዛት ወይም በጉልበት የተያዘ ነው፡፡ ከወሰንና አስተዳደር አኳያ ባለቤትነቱ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ በታሪክም ሆነ የትግራይ አስተዳዳሪዎችና ከትግራይ የፈለቁ የኢትዮጵያ ነገሥታት በሰጡት ምስክርነት ወልቃይት የአማራ ምድር ነው። ሕወሓት በቅኝ ግዛት በያዘበት ባለፉት አርባ ዓመታት ግን ወልቃይት በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአለም ላይ እጅግ ዘግናኝ ግፍ ከተፈጽመባቸው አካባቢዎች አንዱ ሆኗል፡፡ ለዚህም ነው ወልቃይት በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአለም ላይ እጅግ ዘግናኝ ግፍ ከተፈጽመባቸው አካባቢወች አንዱ የሆነውን ወልቃይትን ጉዳይ በአማራ ይሁን በትግራይ እያሉ እንደ እንደሚቀልዱትና በማይካድራ በግፍ ለታረዱትና ክአርባ አመታት በላይ የግፍ መለማመጃ ሆነው ለኖሩት ወልቃይቴዎች ምንም ሰባዊነት እንደሌላቸው የትግራይ ብሔርተኞች ተራ የመሬት ማስመለስ ጉዳይ አድርጎ ማቅረብ ስህተት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም የሚሆነው። ምን አይነት አረመኔነትስ ነው ከአርባ ዓመታት በላይ traumatize ሲደረግ የኖረን ሰው traumatize ከሚያደርገው አካል ጋር አብረህ ኑር ብሎ ሊፈርድበት የሚችለው?
ባጭሩ ስለወቃይት የሚከራከሩ ወገኖች በወሰንና ማንነት ጉዳይ ጊዜ ማጥፋት የለባቸውም። ከአሁን በኋላ የወልቃት ጉዳይ በወልቃይት ለደረሰው ግፍ እንዴት ፍትሕ ያግኝ፤ የወልቃይት ሕዝብ እንዴት ይካስና ስለ መልሶ ማቋቋም መሆን ይኖርበታል፡፡ የአማራ መንግሥት ነኝ የሚለው አካል ካለ እና የአማራ ባለ ጉዳይ ከሆነ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአለም ላይ እጅግ ዘግናኝ ግፍ ከተፈጽመባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው በወልቃይት ምድር በሕወሓት በጅምላ የተገደሉትን፣ የዘር ማጥፋት የተፈጸመባቸውን፣ የተፈናቀሉትን፣ አላግባብ ንብረታቸው የወደመባቸንና የት እንደደረሱ የማይታወቁ የአማራ ተወላጆችን ጉዳይ የሚመረምር ገለልተኛ ኮሚሽን ፓርላማ ተብዮው በአስቸኳይ እንዲቋቁምና ወደ ስራ እንዲገባ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
ከላይ የታተመው ዶሴ ወያኔ እነወልቃይትን ወደ ትግራይ ያካተተው በ1968 ዓ.ም. ባወጣው ማኒፌስቶ እንጂ በሕገ መንግሥት ተብዮው መሰረት አለመሆኑን የሚያሳየን የሕወሓት ፕሮግራም እናት መዝገብ ነው።
Filed in: Amharic