“የኦሮሞ ብልፅግና ከአማራ ሕዝብ ጋር ባለመስማማት ታሪካዊ ስህቶችን እንዳይፈፅም ከሕወሓትም ሊማር ይገባዋል…!!!”
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ለኦሮሞ ብልፅግና ያስተላለፉት መልዕክት
የኦሮሞ ብልፅግና በታሪክ አጋጣሚ በእጃቸው የገባውን የሀገረ መንግስት ስልጣን በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባልም ብለዋል።
“እኔ ስልጣኔን እንዳስረክብ የሆነው ህወሃትን የአማራ ህዝብ መፈናፈኛ ስላሳጣው ነበር። ህወሃቶች ስልጣን ላይ ሊያስቀምጡት የነበረው አቶ ደመቀን ነበር። ይህም ጃዋር ለተባለ ሰው እንዳልተጨነቁ ማሳያ ነው። ህወኃት ለጃዋር ተጨንቀው ቢሆን ኖሮ ለምን አሁን የአማራ ህዝብ ጠላት እሱን ደግሞ ወዳጅ አደረጉት?
ዶ/ር አብይ በምትኩ ስልጣን ላይ እንዲወጣ ያደረጉት ብአዴኖች ናቸው። በመጨረሻ ለውጡ እንዲመጣ ያደረገው ዶ/ር አብይ ራሱ ነው። ቄሮ የለውጥ ሞተር የሚባለው እኮ የኦሮሞ ህዝብ ከፖለቲካው ተገልሏል የሚለውን የቆየ ትርክት አስቀርቶ የኦሮሞን ወጣት በሀገሩ ጉዳይ በንቃት እንዲሳተፍ ለማድረግ በራሱ በብአዴን Recommend የተደረገ ነው ። ይላሉ አቶ ሀይለማርያም
እናም በዚያን ጊዜም ሆነ አሁን ትልቁ የኦሮሞ ጠላት ቢኖር ጆዋር የሚባል ሰው ነው። ዛሬ እንደታዘባችሁት ይህ ሰው ሚሊየነር ለመሆን የማይዋሸው ነገር የለም። የእሬቻ በአል ላይ ለእንኳን አደረሳችሁ የላክነውን ሄሊኮፕተር ቦንብ የያዘ ነው ብሎ መልዕክት እንድተላለፍ በማድረግ ብዙ ሰዎች እንዲሞቱ አድርጓል። በዚያን ወቅት በሱ ፕሮፖጋንዳ በመቶዎች የሚሆኑ ፋብሪካዎች አመድ ሆነዋል። በ100ሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ስራ አጥ እንዲሆኑ አድርጓል። ኢትዮጵያም ከመጣ በኋላ በየሄደበት ሁሉ እስከማሰቀል የሚደርስ አሰቃቂ ግድያዎችን በኦሮሞ ወጣቶች ላይ አድርሷል ።
በዚያ ላይ በሚሰብከው የውሸት ትርክት የኦሮሞን ህዝብ ስነልቦና ጎድቷል። ከወንድም እና እህት ከነበሩ ሌሎች ህዝቦች ጋር አለያይቷል። ከኢትዮጵያ ማንነቱ እንድያፈነግጥ ይሰራል! ይህን ሁሉ የሚያደርገው ሀብቱን ለማካበት ነው! ኦሮሚያ ውስጥ እሞታለሁ ሲል ከአሜሪካ ይልቅ የኦሮሞን ህዝብ እየቦጠቦጥኩ ቢሊየነር እሆናለሁ ማለቱ ነው!”
ሀይለማርያም ደሳለኝ ለCGTN ከተናገሩት