>

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ "ነገ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ ሰበር ሰሚ ችሎት እንናኝ...!!!"

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

“ነገ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ ሰበር ሰሚ ችሎት እንናኝ…!!!”
ባልደራሶች ከቃሊቲ ወህኒ ቤት ለህዝቡ ያቀረቡት ጥሪ 

 

ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን 
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች ማለትም #እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩምና አስካለ ደምሌ ነገ አርብ የካቲት 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።
ከረፋዱ አራት ሰዓት ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ ሰበር ሰሚ ችሎቱ ጉዳያቸውን ይመለከተዋል።
ይህ ችሎት ላልተወሰነ ጊዜ ምስክሮች እንዳይሰሙ ቢያግድም ነገ ብይን ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል።
“ምስክሮችን በግልፅ ችሎት ማቅረብ አልችልም ።  ያሉኝ ምስክሮች በግልፅ ችሎት ስለማይቀርቡልኝ ውሳኔው ካልተሻረ ማስረጃ ሳይሰማ ተከሳሾችን በነፃ እንደመልቀቅ ይቆጠራል”  ሲል ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ በመጠየቁ ነው ጉዳዩ ከከፍተኛው ፍርድ ቤት ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተዘዋወረው። የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሚመለስም የችሎት ቀጠሮው ያመላክታል።
 የነገው ችሎት ‘ምስክሮች በግልፅ ችሎት ይቅረቡ’ የሚለውን የከፍተኛውን ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ከደገመው ብሎም ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ምስክሮቹን ካላቀረበ ተከሳሾች በነፃ የሚሰናበቱበት ሕጋዊ አግባብ አለ።
በመሆኑም መገናኛ ብዙሃን ይህንን ታሪካዊ ችሎት በአዳራሽ ውስጥ ተገኝታችሁ እንድትዘግቡ ተከሳሾች ከቃሊቲ ወህኒ ቤት ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።
Filed in: Amharic