የራሱን መንግስት የሚያሸብረዉ አቢይ …!!!
ሸንቁጥ አየለ
የራሱን መንግስት የሚያሸብረዉ አቢይ በሸዋ አማራ ላይ በዚህ ሳምንት ጦርነትና ሽብር ከፍቷል:: ምናልባትም በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ደግሞ በጎጃም አማራ ላይ ጦርነት እና ሽብር ይፈጥር ይሆናል::
ብዙዎች “ዝናብ በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ላይ አዘነብን” ብሎ አቢይ የተናገረዉን ንግግር በግልጽ ቋንቋ አሸባሪዉ እራሱ መንግስት መሆኑን የመሰከረበት ነዉ እያሉት ነዉ::
የሆነ ሆኖ የኦነግ/ኦህዴድ ሰራዊት በመንግስት እየታገዘ እና እየታዘዘ የከፈተዉ ጦርነት በህዝብ ሀይል የእጁን አግኝቷል::አቢይ በራሱ መንግስት ላይ እሳት እያነደደ ነዉ::የቆላ ሰዉ አስቴኒ ይለዋል::ወታደራዊዉ ሳይንስ ደግሞ ከደረቅ ነገር ሁሉ አፋጭተህ ከእንጨቱም ከድንጋዩን አፋጭተህ እሳት የማዉጣት ጥበብ ይለዋል::
እናም አቢይ ቢቀሰቀስ አልሰማ ብሎ የተኛዉን ብዙሃን በሽብር እየናጠ ጦረኛ እያደረገዉ ነው::በሽብር እና በጦርነት: በማፈናቀል እና በዘር ፍጅት እያዋከበ ህዝቡን ለጥሩ ጦረኝነት እያዘጋጀዉ ነዉ::
አጣዬ: ሸዋሮቢት የተስተዋለዉ ይሄዉ ነዉ::የኦነግ/ኦህዴድ ሰራዊትን ጀግናዉ ህዝብ ገልቦ ገርፎታ:: ግን ጅማሮ ነዉ::አቢይም የራሱን መንግስት ማሸበሩን ይቀጥላል::ህዝቡም እራሱን ወደ ጦረኛ ሃይል ያሳድጋል::
ጦርነቱም አቢይ ቤተ መነግስት ደጃፍ አዲስ አበባ ላይ ይመጣለታል::አቢይ የሆነ የታወረበት ነገር አለ::ብዙሃኑን አላወቀዉም::ጦረኛዉን ህዝብ ፈጽሞ አላወቀዉም::
ሙሶሎኒ በጣሊያን ወረራ ወቅት በአንድ ቀን ስምንት መቶ ሽህ አማሮችን ከጅማ እና ከሀረር አፈናቅሎ ነበር::ተፈናቃዮቹም ወደ አዲስ አበባ ተሰባስበዉ ነበር::እናም የአርበኞቹ ክንድ አዲስ አበባ ላይ ከመፈናቀል ድርጊቱ ብኋላ እንደ ብረት ጠነከረ::
ወዲያዉ ወታደራዊ አማካሪዎቹ “ህዝቡን ወደ አዲስ አበባ እያፈናቀልን ትልቅ የጠላት ማዕከል ፈጠርን::አርበኛዉ በተፈናቃዩ መሃል ገብቶ መጠለያ አገኘ::” ብለዉ ሪፖርት አደረጉለት::ሙሶሎኒም ወዲያዉኒ “ማፈናቀል አቁሙ” ሲል አማራዉን የማፈናቀል ፖሊሲዉን እንደቀየረ በታሪክ ተዘግቧል::
አሁን ከዚያ በባሰ ሁኔታ ታላቅ የጠላት ማዕበል እያዘጋጀ ላለዉ ለአቢይ አህመድ ይብላኝለት::ለእሱ ብቻ ሳይሆን ከሱ ጋር ለቆመዉ ሁሉ:: ቢቀሰቀስ እንቢ ብሎ የተኛዉን ህዝብ እንድ አስተኒ አፋጭቶ እሳት ከድንጋይ እያወጣ ነው::እሳቱ እጅግ ከባድ እና የአቢይን አጠቃላይ መንግስት አጣምቶ እንደሚበላዉ አቢይ አላወቀም::