የዓብይ አህመድ ኩሸት!!
ኤርሚያስ ለገሰ
ከምርጫው በኃላ ብልጽግና ከኢህአዴግ በባሰ ደረጃ አውራ ፓርቲ ይሆናል። የዴሞክራሲ መቃብር ላይ የጥቁር አበባ ጉንጉን በዓብይ አህመድ ግብዣ ወዲ አፍወርቂ ያስቀምጣል!!
*… ይድረስ ለአማራ ብልፅግና( የምትሰሙ ከሆነ!)
1. በፓርላማ ምን አለ?
“የሚቀጥለው ምርጫ በጣም ወሳኝ ምርጫ ነው። ኢትዮጵያ የምታሸንፍበት ምርጫ ነው። “
“እኛ ከተሸነፍን ሁለቴ አናስብም! አስረክበን እንወጣለን።”
2. እውነታው ምንድነው?
2.1. የኦሮሚያ ክልል ምክርቤት ምርጫው ሳይካሄድ አልቋል።
2.2. የቤኔሻንጉል ክልል ምክርቤት ምርጫው ሳይካሄድ አልቋል።
2.3. የሐረሬ ክልል ምክርቤት ምርጫው ሳይካሄድ አልቋል።
2.4. የድሬደዋ ክልል ምክርቤት ምርጫው ሳይካሄድ አልቋል።
2.5. የሲዳማ ክልል ምክርቤት የሲዳማ ብልፅግናና ተቃዋሚው (ሲአን) ዛሬ ባደረጉት የወንበር ክፍፍልና ሌሎች የውስጥ አስደንጋጭ ውሳኔዎች ምርጫው ሳይካሄድ አልቋል።
(በዚህ አጋጣሚ አዋሳ የምትኖሩ የወላይታ፣ ጉራጌና አማራ ተወላጆች ለደህንነታችሁና ንብረታችሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ። ብልፅግና አዲስ አበባ ላይ እያደረገ እንዳለው በሚስጥር እየተሰራ መሆነ ተጨባጭ መረጃዎች ደርሰውናል።)
2.6. ትግራይ ክልል ምርጫ የለም።
3. አንድምታው ምንድነው?
3.1. የፌዴራል ስርአቱን በተመለከተ፤ የመሬት ፖሊሲን በተመለከተ፤ አንቀፅ 39 በተመለከተ፤ የፌዴራሉ የቋንቋ ፓሊሲን በተመለከተ የምርጫ ክርክር ተካሄደም/አልተካሄደም የሚለወጥ ነገር አይኖርም። እነዚህ ሕገ መንግስታዊ ጉዳዮችን ለመለወጥ ከተፈለገ ከምርጫው በፊትም ሆነ በኋላ የብልፅግና መልካም ፍቃድ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። በአጭሩ ለውጥ ማድረግ የሚችለውም ብልፅግና እና ብልጽግና ብቻ ነው። ምርጫውንም መጠበቅ የለበትም።
3.2. ከምርጫው በኃላ ብልጽግና ከኢህአዴግ በባሰ ደረጃ አውራ ፓርቲ ይሆናል። የዴሞክራሲ መቃብር ላይ የጥቁር አበባ ጉንጉን በዓብይ አህመድ ግብዣ ወዲ አፍወርቂ ያስቀምጣል!!
እናም ዓብይ አህመድ አትዋሽ!!
ይድረስ ለአማራ ብልፅግና( የምትሰሙ ከሆነ!)
እወክለዋለው የምትሉት ማህበረሰብና ክልላችሁ በአራቱም ማዕዘናት ከውስጥም ከውጭም በጠላት ሴራ ተወጥሯል። እናንተ ደግሞ እንዴት በመቶ ፐርሰንት ምርጫውን እናሸንፋለን ብላችሁ ሰነድ አዘጋጅታችሁ ትወያያላችሁ።
ትንሽ አይሸክካችሁም? እንዴት የግለሰባዊ ስልጣን ጥማታችሁ ከህዝባችሁ የሕልውና አደጋ በላይ ሆነባችሁ?
ዛሬ በዓብይ አህመድ የሚመራው ኦሮሙማ የበላይነቱን ተጠቅሞ አደራዳሪ በመሆን የሲዳማ ብልጽግናን እና ተቃዋሚውን(ሲአን) በወንበር ክፍፍል አስማምቷል። በሲዳማ ከምርጫው በፊት ሁሉም ነገር እንዲያልቅ አድርጓል።
በተቃራኒው እናንተ አማራ ክልልና አዲስ አበባ ህዝቡንና የፓለቲካ ፓርቲዎችን የጠላት ወዳጅ ክፍፍል በመስራት ተጠምዳችኃል። እኔ እምለው እንዴት ሶስት አራት ከመሃላችሁ የመጣውን የሕልውና አደጋ በአስተውሎት ማሰብ የቻለ ይጠፋል?