>

የሕወሓቱ ብአዴን የኦሮሙማው አዴፓ - ስልቻ ቀልቀሎ ቀለል ስልቻ...!!!   (አቻምየለህ ታምሩ)

የሕወሓቱ ብአዴን የኦሮሙማው አዴፓ – ስልቻ ቀልቀሎ ቀለል ስልቻ…!!!

  አቻምየለህ ታምሩ

የሕወሓቱ ብአዴን በ1986 ዓ.ም. ባሳተመው ድርጅታዊ ፕሮግራሙ ላይ በግልጽ እንደነገረን በዋናነት ይታገል የነበረው ወራሪ፣ ነፍጠኛ፣ ትምክሕተኛና ብሔረ፣ ብሔረሰቦችን ሲጨቁን ኖረ ያለውን በተለይም አማራ ክልል ከሚባለው ውጭ የሚኖረውን አማራ ለማጥፋት ነበር።
ከሕወሓት ነውረኛ ድርጅትነት ወደ ኦሕዴድ/ኦነግ ጉዳይ አስፈጻሚነት የተሻጋገረው የዘንድሮው የኦሮሙማው ብአዴን ደግሞ ከታች በምታዩዋት ጉድ በኩል መላው አማራ ብሔረ፣ ብሔረሰቦች የተባሉትን ሲጨቁኝ እንደኖረ እየነገረን ነው። ይቺ የብአዴን ጉድ የሕወሓቱን ብአዴን በማስናቅ መላው የአማራ ሕዝብ ጨቋኝ እንደነበር በአደባባይ የበየነችው ጨቋኝ የምትለውን የአማራ ሕዝብ ልታስተዳድር የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ባለችበት ወቅት ነው።
ይህ ማለት እንደ ሕወሓቱ ብአዴን ሁሉ የኦሮሙማው ብአዴንም የሚታገለው አማርኛ ተወልዶ ያደገባቸው የአገራችን ክፍሎች አማራ የሚታረድባቸው ቄራዎች እንዲሆኑ ለማድረግ ነው።
ብአዴንና ይችን መሰል ጉዶቹ ከአማራ ሕዝብ ጫንቃ ላይ እስካልተወገዱ ድረስ ኢትዮጵያ የአማራ መታረጃ ቄራ ሆና መቀጠሏ ሳይታለም የተፈታ ነው። ለዚህም ነው የአማራ ግንባር ቀደም ባለደም ብአዴን የሚባለው ነውረኛ ድርጅት ነው፤ በመላው ኢትዮጵያ በአማራ ላይ እየተካሄደ ያለው የጅምላ ፍጅት የአማራው ርግማን ብአዴን በፕሮግራም ይዞ የታገለለት ዓላማ ነው ስንል የነበረው።
Filed in: Amharic