>

የደናቁራን ሕብረት (ኤልያስ ደግነት/የሺ/

የደናቁራን ሕብረት!

 

ኤልያስ ደግነት/የሺ/

አፍ እንዳመጣ መናገር ከመፍሳ..…. .ከማግሳትም አይሻልም!


ከግብፃዊያን ባህሪ እጅጉን የሚያስቀናኝ ነገር አንዱ በሀገርና በዓባይ ጉዳይ ከሃይቅ የሚሰፋውን የውስጥ ስንጥቃታቸውን ወደ ጎን አድርገው አንድ በሚያደርጋቸው ነገር ሲንገበገቡ ሳይ ያስቀኑኛል፡፡ከሰሞኑ አንድ በስደት የሚኖር ግብፃዊ ሰው/ኳታር መሰለኝ የሚኖረው/ በአልጀዚራቀርቦ በዓባይ ጉዳይ እና በሀገሩ ግብፅ ሉዓላዊነት ጉዳይ ደሙ እየፈለ ኢትዮጵያ እየተሳደበ…አገዛዟን እየነቀፈ ወደር በሌለው እልህ ሲናገር ሰማሁት፡፡ በዓባይ እና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚያነሳቸው ያልተገቡ ነገሮች ያበግናሉ፡፡ከማብገንም በላይ ቲቨውን በለው በለው የሚል የጅልሀሳብ ያስመጣል፡፡ የኃላ ኃላ ግን የሚያስቀናው ነገር ተከሰተና ስለ እና ስለ እኛ ደናቁራን በማሰብ ሌላ ብግነት …እና ጭሰት ውስጥ ገባሁ፡፡

በጣም የሚገርመው ይህ ግብፃዊ አል ሲሲ በመፈንቀለ መንግስት የገለበጠው የሙስሊም ብራዘርስ ሁድ ፓርቲ ቀንደኛ አቀንቃኝ እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሞሓመድ ሙርስ ተከታይ ነው፡፡በዚህ እና በሌሎች ጉዳዮች አልሲሲን አብዝቶ ከመንቀፍ እና ከመክሰስ ተመልሶ አያውቅም፡፡በዚህም ሳቢያ ከሀገሩ ከመሰደድም ባሻገር የአልሲሲ አገዛዝ እስካለ ድረስ ወደ ግብፅ እንዳይገባ ዕገዳ የተጣለበት ሰው ነው፡፡

ይህ ሰው ታድያ ምንም ያህል አልሲሲንም ሆነ አገዛዙን ቢጠላ የመኖራችን ሕልውና ነው ብሎ በሚያስበው ዓባይ እና በሀገሩ ጉዳይ ድርድር ብሎ አገር የለም!

ይሄኔ ነው ወትሮም እገረምባቸው የነበሩ እነኚህን የእኛዎቹን ደናቁራን ማሰብ የጀመርኩት፡፡እንዴት እንደሚያበግኑኝ እኮ!! ሀገር እንዲህ ባለው ክፉ ቀን ተከባ…ዓይን አፍጦ …ጥርስ አግጦ የመጣ የውጭ ሃይል ከደጇ ቁሞ ሳለ…..ግብፅ በዓባይ ጉዳይ እንቅልፍ አጥታ ደንቃራውንምስትጥል…ኮረሪማውንም ስትሰቅል…አዋቂ ቤቱንም ሁሉ ስትሞክር አንዳቸውም በጠባብ ልባቸው ውስጥ ካሰፏት የዕለት ከርስ መሙያ ከሆነች እንጎቻ ውጪ ማሰብ ተስኗቸው …..ሀገር ማገሯ ሊወድቅ ነው….መሰረቷ ሊናጋ ነው ሲሉ ሰምቻቸው አላውቅም፡፡ ሁሉም አዛኝ ቅቤ አንጓችሆነው አማራው ተጎዳ …ኦሮሞው ተበደለ…እከሌ እንዲህ ሆነ ከማለት ውጪ ስለ ሀገር አንድነት እና ስለ ባንዲራ ክብር ሲጨነቁ አለማየት ያማል፡፡ /ለተበደለ መቆም ምንም ኃጥያት የለውም/

ገሚሱ አያቶቹ በጠጡት ጠላ የሰከረ ነው…ሌላው ደግሞ በእከሌ ስም ካልተቃወምኩ እና ካላወራሁ እንዴት ብዬ ኑሮዬን እገፋለሁ ባይ ከርሳም ሆድ አደር ነው፡፡ወዲህ ደግሞ ሌላው ከንፁሓን ደም ተቀድቶ የሚጋተው እና የሚሰፈርለት እርጥባን እንዳይቀርበት የጌቶቹን መገበሪያ የበላሳይጠምቁት የሚለፈልፍ ነው፡፡

እነዚህ ሁሉ ታድያ አረረም መረረም ኢትዮጵያ በምትባል ሀገር ውስጥ ተወልደው ያደጉ ….ኢትዮጵያዊ ነን ባዮች ናቸው፡፡ አይደለንም ያሉትም አይደልንመ ቢሉ ግድ ሲመጣ ወደየትኛውም ሀገር ፈቅ ማለት አይችሉም፡፡

ሀገር ቤት ችግር የለም አይባልም፡፡ችግር ሞልቶ ተርፏል፡፡ ድሮም አለ…አሁን አለ…ወደፊትም ይኖራል፡፡የጨቋኝ ተጨቋኝ ነገርም እንደቆምንበት ቦታ ይለያል፡፡በየትኛውም ሀገር አንድን ሀገረ መንግሰት ሕዝቡ ሙሉ በሙሉ በእኩል ፍቅር ይወደዋልም ይጠላዋልም ማለት አይቻልም፡፡ለአንድ አገዛዝ የሚኖረው ፍቅር እና ጥላቻ አቻ ለአቻ ነው፡፡ይህ መሆኑ ከታወቃ መንቀፍና መደገፍ ስርዓት ባለው መልኩ ሁኖ … ጎደሉ የተባሉት እንዲሟሉ መንገድ እያሳዩ ካልሆነ እድሉን እና አጋጣሚውን ብቻ ስላገኙ አፍ እንዳመጣ መናገር ….ከመፍሳትም ከማግሳትም አይሻልም ፡፡አንደኛቸውን መፍሳት እና ማጋሳት ይሻላሉ ተፈጥሮዋዊ ሚዛናቸውን ጠብቀው ጠረናቸውን እንደሰነፈጠ ይቀጥላሉ፡፡በጥመት አስተሳሰብ …ከከረፋ አንደበት የሚወጡ ቃላት ግና ………ብቻ ይቅር፡፡

አንዳንዴ አለማወቄን የምወደው እንደነዚህ ያሉትን አውቃለሁ ባዮች ሳይ ነው፡፡ዕውቀት እንዲህ የእናት ጡትም ጣትም የሚያስነክስ ከሆነ….ጨዋነት በስንት ጣዕሙ፡፡

የሚገርው ግብጾች ስለ ዓባይ ሽንጣቸውን ገትረው…ዓለም እስከሚያምናቸው ድረስ በየ ሚዲያው ወጥተው ሲታገሉ…አንድም ቀን ወጥቶው ግድቡ የእኔ ነው ሲሉ አለመሰማታቸው ነው፡፡ ዳሩ ሀገር እንደነዚህ ውሃ ሆነው በቀሩ በሚስብሉቱ ልክ እሰይ …ጎሽ የሚያስብሏት ብዙ አል#አሩሲዎች አሏት::

ለማናቸውም እነዚህ እናውቃለን ባይ ልቅልቅ ሊቆች ስርዓቱንም ሆነ መሪውን መጥላት መብታቸው…ነው፡፡ ነገር ግን ልክ ነገ ተመልሰው እንደማይመጡባት …ወዳጅ ዘመድ እንዳላኖሩባት…ዝንት ዓለማቸውን የሰው ሀገር ጃንክ እየበሉ ይኖሩ ይመስል ሀገር ለማፍረስ በማር የተለወሰመርዛም ንግግራቸው/የነገር ክርፋታቸው/ ሁሉ መርጨታቸው.. ውሎ አድሮ…ቀን ሲሄድ …ቀን ሲመጣ ..ታሪክ ሲቀየር ያስተዛዝባቸዋል፡፡በታሪክም አተላ ከመባል እንደማይተርፉ እሙን ነው፡፡

 

አትዮጵያ ትቅደም!!!!

 

 

Filed in: Amharic