>

የጎንደር አማራ መሬቱ ተወሮ ከብቱ ተዘርፎ መንግስት የለውምና ይግባኝ ለፈጣሪ እያለ ነው...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

የጎንደር አማራ መሬቱ ተወሮ ከብቱ ተዘርፎ መንግስት የለውምና ይግባኝ ለፈጣሪ እያለ ነው…!!!

ዘመድኩን በቀለ

 

የሱዳን ወታደሮች ዝርፊያው ስለቀናቸው ግዳይ ስለጣሉ  – መንግስት ተብዬውም ” ወደ ፍርድ ቤት እንጂ ወደ ጦርነት አንገባም!” በማለቱ አላህ ወአክበር – እያሉ መሬት ወረራውን ንብረት ዘረፋቸውን እያከናወኑ አላህ ወ አክብር ይላሉ – ፉከራ ይሁን ጸሎት እነርሱን ፈጣሪ ናቸው የሚያውቁት!
… የማከብረው ዑስታዝ ጀማል በሽር ይሄን አይተረጉምልኝም። ግድብ… ውኃ… እያሉ የሚያዝጉን የዐረብ ቋንቋ ተሟጋቾቻችን ይሄ ይሄ አይታያቸውም። አላህ ወአክበር ይልልሃል የዐማራ ገበሬን ሀብት የሱዳን ወታደር እየዘረፈ።
… ይህ የጎንደር ዐማሮች ንብረት ነው። በዚህ መልኩ በሱዳኖች እየተዘረፈ ወደ ሱዳን እየተጋዘ የሚሄድ የዐማራ ገበሬ ንብረትም ነው ተብሏል። የእውነት እንደ ሰው እንደ ኢትዮጵያዊ ያንገበግባል። ሱዳኖች ይህን ያደርጉ ዘንድ ፈቃድ ያገኙት ደግሞ ከብልጽግና ወንጌሉ መሪ ከአርቲስት ዶክተር ደራሲ ዐቢይ አሕመድ አሊ ነው ይላሉ። አይዞኝ ጎንደር። መቻል ነው እንግዲህ። ሌላ ምን ይደረጋል።
… ጄነራል ባጫ ደበሌ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከሱዳን ጋር ወደፍርድ ቤት እንሄዳለን እንጂ ለመሬት ብለን አዋጋም። ደክሞናል ብሏል። በይፋ። … ኤርትራ ትግራይን…  ሱዳን ጎንደርን ያደቅቁ ዘንድ ባልተጻፈ ሕግ ተወስኖላቸዋል። ኢትዮጵያን አስገድደው እየደፈሯት ነው። አስገድደው። እጅ እግሯን አስረው። አፏን በጨርቅ ጠቅጥቀው። ራቡ እንኳ ትግራይ ብቻ ተወስኖ አይቀርም። ሁላችንም ተዘጋጅተን መጠበቅ ነው። ሰማያዊ ቲሸርት ምግብ ይሆነን ዘንድም አብረን እናየዋለን።
• ጎዣም አይተሃል
• •ወሎ ሰምተሃል
• ሸዋ ተመልክተሃል
… ዐማራማ ዘንድሮ በለጸጋት  !!
#መጪው_ጊዜ_ከብልጽግና_ጋር_ብርር_ነው።
#ዐቢይ_ይምራን  !!
Filed in: Amharic