>
5:13 pm - Friday April 18, 4341

"ምርጫውን ለመታዘብ የመጡት አሜሪካዊ ዜጋ በመኝታ ክፍላቸው ሕይወጌታቸው አልፎ ተገኙ...!!!"  (ኢ.ፕ.ድ)

“ምርጫውን ለመታዘብ የመጡት አሜሪካዊ ዜጋ በመኝታ ክፍላቸው ሕይወጌታቸው አልፎ ተገኙ…!!!” 

ኢ.ፕ.ድ

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት፣ ሙዚቃ፣ ትያትርና የስፖርት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ “ትናንት በራዲሰን ብሉ ሆቴል አሜሪካዊ ዜጋ በመኝታ ክፍሉ ሕይወቱ አልፎ ተገኝቷል” ብለዋል።
የሆቴሉ የጽዳት ሠራተኛ ትናንት ጠዋት አንድ ሠዓት ገደማ አሜሪካዊው ያረፈበትን የመኝታ ክፍል ለማጽዳት ስትገባ ያየችውን ነገር ለፖሊስ ጥቆማ መስጠቷን ገልጸዋል።
ፖሊስ መረጃውን እንዳገኘ ወደ ስፍራው መንቀሳቀሱንና አሜሪካዊው ከአልጋው ላይ ወደ መሬት ወድቆ ሕይወቱ አልፎ እንደተገኘ አመልክተዋል።
በሟች ኪስ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልዩ የምርጫ ታዛቢ ወረቀት (ባጅ)፣ የተለያዩ መታወቂያዎችና መንጃ ፈቃድ መገኘታቸውን ተናግረዋል።
መንጃ ፈቃዱ “በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ብሔራዊ የድራይቪንግ ላይሰንስ” የሚል እንደሆነም አስረድተዋል።
በተጨማሪም አሜሪካዊው የሚጠቀምባቸው “በርካታ” መድሃኒቶችን ፖሊስ ማግኘቱንና “ምናልባት ሁኔታው ሲታይ በተፈጥሮ የሞተ እንደሚመስልና ነገር ግን ትክክለኛው መረጃ ከአስከሬን ምርመራ ውጤት በኋላ እንደሚታወቅ ዳይሬክተሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
“በአሜሪካዊው ዜጋ ሰውነት ላይ ምንም አይነት የአካል ጉዳትና ቁስለት አልተገኘም” ነው ያሉት ኮማንደር ፋሲካ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመሆን በአሜሪካዊው ዜጋ አሟሟት ላይ ምርምራ እያደረጉ እንደሆነም ገልጸዋል።
ፖሊስ አጠቃላይ የምርመራውን ውጤት በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግም አክለዋል።
የካርተር ሴንተር ፕሮግራም በኢትዮጵያ በይፋዊ የትዊተር ገጹ ዛሬ ማለዳ ባወጣው መረጃ በራዲሰን ብሉ ሆቴል ሕይወቱ ያለፈው የተቋሙ የአዲስ አበባ የፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ዶክተር ጆን ማርሽ መሆኑንና ሕይወቱም ትናንት እንዳለፈ ገልጿል።
“የካርተር ሴንተር በኢትዮጵያ በጆን ማርሽ ድንገተኛ ሞት ከፍተኛ ሐዘን ተሰምቶናል፤ ጆን ማርሽ የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ ነው” ብሏል በመግለጫው።
የካርተር ሴንተር ለዶክተር ጆን ማርሽ ወዳጆች መጽናናትን ተመኝቷል።()
Filed in: Amharic