>

ቪቫ ኢትዮጵያ (የሁለት ምርጫዎች ወግ)  97vs 2013 ( ኤሊያስ ዳኝነት)

ቪቫ ኢትዮጵያ

(የሁለት ምርጫዎች ወግ) 97vs 2013
         
ኤሊያስ ዳኝነት

አረረም መረረም መርጠናል!…ይብላኝላቸው መረጥን አልመረጥን ምን እንዳይመጣ ነው ላሉቱ(ወዳጆቼን ጨምሮ)በእኛ ምርጫዎች እነርሱ ይተዳደራሉ።
ፈጣሪ ፈቅዶ በሰጠኝ ዕድሜ….በዘመኔ ሁሉ የሚጠበቅብኝን ሀገራዊ ግዴታዬን ሳልወጣ ባያልፈኝ ደስ ይለኛል።
ካርድ ለመውሰድ በመመላለስ የቀጠነው እግሬ..ሰዓታት ለመቆም አልሰነፈም።ይልቅ የሰልፉን ርዝማኔ ለመርሳት…ታዛቢ የመሰለችኝን ጩቤ ቅልቅል የነበረችውንም ፀሐይ ችላ ለማለት ከስክሪኑ ጀርባ የተሰኘውን የኢቲቪውን ጋዜጠኛ አስገራሚ የምርጫ 97 ትውስታ እና ምስክርነት እያነበብን ሰልፉንም ፀሐዮንም ረስተን መርጠናል።የሚገርም መገጣጠም ነው በአጋጣሚ እያነበብኩ ያለሁት ይህ መፅሐፍ ስለ ምርጫ 97 ያልተሰሙ ያልታዮ ታሪኮችን እና በምርጫው ወቅት  በደራሲው(በጋዜጠኛ አለኝታ እዮኤል)የተዘገቡ ከሕግና ከደንብ ውጪ  በሆነ መልኩ የተቀለበሱ የሕዝብ ድምፆእ እንዲሁም ኢ ፍትሃዊ የሆኑ ክንውኖችን እና ማጭበርበሮችን የዘገበበት ዘገባ ድርጅቱን(Etvን)በሞሉት አዳሪ ካድሬዎች ቀጭን ትዕዛዝ እንዳይተላለፍ የተደረገበትን እና እሱና ለሙያቸው ስነ ምግባር ተገዝተው ያዮትን እውነት ሁሉ የዘገቡትን ምርጥ ጋዜጠኞች የገመገሙበትን ሁኔታ በተመለከተ ይዳስሳል።ከምርጫ 97 ጋር ተያይዞ የነበሩ ቀውሶችን በሙሉ ያነሳል። የኢቲቪን ያልተሰሙ ጉዶች መስማት የፈለገ ይህን መፅሐፍ ፈልጎ ያንብብ!
የሆነው ሆኖ ዛሬ በሁለት ምርጫዎች ወግ መካከል ሁኜ መረጥኩ።ሸጋ ቀን ነበር….ብሩህ ተስፋ ከፊታችን አለን!
እውነት ለማውራት
ቅይጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሉበት…ሀገር የሚያሻግሩ…ረብ ያላቸው…ውሃ የሚያነሱ የቀለጡ የፓርላማ ውይይቶች ለማየትም ለመስማት ቋምጫለሁ።የምርጫውን ውጤት ለመስማት መጓጓቴ እንዳለ ሁኖ ማለት ነው።
ቀጣዮ ጉጉታችን የሁለተኛው የህዳሴው ግድብ ሙሌት ነው።
ለማናቸውም የፓርቲዎቹን ውጤት ባናውቅም
ኢትዮጵያችን ግን  መርጣለችም አቸንፋለች…ይቅርታ አሸንፋለች!
Filed in: Amharic