>
5:31 pm - Friday November 12, 1762

<<የመንግስትን ውሳኔ ትክክል ነው ብለን አንደግፍም...!!! (ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ)

<<የመንግስትን ውሳኔ ትክክል ነው ብለን አንደግፍም…!!!

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ

 ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀ ድርጅትን (ትሕነግን )
ወደ ስልጣን እንዲመጣ መጋበዝ ትክክል ነው ብለን አናስብም። መንግስት የራሱ ጊዜያዊ ስልት ወይንም ታክቲክ ሊኖረው ይችላል።  ከአቅም በላይ የሆነበትን እሱ መንግስት ነው የሚያውቀው። የመንግስት ውሳኔ ከሆነ መቀበል ነው። እኛ ግን የራሳችን ስራ ነው መስራት ያለብን። …የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከመጀመሪያውም ጀምሮ በስም እንጂ በተግባር  ከትሕነግ የተለየ አስተሳሰብ አልነበረውም። የተሻለ ነገር ይመጣል ብለን አልጠበቅንም። ወልቃይት የትግራይ አካል ነው በሚል ግትር አቋም ይዞ ስለነበር ለመንግስትም አሳውቀናል። እንዲያውም  የውስጥ አርበኛ ሆኖ ህዝቡን ባደነት እንዲሰማው ሆኖ የሰራ ኃይል ነው።
….መንግስትም ሆነ የወሰንና ድንበር ኬሚቴው  ለጉዳያችን መልስ ሊሰጥ ይገባል።   ሁመራን እንይዛለን ወይንም ይዘናል እያሉ የውሸት ፕሮፓጋንዳቸውን ለሚነዙት ችግር የለም….የአማራ ህዝብ እስካለ የአማራ ኃይል እስካለ ድረስ  አንድም የትሕነግ ኃይል ወደዚህ ከሞከረ መቃብሩ እዚህ እንደሚሆን አውቀው ሲመጡ ዘመዶቻቸውን ተሰናብተው መምጣት ይኖርባቸዋል።….አትስቡ በቂ ዝግጅት ነው ያለን።
መንግስት በተለይ የክልሉ ጊዜያዊ መንግስት “የተኩስ አቁም ስምምነት ያላደረግነው ለምርጫው ብለን ነው”  ብሎ የሰጠው ምክንያት ትክክል እንዳልነበርና ቀደም ብሎ የተደረገ ስምምነት እንደነበር የሚያሳይ እንደሆነ ነው የሚያሳየን። ከለውጡ ኃይል ጋር እንዳልነበር ነው የማስበው። ስለዚህ  እንደ አማራ አንድ ሆነን በመቆም መታገል አለብን።>>
Filed in: Amharic