>
5:13 pm - Sunday April 19, 4465

የእነ እስክንድር የምስክር አሰማም ሂደት ተቋረጠ ... !!   (ባልደራስ) 

የእነ እስክንድር የምስክር አሰማም ሂደት ተቋረጠ

– ለሐምሌ 29 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ … !!  

ባልደራስ 

… ትእዛዝ ከፌደራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የወጣ ነው በተባለና ማኅተም በሌለው “ከመጋረጃ ጀርባ ምስክሮቼ ይሰሙ” የሚለውን ጥያቄ ደብዳቤ ምክንያት ለዛሬ ከሰዓት በኋላ ምላሽ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕጉ ሮጥ ብሎ በደብዳቤው ላይ ማኅተም አስመትቶ በመምጣቱ ምክንያት ፍርድ ቤቱ የጀመረውን የእነ እስክንድርን የምስክር አሰማም በማቋረጥ ለሐምሌ 29 ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱ እንዲቋረጥ መታዘዙ ተሰምቷል።
… ዐቃቤ ሕግ እስከ ሐምሌ 16 ከነገ ወዲያ ድረስ ምስክር ማቅረብ ካልቻለ የእነ አቶ እስክንድር ነጋን ዐቃቤ ህግ መዝገቡን ለጊዜው በመዝጋት ፍርድ ቤቱ እነ እስክንድርን በመሰናበት መዝገቡ ይዘጋል ተብሎ ሲጠበቅ በዛሬው ዕለት የወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ተቋም ደግሞ ጣልቃ በመግባት ጉዳዩ ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲሄድ አዟል። ሰበር ሰሚው ችሎት ሐምሌ 26 የቀጠረ ሲሆን በ3ተኛው ቀን የሰበር ሰሚው ችሎት የወሰነውን ውሳኔ ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት የእነ እስክንድርን ጉዳይ የሚዳኘው ፍርድ ቤት ለሐምሌ 29 ቀጥሯል።
… እነ አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ ከፍትሕ ሥርዓቱ ምንም ዓይነት መፍትሄ አናገኝም። የእኛ በፍርድ ቤቱ መመላለስ ጥቅም የለውም። ስለዚህ ፍርድ ቤቱ የታዘዘውን ትእዛዝ ተቀብሎ ፍርዳችንን በያለንበት ወኅኒ ቤት ያርዳን ማለታቸው ይታወቃል።
…ለማንኛውም እስክንድር እንደ ጠበል የፍትሕ ሥርዓቱን መፈተሹን፣ ማስለፍለፉንም ቀጥሏል። እስክንድር እስከ አሁን በሕጉ ያምናል፣ በፍትሕም ተስፋ አይቆርጥም። የማይሰበር ብረት የሆነም ሰው ነው። መለስ ዜናዊንም፣ ልጁ ኃይለማርያም ደሳለኝንም፣ አሁን ደግሞ የልጅ ልጁን ዐቢይ አሕመድን በፍትህ አደባባይ ሳይሸሽ እየተጋፈጠ ሚጢጢዬ ድንክ እያደረጋቸው ነው። ከምር እስክንድርማ ይችላል !!
… እደግመዋለሁ። በነገራችሁ ላይ አነ እስክንድር አይከሰሱ የሚል አንድም ሰው የለም። ሁሉም ሰው ከሕግ በታች ነው። እስክንድርም ጭምር። ነገር ግን እየተጠየቀ ያለው ፍትሕ ነው። ፍትሕ። ትክክለኛ ፍርድ፣ እውነተኛ ዳኝነት። ዛሬ በእነ እስክንድር ላይ በሚደርሰው የፍርድ መዛባት ከጓሮ ተደብቀህ የምትስቅ ሁላ ነገ የእጅህን በግልጽ ታገኘዋለህ። ነግ በእኔ ነው። ከጎንህም ታገኘዋለሁ። በራስህ ሲደርስ፣ በቤተሰብ በጓደኛህ ሲደርስ ያኔ ታገኘዋለህ። ይኸው ነው።
Filed in: Amharic