>

ሕግ ካለ ፍትሕ የምትሠራ ከሆነ ዐቃቤ ሕጉ ሊከሰስ ይገባል ....!!! (ዘመድኩን በቀለ)


ሕግ ካለ ፍትሕ የምትሠራ ከሆነ ዐቃቤ ሕጉ ሊከሰስ ይገባል ….!!!

ዘመድኩን በቀለ

* …. ምስክሮች ካልቀረቡ ደግሞ ፍርድ ቤቱ እነ እስክንድርን በነፃ ከማሰናበት በቀር ሌላ አማራጭ የለውም። እናም ይሄ አጣብቂኝ አፍጥጦ የመጣበት ዐቃቤ ሕግ ነው ዛሬ ማኅተም የሌለው የእግድ ትእዛዝ አምጥቶ ተዋርዶ ያረፈደው። 
 
… ከፌደራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የወጣ ነው በተባለ ትእዛዝ… • ዳኛ ሸምሱ ሲርጋጋ… •ዳኛ ዋዚሞ ዋሲራ… • ዳኛ ደረጀ አያና የተባሉ በስም የተጠቀሱ የ3 ዳኞች ስም በተጻፈበት ወረቀት… ነገር ግን ደግሞ ትእዛዙ ማኅተም በሌለው ደብዳቤ ተጀምሮ የነበረው የእነ እስክንድር ነጋ ምስክሮችን የመስማት የፍርድ ሂደት እንዲቋረጥ መታዘዙ ተሰምቷል።
… እስከ ሐምሌ 16 ድረስ የእነ አቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ሂደት እና ምስክሮችን በግልፅ ችሎት የመስማት ሂደቱ ይቀጥል ተብሎ የተወሰነውን ውሳኔ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን በግልጽ ማቅረብ አልችልም። ምስክሮቼ ስማቸው ሳይጠቀስ፣ መልካቸው ሳይታይ፣ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ይመስክሩልኝ ማለቱ የሚታወስ ነው። ከብዙ ክርክር በኋላ ፍርድቤቱ የዐቃቤ ሕግን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ችሎቱ በግልጽ፣ ምስክሮቹም ቀርበው ይመስክሩ በማለት ውሳኔ አሳልፎ በውሳኔው መሠረት መቀጠሉ ይታወሳል።
… ምስክሮቹ እስከ ዛሬ ድረስ አልቀረቡም። ችሎቱም እስከ ሐምሌ 16/2013 ዓም ድረስ ይቀጥላል። እነ እስክንድር ከነ ጠበቆቻቸው ዕለት በዕለት በችሎቱ ይቀርባሉ። ዐቃቤ ሕግና የተባሉት ምስክሮች ግን የሉም። ምስክሮች ካልቀረቡ ደግሞ ፍርድ ቤቱ እነ እስክንድርን በነፃ ከማሰናበት በቀር ሌላ አማራጭ የለውም። እናም ይሄ አጣብቂኝ አፍጥጦ የመጣበት ዐቃቤ ሕግ ነው ዛሬ ማኅተም የሌለው የእግድ ትእዛዝ አምጥቶ ተዋርዶ ያረፈደው።
… በፍርድ ቤቱ እና በእነ እስክንድር ጠበቆች አማካኝነት ዐቃቢ ሕግ ትክክለኛ መረጃ ወይም ደብዳቤ ባለማቅረቡ ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበርም ለመረዳት ተችሏል። ሕግ ካለ ፍትሕ የምትሠራ ከሆነ ዐቃቤ ሕጉ ሊከሰስ ይገባል ነው የሚሉት የሕግ ባለሙያዎቹ። ለማንኛውም እስክንድር እንደ ጠበል የፍትሕ ሥርዓቱን መፈተሹን፣ ማስለፍለፉን ቀጥሏል። በሕጉ ያምናል፣ በፍትሕ ተስፋ አይቆርጥም፣ የማይሰበር ብረት የሆነ ሰው ነው። መለስ ዜናዊንም፣ ልጁ ኃይለማርያም ደሳለኝንም፣ አሁን ደግሞ የልጅ ልጁን ዐቢይ አሕመድን በፍትህ አደባባይ ሳይሸሽ ሚጢጢዬ ድንክ እያደረጋቸው ነው። ከምር እስክንድር ይችላል !!
… ፍርድ ቤቱ ከሰበር ሰሚ ችሎት የተላከ የተባለውን ደብዳቤ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ ዘጠኝ ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል። የአዲስ አበባ ህዝብ በችሎቱ የሚሰጠውን ውሳኔ ለመስማት በጉጉት በስፍራው ላይ መጠባበቁም ተነግሯል። ዘጠኝ ሰዓት ልደታ ፍርድ ቤት አለ ነገር። ፍትሕ ትፈተናለች። ወይ ትወድቃለች። ወይ ደግሞ ታልፋለች። 9 ሰዓት የሚወሰነውን ውሳኔም ይዤላችሁ ለመቅረብ እሞክራለሁ። ጠብቁኝ።
… በነገራችሁ ላይ አነ እስክንድር አይከሰሱ የሚል አንድም ሰው የለም። ሁሉም ሰው ከሕግ በታች ነው። አይቀጡ፣ አይከሰሱ፣ አይጠየቁ ያለ የለም። እነሱም አላሉም። ነገር ግን እየተጠየቀ ያለው ንፁህ ፍትሕ ነው። ፍትሕ። ትክክለኛ ፍርድ፣ እውነተኛ ዳኝነት። ዛሬ በእነ እስክንድር ላይ በሚደርሰው የፍርድ መዛባት የምትስቅ ሁላ ነገ የእጅህን ታገኛለህ። ከጎንህ ታገኘዋለሁ። በራስህ ሲደርስ፣ በቤተሰብ በጓደኛህ ሲደርስ ታገኘዋለህ። ለማንኛውም የሰበር ሰሚ ችሎቱ የእግድ ደብዳቤም ከታች ተያይዟል። ለታሪክም ይቀመጥ።
ፍትህ ለ እስክንድር !
ፍትህ ለስንታየሁ !
ፍትህ ለአስቴር ! 
ፍትህ ለአስካለ !
Filed in: Amharic