>

ልኩን ያለፈው የህወሀት የንቀትና የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ...!!! (አሳዬ ደርቤ)

ልኩን ያለፈው የህወሀት የንቀትና የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ…!!!

አሳዬ ደርቤ

– የትሕነግ ልጆች ለኦሮሞ ሕዝብ ያላቸው ንቀት እጅግ የወረደ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አገር መምራት የማይችል ሕፃን አድርገው ‹‹አቡሽ›› እና መሽረፈት›› እያሉ ይሳለቁበታል፡፡
– ኢታማዦሩን ‹‹በደርግ ዘመን ወደ ትግራይ ከዘመተ በኋላ አንድ ጥይት ሳይተኩስ የተማረከ ነው›› እያሉ ያናንቁታል፡፡ ኢታማዦር ለመሆን ይቅርና እንደ ወታደር ጦርነት ላይ ለመዝመት ብቁ አይደለም›› በሚል ፕሮፖጋንዳ ሥሙን ያጠፉታል፡፡
– ሌ/ጄ ባጫ ደበሌን  ምርኮኛ ከመሆን የዘለለ እጣ ፈንታ እንደሌለው ይነግሩኻል፡፡ ማዕረጉን ገፍፈው ንቀታቸውን በሚገልጽ ቅጽል ሥም ይጠሩታል፡፡ ብቻ በአጠቃላይ ‹‹ኦሮሞ አዋጊም ሆነ ተዋጊ መሆን አይችልም?›› ይሉሀል…
ዛሬ ደግሞ  በእነ አሉላ ሰሎሞን የሚመራው የሳይበር አሸባሪ ከአፋር፣ ከአማራ፣ ከሲዳማ፣ ከደቡብ፣ ከሶማሌ፣ ከጋምቤላ፣ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ከዘመተው ልዩ ሃይል በተለየ መልኩ ከኦሮሚያ የዘመተውን ልዩ ሃይል በቅጽበት ውጊያ መደምሰሳቸውንና መማረካቸውን እየገለጹ ነው፡፡
ጦረኝነትና ጀብደኝነት በዘር የሚተላለፍ ይመስል እራሳቸውን ብቻ እንደ ጦረኛ የሚቆጥሩት የትሕነግ ትምክህተኞች ጀግናውን የኦሮሞ ሠራዊት ከምርኮኛ ተርታ መድበው ‹‹ተው ይቅርብህ እያልነው የዘመተውን የኦሮሞ ሠራዊት በቅጽበት ውስጥ ሟችና ምርኮኛ ስላደረግነው ቄሮ ሆይ ከዚህ ተምረህ አርፈህ ተቀመጥ›› የሚል መልዕክት እያስተላለፉ ነው፡፡
ሆኖም ግን ይህ የንቀት ፕሮፖጋንዳቸው መላውን የኦሮሞ ወጣት ለውጊያ የሚያነሳሳ እንጂ ተሸናፊ ስነ ልቦናን የሚያወርስ አይደለም፡፡ የሚነዙት የውሸት ሰበር ዜናም ለእራሳቸው የሚሰጡትን የተጋነነ ግምትና ለኦሮሞ ያላቸውን ንቀት ከመግለጽ የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡
ምክንያቱም በአድዋም ሆነ በማይጨው፣ በካራማራም ሆነ በባድሜ ጦርነት ላይ ኦሮሞ ከመዋጋት በተጨማሪ ማዋጋት የሚችል ጦረኛ ሕዝብ መሆኑን ያሳየ ጀግና ሕዝብ ነው፡፡
በጣሊያን ጊዜ እንኳን ያለውን ታሪክ ብንመለከት ባንዳው ራስ መንገሻ ጉግሣ ጣሊያንን በእልልታ ተቀብሎ አገሩ ላይ ሲዘምት በሰላሌው ጀግና ‹‹አቢቹ›› የሚመራው የጎበዝ አለቃ ግን ጣሊያንን እና ባንዳን ሲያግለበልባቸው ነበር፡፡
በመሆኑም የኦሮሞ ሕዝብ ልክ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁሉ ተዋግቶ ከሚያሸንፈውና ለአገሩ መስዋዕት ከሚከፍለው አርበኛ ተርታ የሚሰለፍ እንጂ የውጭ ወራሪ በመጣ ቁጥር የሚበነድድ ወይም ደግሞ ሳይዋጋ የሚማረክ አይደለም፡፡
ሐቁ ይሄ ቢሆንም ታዲያ እራሳቸውን ከግሪክ አማልክቶች ተርታ የሚመድቡት እኒህ የእፉኝት ልጆች በአገር መሪነትም ሆነ በጦር መሪነት ለሚታወቁት የኦሮሞ ልጆች ያላቸው ንቀት በጣም የሚያስገርም ነው፡፡ ከሰሞኑም አፈር ድሜ ሊያስበላቸው ወደ ውጊያ የዘመተውን የኦሮሞ ሠራዊት ከሌሎች ወንድሞቹ ለይተው ‹‹ማርከነዋል›› እና ‹‹ደምስሰነዋል›› ማለታቸው ይሄን ንቀታቸውን የሚገልጽ ነው፡፡
የሚገርመው ነገር ታዲያ እንደ ግርማ ጉተማና ብርሐነ መስቀል ያሉ የኦሮሞ ኤሊቶች ከኦሮሞ የወጡ የአገርና የጦር መሪዎችን ከሚደግፈው ዜጋ ይልቅ ከሚያንቋሽሸው አካል ጋር አብረው እየሠሩ መሆናቸው ነው፡፡ ትሕነጎች ‹‹ዐቢይ ይውረድ›› ሲሉ ‹‹ዳውን ዳውል›› የሚሉ፣ የኦሮሞ አዋጊዎችን ሲያናንቁ ‹‹አዎ እኛ እኮ ምርኮኞች እንጂ አዋጊዎች መሆን አንችልም›› እያሉ ስለ እራሳቸው የሚመሰክሩ፣ ‹‹የኦሮሞን ጦር ማረክነው›› የሚል ፕሮፖጋንዳ ሲነዙ ‹‹እሰይ የእኛ ጀግኖች›› እያሉ የሚያደንቁ መሆናቸው ነው፡፡
አግራሞት የሚጭረው… ህዝቅኤልና ግብረ አበሮቹ ዐቢይን አውርደው ደጺን፣ ጀኔራል ብርሐኑን ጥለው ጀኔራል ጻድቃንን፣ ፣ ሌ/ጄ ጫላ ደበሌን አስወግደው ጀኔራል ሐጎስን፣ የኦሮሞ ልዩ ሃይልን አስማርከው የትሕነግ ጦርን በኢትዮጵያና በኦሮሞ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ለመጫን የሚንደፋደፉ ገረዶች ከኩሩውና ከጀግናው የኦሮሞ ሕዝብ አብራክ መፍለቃቸው ነው፡፡
Filed in: Amharic