>

የህወሓት ታጣቂዎች ኤርትራዊያን ስደተኞችን መግደላቸውን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ!!!

የህወሓት ታጣቂዎች ኤርትራዊያን ስደተኞችን መግደላቸውን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ!!!

የስደተኞችና ከስደት  ተመላሾች  ጉዳይ  ኤጀንሲ

*… የስደተኛ ጣቢያ ንብረትን ለወታደራዊ አገልግሎት ማዋላቸው፣ 
*… በጣቢያዎቹ ውስጥ ከባድ መሳሪያ መትከላቸውና ሌሎች ወንጀሎችን እየፈጸሙ መሆናቸው ተገለጸ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ኤርትራዊያን ስደተኞች ባሉባቸው ጣቢያዎች በመግባት ስደተኞችን መግደላቸውን፣ የጣቢያውን ብበረት በመዝረፍ ለወታደራዊ አገልግሎት  ማዋላቸውን፣ ስደተኞችንም አግተው መያዛቸውን፣ በጣቢያው ውስጥ መሳሪያ መትከላቸውን እና ሌሎች ወንጀሎችን እየፈጸሙ እንደሆነ ተገለጸ።
የስደተኞችና ከስደት  ተመላሾች  ጉዳይ  ኤጀንሲ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባደረሰው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ህወሃት የስደተኛ መጠለያ   ጣቢያዎች   ወዳሉባቸው  አካባቢዎች   መግባቱን   ተከትሎ  እስካሁን  ድረስ  ቢያንስ   ስድስት  ስደተኞች እንደተገደሉ  የሚያሳዩ መረጃዎች  ተገኝተዋል።
ዓለም  አቀፉን  የሰብዓዊ  መብት  ሕግን  በመጣስ  የህወሃት  ታጣቂዎች በስደተኛ መጠለያ  ጣቢያዎች  ውስጥ ከባድ መሣሪያዎችን  የተከሉ መሆናቸውን የገለጸው ኤጀንሲው፤ ቀጣይነት ያለው የታጣቂ እንቅስቃሴ እና አልፎ አልፎም የተኩስ እሩምታ በማሰማት  ላይ ይገኛሉ ብሏል፡፡
በተጨማሪም  ለሰብአዊ አገልግሎት እንዲውሉ የተዘጋጁና የተቋቋሙ ጤና ጣቢያዎችን ጨምሮ አምቡላንሶችን እና መሰረተ ልማቶችን ለወታደራዊ አገልግሎት እያዋሉ እንደሆነ ያስታወቀው ኤጀንሲው፤   በዚህም ምክንያት ቢያንስ ሁለት ስደተኞች በጤና አገልግሎት እጥረት መሞታቸውንና እናቶችም አስጊ በሆነ ሁኔታ እየወለዱ ይገኛሉ ብሏል።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም መጋዘኖችን ጨምሮ የኤጀንሲያችን እና የሌሎች አጋሮች ንብረቶች ተዘርፈዋል ያለው ኤጀንሲው፤ ስደተኞች ለጦርነቱ የሚውል በዓይነትና በገንዘብ መዋጮ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ይገኛሉ ብሏል።
በተጨማሪም ስደተኞቹ ከግጭቱ አካባቢ ለመልቀቅ የሚያደርጉት ጥረት ሁሉ በህወሓት የተከለከለ ነው፤ የሚገኙበት ሁኔታ ከእገታ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ የሚመላክቱ ሁኔታዎች አሉ ያለው ኤጀንሲው፤ በተቃራኒው ስደተኞችን በጅምላ ወዳልታወቁ ቦታዎች በኃይል የማጓጓዝና እና የተወሰኑትን በህዳር ወር ችግሩ እንደተከሰተ በራሳቸው በህወሃት ታጣቂዎች ጥቃት ደርሶባቸው ወደ ተዘጉት ህጻፅና እና ሽመልባ መጠለያ ጣቢያዎች እንዲዛወሩ የማድረግ ሙከራዎች እንዳሉም አስታውቋል።
የኤጀንሲው መግለጫ ሙሉ ቃል ከስር የተያያዘውን ሊንክ ተጭነው ያገኙታል።
Filed in: Amharic