>

የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በንጹሀን አማራዎች ላይ ተኩስ በመክፈት በርካቶችን ሙትና ቁስለኛ አድርጓል..!!! (አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ)   

የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በንጹሀን አማራዎች ላይ ተኩስ በመክፈት በርካቶችን ሙትና ቁስለኛ አድርጓል..!!!
 
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ

የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በሆሮ ጉድሩ ዞን አሙሩ ወረዳ ዲንጋም ጮምቤ ቀበሌ እድገቴ አካባቢ እና በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ አሹ ቀበሌ በአማራዎች ላይ ተኩስ መክፈቱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
አሚማ ከአካባቢው ነዋሪዎች ለማጣራት
 እንደሞከረው የተደራጁ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአማራዎች ላይ ተኩስ በመክፈታቸው በርካቶች ከመኖሪያ ቤታቸው እየሸሹ ወደ ጫካ እየገቡ ነው፤ የሚከላከልላቸው የፀጥታ አካልም ለማግኘት አለመቻላቸው ተጠቁሟል።
በአሙሩ ወረዳ ዲንጋም ጮምቤ ቀበሌ እድገቴ አካባቢ ሚሊሻዎች ለመከላከል ጥረት እያደረጉ መሆኑ ቢገለፅም ከአቅማቸው በላይ መሆኑ ተጠቁሟል።
በኪረሞ ወረዳ አሹ ቀበሌ ግን ከአሁን ቀደም በርካታ ሚሊሻዎች የሽብር ቡድኑ ሰለባ በመሆናቸውና ለመንግስት ትጥቅ የመለሱም በመሆናቸው ነዋሪዎች ራሳቸውን ለማትረፍ እየሸሹ ነው ተብሏል።
የሽብር ቡድኑ ተኩስ የከፈተው በተናበበ መልኩ ሲሆን በኪረሞ ዛሬ ሀምሌ 24 ቀን 2013 ከቀኑ 8 ሰዓት፣ በአሙሩ ወረዳ እድገቴ ደግሞ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል።
ነዋሪዎች በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ቢገልፁም ማንና ምን ያህል እንደተጎዳ ግን ለጊዜው ለማወቅ አልቻሉም።
የሚመለከተው የመንግስት አካል በአስቸኳይ ደርሶ ማህበረሱን ከበለጠ ጥቃት እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል።
Filed in: Amharic