>

“የጂቡቲ አዲስ አበባን መስመር በመዝጋት  ጉረሮ እናንቃለን፤  አዲስ አበባም እንገባለን”  የህወሀት የቁም ቅዠት...!!! (ነአምን ዘለቀ)

“የጂቡቲ አዲስ አበባን መስመር በመዝጋት  ጉረሮ እናንቃለን፤  አዲስ አበባም እንገባለን” 
የህወሀት የቁም ቅዠት…!!!
ነአምን ዘለቀ

 

ኢትዮጵያን ዳግም እንገዛለን፣ ይህን  ካልቻልን አፍርሰን በኢትዮጵያ መቃብር ላይ የትግራይን ሪፓብሊክ እንመስርታልን የሚል ቅዠት የተለከፉት የናዚ የወያኔ ትግሬ ፋሽቶች ግበአተ መሬት በአፋር ክልል እየተፈጸመ ነው። 
ጀ/ል ጻድቃን የወያኔ ትግሬዎች ስራዊት መሪ ከሙትና ምርኮ  የተረፉ የተወሰኑ የህወሃት ጀነራሎችና ኮሎኔሎች አሉት። “የጂቡቲ አዲስ አበባን መስመር በመዝጋት ኢትዮጵያን ጉረሮ እናንቃለን (chock—off) ፣ ከዚያም አዲስ አበባ እንገባለን” ሲል ለቢቢሲ በሰጠው ቃለ ምልልሱ  ተደምጦ ነበር። ይህን በፎከረ በሶስት ሳምንት ወደ አፋር የላከው ብዙ መቶ  የትግራይ ሕጻናት የሚገኙበት ሶስት ክፈለ ጦር በአፋር ልዩ ሃይልና በመከላከያ ሰራዊቱ ጀግንነት በልዩ ልዩ ዞኖች ትልቅ ሽንፈቶች ደርሰውበት ሙትና ምርኮ እየሆነ መሆኑ እየተረጋገጠ ነው።
የህወሃት የረጅም ጊዜ ወዳጅና ዛሬ ደግሞ  በአለም አቀፍ ደረጃ ዋና ፕሮፓጋንዲስት የሆነው የተፍትስ ዩኒቨርሲቲ አሌክስ ዲዋል በቢቢሲ በጻፈውና በተናገረው ጀ/ል ጻድቃንን ለማግዘፍ፣  ትልቅ የአፍሪካ ሚሊታሊ ስትራቴጄስት ጀነራል አድርጎ በማጀገን፣ ብሎም  አለምን ለማወናበድ የኢትዮጵያን ሰራዊትና አዛዦቹን አኮስሶና አሳንሶ ለማቅረብ የተሞከረበት ብዙም ርቀት ሳይሄድ አፈር እየበላው ነው።
=======
ከዛሬ ሳስት አመት በፊት በማህበራዊ ሚዲያ የወጣው ጽሁፍ ፦  በኤርትራ ጦርነት ወቅት ጀ/ል ጻድቃን ፣ በወቅቱ ከላይ እሰከታች 90% በወያኔ ትግራይ ዱውይ የጦር መኮንንኖች ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊት ኢታማጆች ሹም ነበር።  ከኤርትራ ጋር በተደረገው የመጀመሪያ ዙር  ውጊያዎች ተደጋጋሚ ሽንፈቶች ሳቢያ  እምባ አውጥቶ አልቅሶ ነበር።
=====================
የህወሓት ትግራይ  ጸረ ኢትዮጵያ ባንዳዎች አይናቸውን በጨው የታጠቡ ጉድ የማያልቅባቸው ጉዶች ናቸው!! ሰሞኑን ወያኔዎች፡ የነሱ ቱቦዎች፣ እንዲሁም የህሊና እና የታሪክ ድውያን አሸርጋጆቻቸው፡ በቢቢሲ ሃርድ ቶክ በሰጠሁት ቃለ ምልልስ “ባድመ ለኤርትራ ተወስኖአል” ማለቴን ተከትሎ አንጀታቸው እርር ብሎ ተቃጥሏል። የ “ግንቦት 7” ነአምን ዘለቀ የብሄራዊ ጥቅም “National Interest” አያውቅም፣ ባድመን ለኤርትራ አሳልፎ ሰጠ በሚል ያዙኝ ልቀቁኝ በየድረ ገጾቻቸውና ሶሻል ሚዲያ  የሚሞነጫጭሩትን ጓደኞቼ ልከውlኝ ተመለከትኩ።   አጉል አውቀን አብቅተናል በሚሉ ግብዞች የነሱ ጫጩቶች ደግሞ የነሱን ወስደው ማስተጋባትም ተያይዘውታል።
የህወሓት መሪዎች “አክሱም ለወለይታው ምኑ ነው ላሊበላስ ለጉራጌው?፣ ኢትዮጵያ አልነበረችም ፣ ተረት ተረት ናት፣ ሚኒሊክ በሳንጃ የሰበሰባትን እኛ ለመጠበቅ ሃላፊነት የለብንም” ሲሉ አልከረሙም ወይ? የኢትዮጵያን ህዝብ ቅስም   ለመስበር ሁሉንም  ድንጋይ የፈነቀሉት እነሱ አልነበሩም ወይ?
”ሉኣላዊነት ተደፈረ” በሚልም ሲያጠቁትና ሲያንክዋስሱት የቆዩትን የኢትዮጵያዊነትን ካባ  አጥልቀው ህዝብን ቀሰቀሱ። ባድመ በሻቢያ ተወረረ በሚል ለባዶ ደረቅ መሬት 96 ሺ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንን  ደም፣አጥንትና፣ ህይወት የገበሩ እነሱ። አስታውሱ በወቅቱ ኢታማጆች ሹም የነበረውን ጀ/ል ጻድቃንን እምባ እውጥቶ ባስለቀሰ በድውያን የህወሓት ጀነራሎች የተመራ ፈንጂ እሰረጋጭ የበርካታ ዙር የእልቂት ዘመቻዎች ብዙ ሺ ኢትዮጵያዊያንን አሰጨረሱ።  ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች- የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የጉራጌ፣  የጋምቤላ የሌሎች ብሄር ልጆች– እንዲሁም ለውርደትና ለልመና የዳረጉትን የቅድሞ ሰራዊት አባላትና ምርጥ ጀነራሎች በአስርቱ ሺዎች በድረሱልን ልመና አምጥተው አዘመቱና ጦርነቱ እንደምንም በ11ኛ ሰአት ወደ አለቀ።  ከጦርነቱ በሁላ ያ የታሪክ አተላ ሟቹ የውያኔ መሪ “ ኣባታቸውን የሞተባቸውን ማን ያመጣቸው? አባሩልኝ” በማለት  ለጦርነቱ ከፍተኛውን አስተዋጾ ያደረጉትን የቀድሞ ሰራዊት አባላትን ወያኔዎች በድጋሚ አባረሩ። ታሪክን ለማንረሳ፣ የወጋ ቢረሳ….. ነውና።
አልጀርስ ላይ የማይቀለበስ “Binding” ስምምነት ሄደውም ተፈራረሙ። እኛ አይደለንም የፈረምነው፣ ወያኔዎች እንጂ፡፡ ከአልጀርሱ ስምምነት በኋላ እነሱ በተፈራረሙት “የማይቀለበስ” ስምምነት መሰረት  አለም አቀፍ የድንበር ኮሚሽን ለኤርትራ ፈርዱን ሰጠ፣ “ባድመ የኤርትራ ነሽ በማለት ፍርዱን ሰጠ” ። እኛ አልተፈራረምን፣ እነሱ እንጂ!። እንደ  ስዩም መስፍን  በአደባባይ ዋሽተንም “ለኢትዮጵያ ተፈረደ” ብለን የኢትዮጵያን ህዝብ ሰልፍ ያስወጣንም  እኛ አይደለንም። እነሱ እንጂ!
ብዙ ብዙ ማለት ቢቻልም እሲቲ መለስ ብለን ጥቂቶቹን ብቻ የታሪክ ሀቆችን  እንቃኝ። ከፈረንጅ ጋር ፈረንጅ፣  ከጋዳፊ ጋር ሲገናኙ የየመን አረብ፣ ሲያድ ባሬ ኢትዮጵያን  እስከ አዋሽ፡ ድሬ ደዋ ድረስ ወራሪውን ጦር አስገብቶ፣ ኢትዮጵያ ተወራ መለስ ዘናዊና የወያኔ መሪዎች ነበሩ በሶማሌ ፓስፖርት እየተጠቀሙ፡ ሞቃዲሾ ሲመላለሱና ሲዝናኑ የነበሩት። እነሱ ነበሩ  ወይስ እኛ   ከግብጹ፣ ከሶሪያ፣ ከኢራቅ፣ ወዘተ “ደርግን ለመዋጋት” ከምድረ አርብ ጋር የተመሳጠሩ ፣ ብዙም እርዳታ ያገኙ እነሱ አልነበሩምን? ስለኢትየጵያ “ብሄራዊ ጥቅም” የተደረገ መሆኑ ነው? በጣም አስቂኝ አይሆንም?
ለኤርትራም ከኤርትራውያን በላይ የተዋጋን እያሉ አረፋ አይደፈቁ ሲጎማለሉ የነበሩት እነ የህወሓት የጡት አባት እነ ስብሀት ነጋ አይደሉም ወይ? የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር የነበረው አምባሳደር ሔርማን ኮሂን በአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ተጠይቆ እነመሰከረባቸው  አሰብን ከኤርትራውያን ጋር መደራደር ሲችል ፣ ኢትዮጵያን የለባህር በርና ወደብ አልባ ያደረገው ፣ በኋላም ይህን  የወያኔዎች ስትራቴጂካዊ ድድብና የሚያረጋግጥ ግዙፍ ወንጀል ለመደበቅ ለኢትዮጵያ “ብሄራዊ ጥቅም”እንዲሁም ደህንነት  ወሳኝ ከሆኑ አንዱ የሆነውን የወደብና የባህር በር አስፈላጊነት በማንኳሰስ  “ወደብ ሸቀጥ ነው!፣ ቀይ ባህርንም ግመሉን ያጠጣበት” በማለት ሲመጻደቅብን ከርሞ ህይወቱ ያለፈችው የወያኔው ትልቁ ጉድ መለስ ዜናዊ እንጂ እኛ አልነበርንም!
ባንዳ፣ ከሃዲው፣ሃገር ሻጩ፣ ማን እንደሆነ እኮ ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ አያጣውም። ወያኔዎች 60 ሺ የትግራይ ልጆች መስዋእትነት ከፈሉ በማለት ነጋ ጠባ ያቅራራሉ። ለትግራይ ሪፑብሊክ ግንጠላ እንጂ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት አልተሰው። ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለፍትህ ፣ ለመብት፣ ለእኩልነት ተሰውተው ቢሆን እንኳን  እሰየው እንል ነበር። ያ ቢሆንማ ለ27 አመት የወያኔ ትግራዮችን የበላይነት በምድረ ኢትዮጵያ አያንግሱም ነበር።  እነሱ ግን እኛ መስዋእትነት ስለከፈልን “እኛ ወርቅ ነን”፡ ሌላው ኦሮሞው፣ አማራው፣ ጉራጌው፣ ጋምቢላው፣አፋሩ ፣ ወዘተ  ጨርቅ ስለሆነ ራሱ ላይ የወርቅ ዘውድ ሆነን እየዘረፍነው፣ እየገደልነው፣ በሌላው ኢትዮጵያዊ  ኪሳራ የህውሓት ትግራውያንን  የበላይነት እናስቀጥላላን ብለው 27 አመታት እንደ መዥገር ተጣብቀው የኢትዮጵያን ህዝብ ደምና አንጡራ ሃብት የሚመጠምጡ  እኛ ሳንሆን እነሱ እኮ ናቸው!
ይህ የበላይነት ካላስቀጠልን ደግሞ ኢትዮጵያን ብትፈራርስ ቁብም እንደማይሰጣቸው በአደባባይ የሚነግሩን እነሱ አይደሉም ወይ? ኪዚያም አልፈው ኢትዮጵያን እናፈርሳለን በማለት የኢትዮጵያን ህዝብ የአገር የመበታተን አደጋ ስጋት ወስጥ ለመጨመር ያለሀፍረትና ይሉኝታ በአደባባይ መሪዎቻቸው አነአባይ ጸሃይ፣ ስዩም መስፍን በቅርብ ወራት እንኳን በአደባባይ ሲናገሩ አልነበሩም ወይ ?  እኛ እይደለንም ይህን ያልነው! ከጎንደር፣ ከወሎ መሬት የዘረፉ እነሱ!፣ ለባእዳን አረብ፣ ለሱዳን መሬት ቆርጠው የሚሰጡ፣ የሚሸነሽኑ እንሱ!እኛ እይደለንም።
በምን ስሌት ነው ታዲያ እነሱ የ”ኢትዮጵያ ብሂራዊ ጥቅም” ዘብ እና ጠበቃ ሆነው ለመቅረብ የሚሞክሩት?። ከመቼ ወዲህ? ታሪካቸው እኮ ይመሰክራል!። አሁን መልሰው “ “ የብሄራዊ ጥቅም የማያውቁ ይሉናል” ባድመ ለሚባል ለኢትዮጵያ ጥቅምም፣ እድገትም ፣ ህልውናም፣ ደህንነትም ምንም ስትራቴጂካዊ   ዋጋ የሌለው ምድረ በዳ መሬት አንወጣም በማለት ግግም ብለው የምድር ጉድ ድውያን፡ ኢትዮጵያን እያደሙና፣ እየዘረፉ፣ እየደፈሩና ፣እንደከብት እያረዱ፡ ስለኢትዮጵያ “ብሄራዊ ጥቅም” ሊሰብኩን የሚሞክሩ የውቅሮ ብልጣ ብልጦች ቱሪስት መብላት ይችልሉ! በዚህ የሚበላ ኢትዮጵያዊ ካለ የበስተኋላውን በፍጹም ያማያውቅ ሌላ ፕላኔት ላይ ያለ ብቻ ፍጡር ይመስለኛል።
የወያኔ ጸረ ኢትዮጵያ ባንዳዎች አይናቸውን በጨው የታጠቡ ጉድ የማልቅባቸው ጉዶች ናቸው!!።እኔ የሚገርመኝ የወያኔ የምድር ጉድ ነፈስ በላ ፋሽቶች ሳይሆኑ ምንም ታሪክ ሳይሰሩ የነሱን ውዥንብር የሚያስተጋቡ ሰሞኑን ውር ውር የሚሉ ድውያን አሸርጋጆች ናቸው።
Filed in: Amharic