>
5:13 pm - Friday April 20, 1753

አብን ሚናውን ይለይ ይድረስ ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ወንድወሰን ተክሉ

አብን ሚናውን ይለይ: ይድረስ ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)

ወንድወሰን ተክሉ

ጉዳዩ ፦ ሚናውን እንዲለይና ብሎም የወሎን ሕዝብ በተመለከተ ኋላፊነት እንዲወስድ ስለመጠየቅ
*** ***
*…. አብን በአሰቸኴይ ይህንን ኋላፊነት ወስዶ ወደ ስራ እንዲገባ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መሪ ረ/ፕ በለጠ ሞላ ወሎ ባለው አማራዊው ሕዝባችን ላይ ያንዣበበውን አሰቃቂ የርሃብ አደጋን በመግለጽ ደረጃ የተላለፉትን ሶስት ተከታታይ መልእክቶችንና ጥሪዎችን አድምጠናል ተመልከተናልምምል።
የችግሩ ስፋት ጥልቀትና እጅግ አስጨናቂነትን ስፍራው ድረስ ሄዶ በአካል ተገኝቶ በመመልከት እውነታውን ከገለጽልን ከድርጅታችሁ መሪ በኩል በተገለጸው  ተከታታይ መረጃ መሰረት ችግሩ ወይም አደጋው የሚሊዮን አማሮችን ህይወት በአደጋ ላይ የጣለ አደገኛና ብሎም መጠነ ሰፊ መሆኑን ድርጅታችሁ መረዳት ተችሎታል ብዬ አምናለሁ።
ይህ የድርጅታችሁ እይታዊ መረዳታችሁ መጠነ ሰፊ የሆነውን የርሃብ አደጋ ይዘት ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን የመንግስትንም ሚና -ማለትም- የክልሉም ሆነ የፌዴራሉን መንግስት ሚናን ሙሉ በሙሉ ቸልተኝነት አድሎአዊነትንና ብሎም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነውን የሰው ሰራሽ ርሃብ ፈጣሪነቱን የተረዳችሁ ናችሁ ብዬ አገምታለሁ።
ይህንንም እይታዊ መረጃን መሰረት በማድረግ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በድርጅቱ መሪ በኩል በተናጥል እየተስተጋባ ያለውን የወሎን ችግርና መፍትሄዎቹን የማቅረብን ግላዊ ጥረትን ብድግ አድርጎ በመቀበል ድርጅታዊ አጀንዳው አድርጎት ይንቀሳቀሳል ብለን ብንጠብቅ ብንጠብቅ ተግባራዊ እርምጃን ድርጅታችሁ  ሲጀመር ማየትም ሆነ መስመት ባለመቻሉ በእጅጉ ለማዘንና ብሎም ይህንን አስቸኴይ ግልጽ ጥያቄን ለመጻፍ አስገድዶናል።
አብን እንደ አንድና ብቸኛ የአማራ ህዝብ ድምጽና ተወካይ ድርጅትነቱ ይህንን አማራዊ የሆነን የወሎን ሰው ሰራሽ ርሃብ አደጋን እና ብሎም  ባለፈው ነሀሴ ወር ውስጥ በወለጋ በግፍ በተጨፈጨፉ ከ300 በላይ አማራዊያን ጉዳይ ላይ እያሳየን ያለው አቌም ተቆርቌሪነትና ብሎም ችግሮቸን በመግለጽና ለመፍታትም ከመጣር አኴያ እጅግ ዳተኝነት ልክ ስልጣን ላይ እንዳለው ኦህዴድ/ብአዴን ብልጽግና መራሹ ጸረ አማራ መንግስት  ዝምታን መምረጥ ፈጽሞ ያልተጠበቀና ሊሆንም እማይገባን እንዝህላልነትን ድርጅታችሁ አሳይቷል።
ድርጅታችሁ እንደ የአማራ ህዝብ ድምጽነቱና ተወካይነቱ እራሱን ከብአዴን የተለየና በትክክልም ለአማራ ህዝብ ጥቅምና ህልውናን የቅድሚያዎች ሁሉ ቅድሚያ ሰጥቶ ለመታገል የተቌቌመ አማራዊ ድርጅት ከሆነ አብን በአስቸኴይ ይህንን የዳተኝነት የእንዝህላልነትንና የቁጭ ብሎ መንግስት ሆይ ህዝባችንን እርዳ አይነት ጨዋታን እርግፍ አድርጎ በመተው በወሎ ህዝብ ላይ ያንዣበበውን የርሃብ እልቂትን ለመከላከል እርዳታ የማሰባሰቡን የመሪነትን ሚና ተቀብሎ ዘመቻውን መምራት አለበት ብዬ አምናለሁ።
ይህ ማለት ዛሬ በአንዳንድ የድርጅቱ አመራሮች መንግስት ለወሎ ህዝብ የአስቸኴይ ግዜ የምግብና መድሃኒት እርዳታን እባክህ አድርስልን እየተባለ የሚስተጋባውን የአቅምና ስልጣነቢስ የይስሙላን መልእክት ማስተላለፍን እርግፍ በመተው ድርጅቱ አጠቃላይ የውሎን ጉዳይ ዋና አጀንዳው በማድረግ ህይወት የማዳን ዘመቻውን እራሱ መንግስትን ሳይጠብቅና ሳይለምን መፈጸም ይገባዋል ማለት ነው።
አብን አንድ ንኡስ ኮሚቴ(ግብረ ኋይል ) ፈጥኖ በማቌቌም ውሎ ሳያድር አንድ ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው – ማለትም የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የውጭ ሚዲያዎችን፣በአዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሮችን ኮርዲፕሎማቲኮችን ፣የሰብዓዊ  መብት ተሟጋች ድርጅቶችን፣የአደጋጋና ድርቅ ማስወገጃ ኮሚሽንን እና መሰል ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት ባሉበት አጠቃላይ የችግሩን ስፋት ጥለቅትና የሚፈለገውን የእርዳታን መጠን በይፋ ለዓለም በመግለጽ ህይወት የመታደግ ዘመቻውን በመሪነት ይዞ መምራት ይገባችኋል ብሎ ነው መላው አማራ ከእናነተ እየጠበቀ ያለው።
እናም በፍጥነት ወደ ተግባራዊ ስራ እንድትገቡ ስንል ጥሪያችንን እናቀርባለን።
፠ የመልእክቱ መቌጫ- አብን ከአማራ ህዝብና ከብልጽግና መራሹ ስርዓት መካከል ሚናውን በግልጽ  መለየት ያለበት ዛሬ ነው።
አብን በብአዴን መራሹ የአማራ ክልላዊ መንግስት በኩል የታወጀውን የህልውና ክትተ አዋጅን ሙሉ በሙሉ ደግፎ  ድርጅቱ  ሁለንተናዊ አትኩሮቱን  ሙሉ በሙሉ በጦርነቱ ላይ ማድረጉ ይታወቃል። ይህንን የድርጅቱን አቌም አብዛኛው የአማራ ህዝብ በአዎንታዊ እይታው እንደደገፈውም ይታወቃል።  የአብን የህልውና ክተተ አዋጁን መደገፍና ብሎም ሁለንተናዊ አትኩሮቶን በጦርነቱ ላይ ማድረጉ ላይ አንዳችም ቅዋሜና ቅሬታ ባይኖረንም ድርጅቱ ይህንን የህልውናን ዘመቻ ላይ እየተሳተፈበት ያለበት መንገድ እና ድርጅቱ በዘመቻው ላይ ያለውን ሚና ስናይ ግን በእጅጉ ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግል አኴያ ያልተቃኘ፣ ከአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ የነጻነት ትግል ጋር ያልተናበበ የክተተ ዘመቻውን ወደ ብአዴናዊና ብልጽግናዊ የስልጣን ማስጠበቂያነት ደረጃ ባወረደ መልኩ ልክ እንደ ኢዜማው አፍቃሬ ብልጽግና ፓርቲ አብን አፍቃሬ ብልጽግናዊ አቌም ማሳያ በማድረጉ  ድርጅቱ የተነሳለትን ህዝባዊ ዓላማና ግብን እንዳይስት የሚል ስጋትን ከወዲሁ መፍጠር መቻሉን ለማሳወቅ እንወዳለን።
አማራውም ሆነ አብን ወያኔን ለመዋጋት የግድ የብአዴንና የብልጽግና አፍቃሬ ደጋፊና ተከታይ መሆን አለባቸው ብሎ የሚያምን አለ እንዴ??
ወያኔን ስንዋጋ በኦሮሚያ በወሎ በአጣዬ በመተከልና በመሰል የሀገሪቱ ክፍል ውስጥ በብልጽግና መራሹ መንግስት ይዞታ ስር ውስጥ የተፈጸመንና የሚፈጸምን ጸረ አማራዊ ጥቃታዊ ክስተትን በዝምታ ማለፍ ማለት ነው ብሎ ነው እንዴ ድርጅታችሁ የሚያምነው??
ስለወለጋው መተከሉ ወሎና መሰል አደጋዎች የብአዴኑ አመራር እያየ እንዳላየ ሆኖ ዝም ማለት ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን እንደ ብልጽግናነቱ በእያንዳንዱ አደጋ ላይ እጁ ሙሉ በሙሉ የተነከረበት ከመሆኑ አንጻር የብአዴን ዝምታን ምስጢር መረዳት ይቻላል። ግን ይህንን ብአዴናዊን ዝምታን ሙሉ በሙሉ የአብን አድርጎ ማስተጋባት እጅግ ፈሩን የሳተ ከመሆኑም በላይ ወያኔን መዋጋትም ማለት እንዳልሆነ በግልጽ ልታውቁት ይገባል።
በአንዳንድ የድርጅታችሁ አመራሮች «ዛሬ በእኛና በመንግስት መካከል ልዩነት የለም።እርሰበርስ ጣት መጠቌቆምን ትተን በጋራና በአንድነት ተሰልፈናል » የሚለው መግለጫና አገላለጽ ግለሰባዊ ሳይሆን ድርጅታዊ የሆነ የአብን አቌም ከሆነ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ አብን ኦፊሴሊያዊ የአማራ ተወካይ ተቃዋሚ ፓርቲነቱ አክትሞ ልክ እንደ ኢዜማ ከብልጽግና ጋር የተደመረ አፍቃሬ ብልጽግና የመንግስት አካል የሆነ ፓርቲ ሆኗለት ማለት ነው።
ይህ ነው የድርጅታችሁ የአብን አሁናዊ ሁኔታና አቌም?? አማራ ከብልጽግና ያልተደመረ የአማራ አደረጃጀት እንዲኖረው ለዓመታት የታገለው በማንነቱ ላይ ያተኮረው የህልውናው ጠላት አንዱ ወያኔ ብቻ ሳይሆን ብልጽግናም (ኦህዴድ ብአዴን ኦነግ) ጭምር ቁጥር አንድ የአማራ ጠላት በመሆናቸው ነው። አብን እንዴት ነው አንደኛውንና ስልጣን ላይ ያለውን ጸረ አማራ የሆነውን ብልጽግናን ተቀብሎና ተደምሮ ወያኔን ብቻ  በመታገል የአማራን ህዝብ ወደ ሁለንተናዊ ነጻነት ለመምራት ተወካይ ሆኖ ታግሎ ለማታገል የሚችለው??
ወይንስ እንደ ብልጽግና አብን የአማራ ህዝብ ጠላት ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው ብሎ ያመነ ድርጅት ነውን ??
እናም አብን እንደ ድርጅት ይህንን ብዥታን ግልጥልጥ አድርጎ ሊያሳያ በሚችል መልኩ ሚናውን በአስቸኴይ በግልጽ ይለይ የሚለውን ወሳኝ ጥያቄ ለማቅረብ የተቻለው።
እናም መልስ እንፈልጋለን።
በመጨረሻም አንዳንድ የአብን አመራሮች ለአማራ ህዝብ ከመጮህ በወለጋ በወሎ ላለው ክስተት ተቆርቁረውና ተቆጭተው የጥብቅና ድምጻቸውን ከማስተጋባት ይልቅ 7/24ሰዓት ሊባል በሚችል መልኩ አማራው ሲጨፈጨፍ ተመልካችና ብሎም በመጨፍጨፍ ሚና እየተጫወተ ያለውን መከላከያ ተብዬን ሲያወድሱ ሲያደንቁ የሚውሉ የአገኘሁ ተሻገር የብአዴንና የብልጽግና ጠበቃ ሆነው የሚሞግቱ አንዳንዶች ደግሞ ስለአማራ መጮህ ይቅርና አማራ የሚለውን ቃልሊትዮጲያ በሚለው ተክተው የአማራ ህዝብ ተወካይነታቸውን የዘነጉ ወይም የለወጡ አይነት አቌሞችና ተግባሮችን ሲፈጽሙ የሚታይ ሆኗልና ድርጅቱ እንደ የአማራ ህዝብ ብቸኛና ትክክለኛ ተወካይነቱ ለመቀጠል እነዚህን ህጸጾች በአስቸኴይ የእርምት ማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድባቸው ይመከራል።
Filed in: Amharic