የልደቱ አያሌው ነገር …?!?
አቻምየለህ ታምሩ
ልደቱ አያሌው የጻፈውን “የመፍትሔ ሀሳብ” አነበብሁት። የአንድ ችግር መፍትሔ የሚጀምረው የችግሩን ሥረ መሠረት ከመረዳት ነው። ፈረንጆች የችግር ምንጭ ማወቅ የመፍትሔው ግማሽ ነው የሚል ብሒል አላቸው።
የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ምንጭና መፈልፈያ የሰው ስጋ የተራቡ፣ የሰው ደም የተጠሙ፣ የሰው አጥንት የሚቆረጥሙ፣ በጭካኔያቸው የፈጠራቸው አምላካቸው ሳይቀር እነሱን በመፍጠሩ የሚጸጸትባቸው የትግሬ ብሔርተኞች ለቅሚያ፣ ለዘረፋ፣ ለወረራና ለግድያ ያቋቋሙት ሕወሓት የሚባል የወንጀል ድርጅት ነው።
ልደቱ አለኝ ያለውን የመፍትሔ ሀሳብ ለማቅረብ ያን ያህል ረጅም ጽሑፍ ሲደርት ሲውል የኢትዮጵያ ዋነኛ ችግር ስለሆነው ስለዚህ የወንጀል ድርጅት አንድ አረፍተ ነገር እንኳን አልተነፈሰም።
ስለዚህ ልደቱ የደረተው የቃላት ጋጋታ የተከማቸበት ምንም ሀሳብ የሌለበት ወሬና ቅራቅንቦ እንጂ የኢትዮጵያ ችግር መፍቻ የመፍትሔ ሀሳብ አይደለም። ልደቱ አያሌው የአንድን ችግር ዋና ምንጭ ወደጎን በማለት አዲስ የመፍትሔ አሰጣጥ ዘዴ ተጀምሯል የሚል ከሆነ አለኝ የሚለውን የመፍትሔ ሀሳብ እንካችሁ ከማለቱ በፊት ስለዚህ አዲስ የመፍትሔ አሰጣጥ ዘዴ ሊነግረን ግድ ይለዋል።
የችግራችን ዋነኛ ምንጭ ሳያውቅ ለችግራችን መፍትሔ ሊያሳውቀን የሚነሳ ማንም ሰው አንድም የከፋ የጤና መቃወስ አጋጥሞት ነገር አለሙን ረስቷል አልያም እያጭበረበረ ነው። የአገራችንን ዋና ችግር፣ ሕመሟን ያላወቁና ያልተረዱ ሰዎች እየተነሱ ካላከምንሽ የሚሉት ፈሊጥ ድፍረት ነው። እነዚህ ሰዎች ራሳቸው መታከም የሚገባቸው በሽተኞች ናቸው። ልደቱ የትኛው ምድብ ውስጥ እንደሚወድቅ ባላውቁም የኢትዮጵያን ዋነኛ ችግር ሳያውቅ የመፍትሔ ሀሳብ አውቃለሁ ማለቱን ግን ቢተወው ይሻላል።
ልደቱ የመፍትሔ ሀሳብ ካላቀረብሁ ሞቼ እገኛለሁ ካለ ግን ዋነኛ የችግራችንን ምንጭ ሳያውቅ የመፍትሔ ሀሳብ ሊያሳውቀን አይቻለውምና እኛን ለማስተማር ከመሞከሩ በፊት የኢትዮጵያን ዋነኛ ችግር ከሚያውቁ ሰዎች እግር ስር ተቀምጦ የኢትየጵያ ችግር የሚፈታበትን የመፍትሔ ሀሳብ ራሱ ይማር።