>

የኢትዮጵያ መልክ ብዙ ነው! ልጆቿ ባንዳዎች፣ የማታውቃቸው ባለውለታዎች ሆነዋል...!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

የኢትዮጵያ መልክ ብዙ ነው! ልጆቿ ባንዳዎች፣ የማታውቃቸው ባለውለታዎች ሆነዋል…!!!

ጌታቸው ሽፈራው

ልጆቸ የምትላቸው፣ ሲቦጠቡጧት የኖሩት ይወጓታል። ካለ ከሌለ የውጭ ጠላት ጋር ሆነው ይዶልቱባታል። ከኢትዮጵያውያን ግብፅና ሱዳን ይቀርባሉ ብለው ደመኛ አድርገው ይስሏቸዋል። አንዳንዶቹ “ፍርስርሳዋ ሊወጣ ነው” ብለው መፍረሷን እንደመልካም ሕልም ያልማሉ።
ጋናዊቷ ግን በኢትዮጵያ መልክ አሸነፈች። ኢትዮጵያ ልጆቸ የምትላቸው ታሪኳን በሀሰት ሲያበላሹ ጋናዊቷ በኢትዮጵያ ታሪክ፣ እንደ አፍሪካዊት ደመቀችበት፣ አሸነፈችበት።
ኢትዮጵያ በርካታ ባንዳ ሲርመሰመስባት፣ የውጭ ዜጎች ግን ቀለሟን ይዘው መድረክ ላይ ሲያስተዋውቋት ከረሙ። ሲመቻቸው የኢትዮጵያ ልጆች ነን ሲሉ የነበሩ ከሃዲዎች መሳርያ  ጠምደው ንፁሃንን ለመጨረስ ያቀዱባቸውን ቦታዎች ጋናዊቷ አስተዋውቃ አሸነፈችባቸው።
ኢትዮጵያ ልጆቸ ናቸው በምትላቸው እየተወጋቸው፣ በማታውቃቸው ደግሞ በየመድረኩ በመልካም ትወሳለች።
የኢትዮጵያ ገናና ታሪክን የእኔ አይደለም ብለው የሚወጓት ልጆች ራሳቸውንም፣ ሀገርንም ለማክሰር ሲጥሩ፣ ሌሎች በኢትዮጵያ ገናና ታሪክ፣ ባሕል ይገንናሉ። ይታወቁበታል። ያስተዋውቁታል። ያሸንፉበታል።
በኢትዮጵያ በሌላ ላይ የተጫነ የተባለ ባሕል፣ ታሪክን፣ ጋናዊቷ የአፍሪካ ምልክት፣ ሊኮራበት የሚችል አድርጋ አቅርባ አትርፋበታለች። ክፋት ባይበዛ ከጋናዊቷ በፊት ኢትዮጵያውያን ብዙ ብዙ እናተርፍበት ነበር።
Filed in: Amharic