>

ቀጣዩ መርዷችንስ ከየት አካባቢ ይመጣ ይሆን??? (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ቀጣዩ መርዷችንስ ከየት አካባቢ ይመጣ ይሆን???

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

መጀመሪያ ለውጥ ከዚያም ሕግ የማስከበር ጦርነት እያለ ከሦስት ዓመት ላለፈ ጊዜ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ድራማ እየተወነ ያለው ወያኔ/ኢሕአዴግ አማራን ለመፍጃ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ወይም ሰበብ እንዲሆነው በማሰብ “የፌዴራል መንግሥት!” እና “ወያኔ!” ተባብሎ ለሁለት በመቧደን በፈጠረው የውሸትና የአሻጥር ጦርነት መርጦ ከፈጃቸው የሰሜን ዕዝ አማራ የሠራዊቱ አባላት እስከ ማይካድራ ሕዝብ፤ ከዚያም ደግሞ በዚሁ የውሸት ጦርነት “እርስታቹህን አስመልሱ!” ብሎ አታሎ ያስገባቸውንና ከኋላ በመከላከያ ከፊት ደግሞ በወያኔ እየመታ የፈጀውን በበርካታ ሽዎች የሚቆጠር የፋኖን፣ የአማራ ሚኒሻንና የአማራ ልዩ ኃይልን እልቂት ለማለባበስና ሚዛን ለመፍጠር ሲባል ወያኔ “ተደመሰሰ፣ ተቀበረ፣ ጠፋ!” ተብሎ እንዲወራ ተደረገና ሕዝቡ የፈጁትን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን አማራ “ወያኔ ተደመሰሰ!” በሚለው የውሸት ዜና አካክሶ ለወር ለሁለት ወር አርፎ እንዲቀመጥ ተደረገ!!!
አጭር ትውስታ (short term memory) ነው ያለው ያሉትን ሕዝብ የተፈጸመበትን ግፍና እልቂት በወርና በሁለት ወር የወያኔ የመደምሰስ የውሸት ዜና የወገኖቹን እልቂት እንዲረሳ ካደረጉት በኋላ እንደገና ደግሞ “የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ!” እንዲሉ እሱ ተጨፍጭፎ ባለቀና እንደ ቅጠል በረገፈ የሌለ ሒሳብ ፈጠሩና “ሒሳብ አናወራርዳለን!” ብለው ዝተው በመነሣት “ተደመሰሰ፣ ተቀበረ፣ ነፋስ ላይ የተበተነ ዱቄት ማለት ነው!” የተባለው ወያኔ ሎሌዎቹን “የተናጠል ተኩስ አቁም አደረግን!” እንዱሉና ትግራይንም ለቀው እንዲወጡ ካደረገ በኋላ ወዲያውኑም ከሰሜን ወሎ እስከ ደቡብ ጎንደር ድረስ እንዲሁም የሰሜን ጎንደርን ከፊል ክፍል ያለ ጦርነት እየተለቀቀለት እንዲገባ ከተደረገ በኋላ መጀመሪያ አጋምሳ ላይ ከዚያም ጭና ላይ አሁን ደግሞ ቆቦ ላይ ሕዝቡን እጅግ አረመኔያዊ በሆነ መንገድ እንደጨፈጨፈ እየነገሩንና በየተራ እያረዱን ይገኛሉ!!!
ወያኔ ሲገባበት ከየስፍራው ተፈናቅሎ የሸሸው ሕዝብም በአገዛዙ የብዙኃን መገናኛዎች ሳይቀር እየሰማቹህት እንዳላቹህት የወያኔ ኩሊ የሆነው አገዛዝ ለተፈናቀለው ሕዝብ ማቅረብ ያለበትን የእርዳታ አቅርቦት እስከአሁንም ድረስ እንዳያገኝ በማድረጉ ወይም በመንፈጉ በረሀብ እየተሰቃየ ይገኛል!!!
ተፈናቃይ ወገኖቻችን እስከአሁንም ነፍሳቸውን ማቆየት የቻሉትም ተፈናቅለው መጥተው ያረፉበትና በኑሮ ውድነት እንዲቆላ እየተደረገ ያለው ሕዝብ ከጉሮሮው ነጥቆ እያካፈለ በሚሰጣቸው ነው!!! ይሄም አንዱ አማራን የማደህየት አንዱ ስልታቸው መሆኑ ነው፡፡ እራሳቸው ያፈናቅላሉ አገዛዙ ለተፈናቀለው ሕዝብ የእርዳታ አቅርቦት ማቅረብ ሲኖርበት ማቅረብ ያለበትን እርዳታ ይነፍጋል ወገን ደግሞ የእርዳታ አቅርቦት የተነፈገው ወገኑ ዓይኑ እያየ በረሀብ እንዲያልቅ ስለማይፈልግ ከሀገር ውስጥ እስከ ዳያስፖራ ያለው ይረባረብና ነፍሳቸውን ለማትረፍ ጥረት ያደርጋል፡፡ የሚበዛውን ከሕዝብ የተሰበሰበ እርዳታ ግን አገዛዙ ወደ እጁ እንዲገባ በማድረግ የተፈናቀለው ሕዝባችን እንዳያገኘው ያደርጋል፡፡ በዓይነት የተሰበሰበውን ባለበት መጋዘን አቃጥሎ ያወድመዋል ወዘተረፈ. በሒደቱም አማራ በኢኮኖሚ እየደቀቀ፣ እየተሰበረ፣ እየቆረቆዘ ይሔዳል!!!
ወገን ሆይ! አገዛዙ የተፈጸመብህን የእልቂት ግፍ በኋላ ላይ ስትሰማው ዱብዳ እንዳይሆንብህና ችግር እንዳትፈጥር ጆሮህን ለማላመድ ያልህ የፈጸሙብንን የእልቂት መርዶ አልፎ አልፎ በመንገር ብቻ መረጃው እንዳይደርስህ ስላደረገ ነው እንጅ አረመኔውና አሸባሪው ወያኔ/ኢሕአዴግ ጭፍጨፋ የፈጸመባቸው ስፍራዎች እነዚህ ሦስቱ ስፍራዎች ብቻ እንዳይመስልህ!!!
ወያኔ ወሮ በያዛቸው ስፍራዎች ሕዝቡ እንዳያመልጥ መውጫ መውጫ በራቸውን በመዝጋት ነው በብዙ ስፍራዎች አረመኔያዊ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋውን የፈጸመው፡፡ ከጭፍጨፋ ማምለጥ የቻለውና ሸሽቶ በየጫካው የተደበቀው ብቻ ነው የተረፈው፡፡ እሱም በያለበት በረሀብ እያለቀ ነው!!! ወገኖቸ ሰው ይተርፋል ብላቹህ እንዳትጠብቁ፡፡ እነኝህ የተጨፈጨፉት ወገኖቻችን በአማራነታቸው እንደጨፈጨፏቸው ካወቃቹህ የተቀሩትን ወገኖቻችንን ሊተዋቸው እንደማይችል መገንዘብ ይኖርባቹሃል!!!
ወይኔ ወገኔ!!! ፀረ አማራው የወያኔ አህያ ብአዴን ከጭፍሮቹ አብኖች ጋር ሆኖ ተጫወተብህ!!! ገና ምን ዓይተህ እንዳትነቃ እንዲህ የማይሆን ተስፋ እየሰጡ እያጃጃሉ፣ እያፈዘዙና እያደነዘዙ ከየደጅህ በማጅራትህ ያርዱሃል ገና!!! ተኝተህ፣ ፈዘህና ደንዝዘህ ጠብቃቸው!!!
ሰው ይሄ ሁሉ ጉድ ከሆነ በኋላ እንኳ እንዴት አይነቃም??? አይገርምም??? በጣም የሚገርም ትንግርት እኮ ነው!!! ምን ዓይነት የሚያፈዝና የሚያደነዝዝ አዚም ነው ግን ያደረጉብህ ወገኔ???
Filed in: Amharic