ፓርቲው ከተመሰረተ ጀምሮ በምክትል ኘሬዝዳንትነት ኃላፊነታቸውን እስከ ለቀቁበት ድረስ ፓርቲውን በትጋት እና በከፍተኛ ሁኔታ ሲያገለግሉ የቆዩት የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት በተለያዩ ተደራራቢ ስራዎች ምክንያት ኃላፊነታቸውን በገዛ ፈቃዳቸው የለቀቁ ሲሆን ፤ በምትካቸው የፓርቲው ኘሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ የባልደራስ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የነበሩትን ኢ/ር ጌታነህ ባልቻ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ ተመረጡ ፤ባለፉት ሁለት አመት የተሰጣቸውን ሃላፊነት በአግባቡ ሲያከናውኑ ለቆዩት የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ለነበራቸው አገልግሎት እና ላደረጉት ከፍተኛ አስተዎፅዖ የፓርቲው ፕሬዝደንትና የስራ አስፈፃሚ አባላት ምስጋና እንዲሁም ለወደፊቱ መልካም ነገሮች ሁሉ እንዲገጥማቸው ተመኝተውላቸዎል።
ለአዲሱ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጌታነህ ባልቻ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው አስፈላጊ ድጋፍ በማድረግ ፓርቲው የተነሳለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ከጎናቸው እንደሚሆኑ የስራ አስፈፃሚ አባላት ገልጸዋል።