ይህ ሠራዊት ማለት…
አሳዬ ደርቤ
➜የመንግሥት አካላት “አያ ጅቦ” መጣልህ እያሉ ዜጎችን እንደ ሕፃን ልጅ የሚያስፈራሩበት፥
➜ለኢትዮጵያውያን እንጂ ለብልጽግናዎች የስጋት ምንጭ ያልሆነ፥
➜”እኛ ከወረድን የባሰ ይመጣል” በሚል ምክንያት የሥልጣን እድሜያቸውን የሚያራዝሙበት፥
➜የገዥው ፓርቲ አመራሮች ከህውሓት ጋር ተባብረው አማራን ማጥፋት ሲፈልጉ የሚጠቀሙበት፥
➜የባለፈውን ምርጫ ያለ ምንም ፉክክር ለማሸነፍ በሃይለኛው የተጠቀሙበት፥
➜ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ሳይሆን ከአማራ እናቶችና ሕፃናት ጋር የሚያጋጥሙት፥
➜ጫና ሲበዛባቸው አሰልፈው ፎቶ የሚያነሱት፣ ቀለል ሲላቸው ደግሞ የሚበትኑት፤
➜ድሮን ሊሸልሙት እንጂ በድሮን ሊመቱት የማይሹት፥
ወዘተ!️
ወዘተ!️
ወዘተ!️
ሼኔ በጃልመሮ ሳይሆን በብልጽግና ባለሥልጣናት የሚመራ የሽብር ቡድን ነው! ስለሆነም ከዚህ መንግሥት ከአምና የባሰ ቁማር እንጂ ከአምና የተሻለ አገር መጠበቅ አይቻልም!