>

የዚህ ሰራዊት ዝግጅት ለማን እና በማን ይመስልሃል??!? (ወንድወሰን ተክሉ )

የዚህ ሰራዊት ዝግጅት ለማን እና በማን ይመስልሃል????

ወንድወሰን ተክሉ 

፠ …. በሁለት «ታላቅ» ግዛት ለመሆኑ በቌመጡ ኋይሎች መካከል ኢላማ የሆነው የአማራ ሕዝብ እና ይህንን አደጋ የሚመክትበት ሕዝባዊ ኋይል እጅግ አስፈላጊነት!!
 
፠  ….. ይህ ገዳይና ጨፍጫፊ  ኋይል እየተዘጋጀ ያለው ለማን ይመስልሃል???
 
፨ 1-አንደኛው በሰሜን (ትህነግ)  ሌላኛው በደቡብ (በሸዋ በዳቦ ስሙ ኦነግ )  ከፍተኛ የተዋጊ ኋይሎችን ስምሪትንና ምረቃትን እያካሄዱ መሆናቸውን ያሳያል
፨2- የሁለቱንም ተዋጊ ኋይሎችን ጸረ አቢይነትን በመግለጽ «ታዲያ ለእኔ ለአማራው ምን ይመለከተኛል የማንም እንኩሮ ቢንጋጋ» በሚል ትምክህታዊ እይታ ጉዳዩን እንደለመድነው አቃላንና አናንቀን የምናየው ይሆናል። ይህን መሰሉ ንቀታዊ የእኛ እይታ ለጠላት ታላቅ እድል ለህዝባችን ታላቅ መከራን በማምረት ብዙ ዋጋ ማስከፈሉን ግን በተጨባጭ ገሀድ እያየነው ነው።
፨ 3- በሌላ በኩል ደግሞ የእነዚህን ኋይሎች አዘገጃጀትን እየተከታተለ የአጸፋ እርምጃን እየወሰደ ያለ ሁለት መንግስታዊ ኋይል አለን -እነሱም  አቢይ መራሹ የፌዴራል መንግስትና አገኝሁ ተሻገር መራሹ የአማራ ክልላዊ መንግስት -አሉንና የሚያሳስበን ጉዳይ የለም የምንልም እንኖራለን።  አባባሉ ግን እጅግ ጥቂት እውነታን (የብአዴንና ብልጽግና ለስልጣናቸው መዋጋትን  የሚመለከት) ከመያዙ በዘለለ አደጋው ሙሉ በሙሉ ባነጣጠረው የአማራ ህዝብ ህልውና ጋር አንዳችም አይነት ዝምድና እና ግንኙነት ስለሌለው እጅግ አዘናጊና ብሎም ህዝባችንን ዋጋ አስከፋይ እይታ መሆኑን ነው መረዳት የሚገባው።
፠ ታዲያ ይህንን የሚመጥን እርምጃና ዝግጅት ምንድነው ፦????
ይህ የጠላት ዝግጅት ከብልጽግና ስልጣናዊ ህልውና ይልቅ የአማራን ህዝብ ህልውና ላይ ያነጣጠረ የጠላት አሰላለፍ መሆኑን ስንመለከት-በዚህም በኦሮሚያ ክልል በተባለው አካባቢ ያለን የብሄረ አማራ ተወላጅን ብቻ ሳይሆን በሸዋ፣በወሎና ብሎም በጎጃም ላይ መጠነ ሰፊ ወረራን በመፈጸም የ«ትልቌን ኦሮሚያን» የግዛት ምስረታን ለመመስረት አላማው አድርጎ የተነሳ ኋይል መሆኑን በመረዳት ይህንን የሚመጥን አማራዊ የፋኖን ኋይል በማዘመኑ በማጠናከሩና በማስታጠቁ ላይ ዛሬ ነገ ሳይባል ዛሬውኑ የምንረባረብበት ስራዎቻችን እናደርጋለን ማለት ነው።
፨   የ«ታላቌን ኦሮሚያን» ግዛት ምስረታ ዓላማ በዳቦ ስሙ የኦነግ ሸኔ አላማ ነው ብለህ አንድም አማራ ፈጽሞ እንዳትወናበድ።   ጽንሰ ሀሳቡ ኦነጋዊ ይሁን እንጂ የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎትና ጥያቄን ከጥንታዊው የኦነግ ኋይል ይልቅ እኔ በተሻለና በበለጠ መልኩ እፈጽማለሁ በማለት የኦነግ ወራሽ ሆኖ ከኦነግም በላይ ኦነግ ሆኖ ያለው የአቢይ አላማና ውሳኔ መሆኑን እያንዳንዱ አማራ ማወቅ አለብህ።
ቀላል በሆነ ስልትና ታክቲክ ይህንን አላማ ለማስፈጸም ተግባራዊ እርምጃዎችና ወረራዊ ዘመቻዎች መፈጸም ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል። በወለጋ በመተከል በአጣዬ በከሚሴ የተፈጸመውና ዛሬም እየተፈጸመ ያለው የዚህ አላማ አካል ነው።
በመጀመሪያ አንድን አካባቢ ሽፍታ የተባለው ሚሊሺያ ወርሮ በመጨፍጨፍ ድምጥማጡን እንዲያጠፋ ይደረግና ነዋሪውን ነቅሎ እንዲያባርር ይደረጋል። ቀጥሎ ጭፍጨፋ ተፈጸመ ተብሎ ጭፍጨፋውን ለማስቆም በሚል መከላከያው ኮማንድ ፖስት አቌቌመ ተብሎ በሚሊሺያ የተወረረርውንና የወደመውን  አካባቢ መከላከያው እጅ እንዲገባ ይደረጋል።
የመከላከያው ኮማንድ ፖስትን የሚመራው የኦሮሞ ተወላጅ ጄኔራል ይደረግና ዋና ምድብ ስራውም በጭፍጨፋው ህይወታቸውን ለማዳን ብርርር ብለው የተፈናቀሉትን ወደ ተፈናቀሉበት ቀዬና እርስታቸው እንዳይመለሱ በማገድ አካባቢውን ባዶ ሆኖ እንዲጠበቅ ዩማድረግን ስራ መስራት ይሆናል።  በሂደትም በዚህ ባዶውን በቀረ ግዛት ውስጥ ጥቂት በጥቂት የኦሬሞ ተወላጆችን ማስፈርና የማስያዙን ስራ ይሰራል።  በፌዴራሉም ሆነ በክልል መንግስታት በኩል የተፈናቀሉትን አንዳችም ድጋፍና እርዳታ እንዳይሰጣቸው በማድረግ ተፈናቃዮቹን በርሃብ በችጋርና በበሽታ እንዲያልቁ አሊያም ወደተፈናቀሉበት ቀዬና ቤት ተመልሰው ዳግመኛ ለመቌቌም የሚያስችል አቅምና ጉልበት እንዳይኖራቸው በማድረግ የግዛት ማስፋፋቱን ስራ በስልትና በታክቲክ እየተሰራ ያለመሆኑን መላው አማራ ማወቅ አለበት።
፠ የዚህ ዓመቱ እቅድና ፕላን ግን ከዚህ ቀደምቶቹ ፕላኖች ሁሉ ይለያል፦ 
ዛሬ በዳቦ ስሙ ኦነግ ሸኔ ስም የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ሚሊሺያ ምስራቅ ጎጃም ደርሷል። በሚገርምህ ሁኔታ የአባይን ወንዝ መጉደል የሚጠባበቅ ቁጥሩ እጅግ በርካታ ታጣቂ ኋይል ጎጃምን ለማመስ የስንዝር ያህል በሆነ እርቀት ላይ በግልጽና በይፋ እንዲሰፍር ተደርጎ ያለበት ሁኔታ ላይ ነው ያለው። የሸዋንና የወሎን ግዛቶች ኦቶሞናይዝድ ለማድረግ ወሎን በሰሜን በወያኔ እንዲወረር እድርጎና በዚያ ጦርነት ወጥሮ በመያዝ በደቡብ በኩል የኦሮሞን ወራሪ ኋይል ብታዘምትበት ሊነሳ የሚችለውን ሁለት የኋይል ምንች ጎንደርንና ጎጃምን -ጌንደር በወልቃይት ጉዳይ የራሱ ግንባር የተጠመደ ከመሆኑም በላይ የአገኘሁ ተሻገር ቡድን በኦሮሙማው ዘመቻ ሙሉ በሙሉ ተባባሪ ከመሆኑ የተነሳ -ልክ አጣዬን አስወድሞ እንድትወረር እንዳደረገውና የሰሜን ወሎን በወያኔ በማስወረር ደረጃ ወሳኝ ሚና እንደፈጸመው ሁሉ – የሸዋና የደቡብ ወሎ በኦሮሞ ሚሊሺያዎችን መወረር ለመከላከል ፈጽሞ የኋይል ስምሪት እንዲፈቀድ አያደርግም። ስለዚህ የሚቀረውን ጎጃም ደግሞ በራሱ ላይ በሚለኮስ እሳት የተጠመደ ለማድረግና እጁን ወደ ወሎም ይሁን ሸዋ እንዳይዘረጋ ለማድረግ በመተከል ቻግኒ በኩል ጀምሮ በምስራቅ ጎጃም ቀጠና መጠነ ሰፊ ወረራን በመክፈት ወጥሮ መያዝ ነው።
ይህ የኦነግ ሸኔ ተብዬው እቅድ ፈጽሞ አይደለም። ከአራት ወራት በፊት ይህ ጸሃፊ አቢይ አህመድ በደቡብ ከሲዳማ ሽማግሌዎች ጋር ባደረገው ዝግ ስብሰባ ላይ ሽማግሌዎቹ «ለምንድነው አማራ ላይ ጦርነት የከፈታችሁት » ብለው ላቀረቡት ጥያቄ « እኛ አማራ ላይ ጦርነት የመክፈት ፍላጎት ኖሮን አልነበረም። ዝም ብላችሁ አርፋችሁ ተቀመጡ አልናቸው። እነሱ ግን ኦሮሞ አይገዛም ኦሮሞ ወራሪ ነው እያሉ መጮህ ጀመሩ። በዚህ ሁኔታቸው የተናደደ የቄሮ ወጣት ዋጋቸውን አቅምሷቸው ዛሬ ድንኴን ጥለው በማልቀስ ላይ ናቸው። ሆኖም ኦሮሞ ወራሪ ነው ለሚለው ስሞታቸው በቅርቡ ጎጃምና ጎንደር ድረስ በመሄድ ወረራ ምን እንደሆነ በተባር ፈጽመን እናሳያቸዋለን» በማለት የመለሰውን መረጃ ማስተላለፉን በማስታወስ ይህ በስመ ኦነግ ሸኔ የዳቦ ስም የሚደረግን ማንኛውም አይነት ጥቃትና ወረራን የአቢይ አህመድ አሊ እቅድና ፕላን ነው ብሎ ዛሬም በግልጽ ለማስታወስ ይወዳል።
፠ የአማራ ሕዝባዊ ኋይል፦   የአማራ ሕዝባዊ ኋይል ፋኖ አደረጃጀት ይህንን በሚመጥን መልኩ መዘጋጀት መታጠቅና ብሎም መጠነ ሰፊ የሆነ የምልመላና የስልጠና ስራዎችን በስፋት መፈጸም ይጠበቅበታል። ይህንን መጠነ ሰፊ ዝግጅትን እውን ለማድረግ ህዝባዊው ኋይሉ ህዝባዊና ሁሉን አማራ አቀፍ እንደመሆኑ መጠን በትጥቅ በስንቅና በሎጀስቲክስ የመላው አማራ ህዝብ ተግባር መሆኑን በመረዴት መጠነ ሰፊ ርብርብ መካሄድ ይገባዋል እንጂ ጉዳዩን ለመንግስት ማለትም ለብአዴን መራሹ ክልላዊ መንግስት በመተው የሚታይ መሆን የለበትም።
እዚህጋ መላው አማራ በግልጽ ማወቅ የሚገባው የአማራ ሕዝባዊ ኋይል አመሰራረት በክልሉ መንግስት ፍቃድና ይሁንታ መሆኑንና ይህ ሀቅ ግን ዛሬ የክልሉ መንግስት ለዚህ አማራዊ ኋይል የሚያስፈልገውን ሁሉ እያማላ ያለ አለመሆኑና እና ይባስም ብሎ በፋኖነት የሚደረግ ምልመላና ስልጠና አስፈላጊነቱ አይታየኝም በማለት ስልጠናዎችን ለማገድ እየጣረ ያለበትና ብሎም አልፎ አልፎ አሰልጥናችኋል ያላቸውን እስከማሰር የደረሰበትን ሁኔታ በማወቅ አማራው ይህንን ህዝባዊ ኋይሉን ሁለንተናዊ ጉዳይ የራሱ የግል ጉዳይ በማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ ለማሟላት መረባረብ ይገባዋል እንጂ ለአንዱ ብአዴና ብቻ ትቶ መቀመጥ እንደማይገባው መረዳት ይኖርበታል።
በዚህ አጋጣሚ በአጭሩ ለምጥቀስ የምፈልገው የአማራን ህዝባዊ ኋይልን አደረጃጀት እንዳይጠናከርና ብሎም ተዳክሞ እንዲከስም ለማድረግ አቢይና ብአዴን ከወስዷቸው በርካታ የማክሸፊያ እርምጃዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የአማራን ወጣት በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ እንዲታቀፍ ተመልመል ተቀጠር እያሉ ያስተጋቡት መጠነ ሰፊ የምልመላ ዘመቻ ዋና ዓላማና ግብ የሚፈጠረውን አማራዊ ኋይል ለማምከን ታምኖበት መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ። በዚህ የአማራን ሕዝባዊ ኋይል አፈጣጠር ማምከኛኘት ለቀረበው መከላከያውን ተቀላቀሉ ዘመቻ ላይ የተቃዋሚው አብን ከፍተኛ አመራሮች ክርስቲያን ታደለ ጣሂር መሀመድ ጋሻው መርሻና እንደነ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው አይነቶቹ በግልጽና በእደባባይ በመሳተፍ የአማራ ወጣት የአማራ ሕዝባዊ ኋይል ከመቀላቀል ይልቅ መከላከያውን እንዲቀላቀል መጠነ ሰፊ የቅስቀሳ ዘመቻን በተከታታይ በማድረግ ተሳታፊ ሆነዋል።
የአማራ ህልውና የሚጠበቀው በመከላከያ ሰራዊቱና በመንግስት ተብዬ ሳይሆን በራሱ በአማራዊ ኋይልና ክንድ (ከፈጣሪ በታች) ብቻ እና ብቻ ሆኖ ሳለ እነዚህ ወገኖች ግን መከላከያውን የአማራ አዳኝና ታዳጊ በማድረግ መላው የአማራ ወጣት እንዲቀላቀል ሲጎተጉቱ ዋና ዓላማቸው አማራዊው ወጣት በመከላከያ ውስጥ ተቀጥሮ ወገኑን እንዲታደግ ለማድረግ ሳይሆን የተፈጠረውን የአማራ ሕዝባዊ ኋይል ተቀላቅሎ እንዳያጠናክርና በውጤቱም የአማራን ሕዝባዊ ኋይል አክሽፎ ለማክሰም በሚል ነው።  (አማራው በመከላከያውን ተቀላቀል ጥሪ ውስጥ የተዘጋጀለት ጸረ አማራዊ ሴራና ምስጢር -በሚል ርእስ ስር የተዙጋጀውን ሰፊ ጥልቅ ዝርዝር መልእክት ተመልከቱ)
 
፠ መቌጫዊ ቃል፦
ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ጩህት ፈጽሞ አይሰራም። አቢይ ከመስከረም 24በኋላ አማራውን ይክዳልም አባባል ዘገምተኝነትን ያሳያል። አማራው በአቢይ የሚካደው መስከረም 24ሳይሆን መሪዎቻችንን በገደለበት 2019 ጀምሮ አማራው 100% በአቢይ የተካደና ዛሬም በጠላቱ አቢይ ላይ የተለጠፈ መሆኑን ማወቅ ግዴታ ነው።
የአማራን የህልውናን ትግል በፖለቲካ ፓርቲዎች በግለሰቦችና ብሎም በጎጥና በሀገር ሁኔታ አንጻር ለመቃኘትና ለማየት መሞከር የድንቁርና ትልቁ መገለጫ ነው። የአማራ የህልውና ትግል ከማንም በላይ ነው። ልድገመውና ከሁሉም በላይ ነው። አብንም ሆነ አመራሮቹ ይህንን ቀይ መስመር የሚያልፉ ከሆነ ወይም አልፈው የተገኙ ከሆነ ጨውነታቸው አብቅቶ ድንጋይነታቸውን ያሳዩ ይሆኑና እንደ ድንጋይ ይጣላሉ እንጂ  የአማራን ትግል ዋጋ እንዲያስከፍሉ አማራው አይፈቅድላቸውም።
የአማራን ሕዝባዊ ይል -ፋኖን አርበኛ ዘመነ ካሴኔ ካፕቴን ማስረሰ ሰጠኝ ፊት ቀድመው በማስተባበር ላይ ያሉ መሆናቸውን እያንዳንዱ አማራ አይታል ሰምታልም።  አሁን የሚፈለገው መላው አማራ ዘመነ ካሴን ማስረሻ ሰጤንና የአማራ ሕዝባዊ ኋይል ሆኖ አማራዊ ህልውናውን ማስጠበቅና መከላከልን ነው።
ነገ ሳይሆን አሁን ዛሬ መደረግ ያለበት ይህ እርምጃ ነው!!!!!
ድል ለታላቁ የአማራ ሕዝብ
Filed in: Amharic