>

ይድረስ - ለአንዱአለም አራጌ - ጉድህን ስማ..!!! (አዲስ አበባ ባልደራስ)

ይድረስ – ለአንዱአለም አራጌ – ጉድህን ስማ..!!!

አዲስ አበባ ባልደራስ

በመሳሪያ ግዳጅ አደገኛ ውንብድና ከሜታ ቢራ እስከ ካቴድራል ት/ም ቤት መሄጃ የሚገኘው ንግድ ባንክ በከባድ ዘረፋ እና  አሰቃቂ ሰዉ ግድያ ወንጀል የሚታወቀው በቃሊቲ ዞን1 ልዩ ጥበቃ እድሜ ልክ ተፈርዶበት ታስሮ የነበረው አንተም ላይ ድብደባ የፈፀመው ይባስ አሰፋ በእስክንድር ነጋ ላይ ምስክር ሆኖ በመምጣቱ ምን ተሰማህ?
አቶ አንዱአለም አራጌ ከዚህ በኀላ የምጠይቅህ አጭር ጥያቄ? ለእስክንድር ነጋ መከላኪያ ምስክር ትሆናለህን?
1_..ፓርቲህ ኢዜማ የዉሸት ምስክር አሰልጥኖ በሰዎች ሕይወት ላይ የሚጫወተውን መሰሪው ብልፅግና ጋር በብርሃኑ ነጋ አማካኝነት ኳልሽን በመፍጠር አብሮ መስራቱ ምን ለማትረፍ ይሆን?
2_..ፍትህ በውሸት ስትጭበረበር ሃቀኛ ልጇቿን ስትበላ ትላንት ባንተ ይደርስ የነበረው በደል ዛሬ በኦህዴድ/ ብልፅግና ተደግሞ ስታየው ምን አይነት ስሜት ይኖርሃል?
3_…አቶ አንዱአለም ከዚህ ወዲያ ፓርቲው ላይ መቆየት ውሸትን ከመተባበር ውጭ ምን ፋይዳ አለው?
4_…ኢዜማን ለቀህ ባልደራስን በመቀላቀል ስለፍትህ  የተከፈለ ሃቀኛ መስዋዕትነት መሆኑን በተግባር ታሳያለህ ወይስ ???
አቶ አንዱአለም አራጌ አንተ የምታቀው ደብዳቢህ ይባስ አሰፋ የመንግስት ሀሰተኛ ምስክር መሆኑን የተሰማህን አስተያየት እንድትገልፅ በአክብሮት እንጠይቅሃለን።
ወንድም እግዜር ይቅር ይበልህ/3/
Filed in: Amharic