>

የሰሜኑ ጦርነት በመንግስት ሳይሆን  በህዉሀት እቅድ እየተመራ ነዉ....!!! (ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ)

የሰሜኑ ጦርነት በመንግስት ሳይሆን  በህዉሀት እቅድ እየተመራ ነዉ….!!!
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ

የኢትዮጵያ መንግስት ከትግራይ ከወጣ በኋላ እና የሕወሓት ታጣቂዎች እንደገና ማንሰራራት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በኢትዮጵያ መንግስት ዕቅድ ላይ ተመስርቶ ሳይሆን ሕወሓቶች በፈለጉት እና ባቀዱት ልክ ነው እየሄደ ያለው ።
መጀመሪያ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ከትግራይ እንዲወጣ ጥረት አደረጉ ወጣ።
ቀጥሎ ሰሜን ወሎን ለመያዝ አቀዱ ያዙ።
ደቡብ ወሎን ለመያዝ ባደረጉት ጥረት የደቡብ ወሎ ሕዝብ ወጥቶ ሲከላከላቸው አፈገፈጉ።
ወር ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ተመልሰው ወደ ደቡብ ወሎ ገቡ።
በሶስት ቀናት ውስጥ ውርጌሳን እና ውጫሌን ያዙ።
በአራተኛው ቀን ደግሞ ሀይቅ ከተማ ለመግባት አምስት ኪሎ ሜትር ቀራቸው።
ወደ ባቲ ለመግባት በወረባቦ ቢስቲማ በኩል መንገድ ጀምረዋል።
መንግስት እስካሁን ከራያ ቆቦ እስከ ደቡብ ወሎ ውጫሌ ድረስ ያፈገፈገበት መንገድ እና የሕወሓት ታጣቂዎችም ከተሞችን የያዙበት መንገድ ተመሳሳይ ነው።
ሕዝብ ከመንግስት ጎን ነኝ እያለ።
ለብዙ አመታት የተገነባ የጦር ሰራዊት ፤ በቂ ባጀት እና ሎጂስቲክ ያለው ኃይል ፤ እንዴት ደጀን ባልሆነው ሕዝብ መሐል ያለው ሕወሓት ይህን ያህል ርቀት ሊጓዝ ቻለ?
ለዚህ መልስ እስኪገኝ ድረስ ግን በሕወሓት ዕቅድ እና ፍላጎት ውስጥ እየተሽከረከረ ባለው ጦርነት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር የዋግ ኽምራ ፤ የደቡብ ወሎ እና የሰሜን ወሎ ዞን ሕዝብ ያለመጠለያ በረሀብ እና በችግር ውስጥ ነው ።
Filed in: Amharic