>
5:13 pm - Friday April 19, 0920

ከ40 በላይ የባልደራስ እንዲሁም የተለያዩ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ታስረዋል...!!! (ጌጥዬ ያለው)

ከ40 በላይ የባልደራስ እንዲሁም የተለያዩ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ታስረዋል…!!!
ጌጥዬ ያለው

“… በጅምላ ከታሰሩት መካከል ሁለቱ በዋስ ሲለቀቁ 40ዎቹ ለሰኞ ተቀጠሩ !
ዛሬ 12.02.2014 በጠዋት ከ5 ፖሊስ ጣቢያ ወደ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ ተብሎ በተነገረን መሰረት ሄደን ነበር። በቦታውም ስንደርስ ትላንት ታፍሰው የታሰሩ ወጣቶችን ለማየት እና ለማስተዋል ሞከርን። የባልደራስ አባላት ብቻ አይደሉም ትላንት ታፍሰው የታሰሩት ። የሌላ ፓርቲ አባላት ፣ ጋዜጤኞች ፣ አርቲስቶች ፣ ፍትሕ ፈላጊ የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ሌሎችም ይገኙበታል። ጉዳዩ ግልፅ ነው። ስለዚህ ጉዳዩ የአንድ ፓርቲ ብቻ አለመሆኑን መገንዝብ ያስፈልጋል።
    በጅምላ ከታሰሩት መካከል ሁለቱ በዋስ ሲለቀቁ 40ዎቹ ለሰኞ ተቀጠሩ !
     የእነ እስክንድር ነጋን የችሎት ውሎ ለመታደም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጥቅምት 11/2014 ዓ/ም የሄዱ 42 የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው ዕለት በፓሊስ ታፍሰው  መታሰራቸው ይታወቃል።
     አቶ እስክንድር በእስር ቤት የደረሰባቸውን ድብደባ በችሎት የሰሙ ታዳሚዎች እያለቀሱ ችሎቱን አቋርጠው የወጡ ሲሆን ፤ ከችሎት ወጥተው በመንገድ ላይ ፖሊስ በጅምላ አፍሶ በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ቆይተው ፤ ምሽት አንድ ሰዓት ወደ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው ታስረው ነበር። ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
  ፖሊስ በዛሬው ችሎት እንደገለጸው ተጠርጣሪዎቹ ” ችሎት ውስጥ ረብሸዋል፣ ሲወጡ ደግሞ ፍትህ የለም ፣ መንግስት የለም በማለት ሁከት እና ብጥብጥ በመቀስቀስ ”  ሲንቀሳቀሱ መያዙን ገልጿል ። ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ የምስክሮችን ቃለ ለመቀበል  እና ማስረጃቸውን ለማሰባሰብ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ቆጠሮ ጠይቋል።
የ42ቱ ተጠርጣሪዎች ጠበቆች ፖሊስ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ አቤቱታ ውድቅ እንዲሆን በመጠየቅ ፤ ” በችሎት ውስጥ ተፈጸመ ለተባለው ድርጊት ፖሊስ የሚመለከተው ሳይሆን በወቅቱ  ችሎቱ በራሱ ትዕዛዝ የሚሰጥበት ነው። ሆኖም ግን ችሎቱ ምንም አይነት ትዕዛዝ ባልሰጠበት ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ተገቢ አይደለም”  ብለዋል ።
    ከዚህም በተጨማሪ ” ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀበት ምክንያት በሕግ ምንም አይነት ድጋፍ ” የለውም በማለት የጊዜ ቀጠሮው ውድቅ እንዲሆን በመጠየቅ  ከእስር እንዲለቀቁ ለፍ/ቤት ጥያቄ አቅርበዋል ።
  ግራና ቀኙን ያከራከረው ፍርድ ቤት ሁለት ህፃናት ልጆች ያላቸውን ተጠርጣሪዎች በዋስትና እንዲወጡ፣ የተቀሩትን ደግሞ  የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ወደ 3 ቀን በመቀየር ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም  እንዲቀርቡ፣  እንዲሁም የተጠርጣሪዎቹን ተሳትፎ ለይቶ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል ።
   እስረኞች በተያዙበት ወቅት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ችሎቱም ለደረሰባቸው ጥሰት ክስ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል ።
ከእስረኞች መካከል  የሚከተሉት ይገኙበታል፦
ሰናይት ታደገ
ማሕሌት እሸቱ
ወግደረስ ጤናው
ምስራቅ ሞገስ
ቢንያም ታደሰ
ሳሙኤል ዲሚትሪ
ፋሲል መሲ
አብይ አባይነህ
አዶኒያስ ገሰሰ
ፍቅረማርያ ሙላቱ
አዳም ውጅራ
በላይ ጥላሁን
መሰረት ማሞ
ፍቅሬ ታደሰ
ደሳለኝ ገረሱ
አሌክስ ሸገር
እሙሽ (ፈረንሳይ)
ተስፋዬ ከበደ
ዳዊት ንጉሴ
ፋሲል ማሞ
ናርዶስ ተስፋዬ…….ይገኝበታል።
Filed in: Amharic